
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የህዝባዊ ሃይሉ ዋና አዛዥ ኮማንደር አሰፋ ማሩ የህዝባዊ ሃይሉን ወቅታዊ አቋም በተመለከተ ሲናገሩ ‘’ህዝባዊ ሃይላችን በኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋውን ዘረኛና አፋኝ የወያኔ አገዛዝ ከህዝባችንና ከአገራችን ጫንቃ ላይ አስወግዶ በምትኩ ፍትሃዊ ና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ከተመሰረተ ጀምሮ ባለፉት ጥቂት አመታት በርካታ ስራዎችን በመስራት አሁን አስተማማኝ ድርጅታዊ አቋም ላይ ይገኛል’’ ሲሉ በምረቃው ስነ ስርአት ላይ ለተገኙት የክብር እንግዶች ተናግረዋል። ኮማንደር አሰፋ ማሩ አያይዘው እንደገለጹት ‘’ይህን የአምስተኛ ዙር ምርቃት ከቀደምቶቹ 4 ዙር ምርቃቶች የሚለየው የኢትዮጲያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ እና የግንቦት ሰባት የፍትህ፣ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ተዋህደው ባንድ ድርጅታዊ ጥላ ስር ትግላቸውን አስተባብረው ለመታገል የሚያደርጉትን የውህደት ሂደት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ያደረሱበት ወቅት ላይ መደረጉ ነው ‘’ ሲሉ አስረድተዋል።
ኮማንደሩ በስተመጨረሻም ‘’ይህ የህዝባዊ ሃይላችን ስልጠና በግንቦት ሰባት ስም ከሚደረጉት ስልጠናዎች የመጨረሻው ይሆናል በማለት የገለጹ ሲሆን ለተመራቂ ታጋዮች ባስተላለፉት መልዕክት ‘’ስልጠና ላንድ ታጋይ የትግሉ የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲሆን በስልጠና ላይ ያገኛችሁትን ትምህርት በተግባር ለቆምንለት ዓላማ እና ተልዕኮ በቁርጠኝነት እንደምታውሉት ሙሉ እምነቴን እገልጻለሁ‘’ ካሉ በኋላ የአገርና የትውልድ ጠላት የሆነውን የፋሽስቱ ወያኔ አገዛዝን ከኢትዮጵያ ምድር ጠራርገን ለማስወገድ በምናደርገው እልህ አስጨረሽ ትግል አብረን እንቁም፤ ሕዝባዊ ሃይላችንንም ተቀላቀሉ ሲሉ ለኢትዮጵያ ህዝብ ወገናዊ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በሀገር ውስጥ እንደማእበል እየገነፈለ ያለውን የአታግሉን የሕዝብ ጥያቄ በተደራጀና በተቀነባበረ መንገድ በተገቢው መልኩ ለማስተናገድ እንዲችል እንደ ድርጅት ከመቼው ጊዜ በላይ ራሱን እያደራጀና እያጠነከረ እንደሚገኝና ምቹ አታጋይ ተቋም ሆኖ ለመውጣት ሌት ተቀን እየደከመ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ቀደም በ 4 ተከታታይ ዙሮች በርካታ ታጋዮችን ማስመረቁን መዘገባችን አይዘነጋም።
No comments:
Post a Comment