Friday, 22 May 2015

የወያኔን የይስሙላ ምርጫ አስመልክቶ ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢትዮጵያ ህዝብ የተላለፈ ጥሪ


May 22, 2015
የተከበራችሁ እናቶቼና አባቶቼ፤ እህቶቼና ወንድሞቼ እንዲሁም ልጆቼ የምትሆኑ ወጣቶች!!
dr-berhanu-Negaአገራችን የምትገኝበትን አስጨናቂ ሁኔታ ሁላችንም እንረዳለን። የህወሓት/ኢሕአዴግ ፋሽስቶች ቡድን እየገረፈ፣ እያሰረና እየገደለ በካርዳችሁ መርጣችሁ የምርጫ ድግሴን ካላሞቃችሁልኝ እያለ ነው። እንኳንስ ዛሬ ታዛቢ በሌለበት፤ ታዛቢ እያለም እንኳን ወያኔ የሕዝብን ድምጽ በትክክል ቆጥሮ አያውቅም። ወያኔ ለህዝብ ድምጽ ምንም ደንታ የሌለው የኋላቀር ወሮበሎች ቡድን ነው::
ለስንት አስርት ዓመታት ለወያኔ ባርነት እንገብራለን? ለሀያ አስምስት ዓመታት ተገዛን፣ ተገደልን፣ ተቀጠቀጥን፣ ታሰርን፣ ተሰቃየን፣ ልጆቻችን በአገራቸው ተስፋ ቆርጠው ሲሰደዱ በበረሀ ንዳድ አለቁ፤ በባህር ሰጥመው ቀሩ፤ በባዕዳን አረመኔዎች እንደከብት ታረዱ፤ ቤንዚን ተርከፍክፎባቸው ተቃጠሉ። ሀይማኖታችን ተዋረደ፤ ባህላችን ረከሰ፤ ታሪካችን ተናቀ። በልማት ስም ወልደን ከከበድንበት ተፈናቀልን፤ አገራችን አደገች እያለ ሕዝብ በኑሮ ውድነት ተሰቃየ። በልቶ ማደር ብርቅ ነው። እንደሙጫ የሚያጣብቀንን ማህበረሰባዊ ትስስር በስልጣን ለመቆየትና ህብረተሰቡን ለመዝረፍ ሲል ሆን ብሎ እያፈራረሰው ነው:: ይኽ ሁሉ አይበቃንምን? ይኸ ሁሉ አይመረንምን?
ወላጆቼ፣ እህት ወንድሞቼ!ውርደት ይብቃን። የተረገጥንና የተገደልን አንሶን ፍጹም ማንንም ሊያሞኝ በማይችል የለበጣ ምርጫ ወደን የተረገጥን፤ ፈልገን የተገዛን ለማስመሰል ወያኔ የሚያደርገውን ሩጫ እናክሽፈው:: ከፊታችን ያለውን ምርጫ ባለመሳተፍ ምሬታችንን እንግለጽ።
ዛሬ በግሌ እና በአርበኞች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ። በዚህ ምርጫ አትሳተፉ። የምርጫ ካርዳችሁን ቀዳችሁ ጣሉት። እናምርር። ካላመረርን ለውጥ ሊመጣ አይችልም። ይልቅስ ለማይቀረው የመጨረሻው ትግል ራሳችንን እናዘጋጅ::
አርበኞች ግንቦት 7፣ ከትግራይ፣ ከኦሮሞ፣ ከአፋር፣ ከኦጋዴን፣ ከጋምቤላ፣ ከቤሻንጉል ድርጅቶች ጋር ትብብር በመፍጠር የአገር አድን ኃይል በመገንባት ላይ ነው። እኛ ልጆችህ በብሔርም ሆነ በሀይማኖት አንከፋፈልም። ከትግራይ እስከ ኦጋዴን፤ ከአፋር እስከ ጋምቤላ ሁሉንም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ያካተተ ስብስብ ፈጥረን በኅብረት አገዛዙን እየታገልን ነው። ይህ ትግል ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ ትግል ነው። የትግሉም ባለቤት የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ነው። ክርስቲያን ሙስሊም፤ ወንድ ሴት፤ ወጣት አረጋዊ ሳንል፤ በብሔርም ሆና በቋንቋ ሳንከፋፈል ሁላችንም ይህን አስከፊ ሥርዓት በቃህ እንበለው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ!
ይህንን የውሸት ምርጫ ባለመሳተፍ ለለውጥ ያለህን ዝግጁነት አሳይ! ደግሜ እለዋለሁ – የምርጫ ካርድህን ቅደድ!!!
የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ሆይ!
እናንተ የሕዝብ አካላት ናችሁ። በወገኖቻችሁ ላይ አትተኩሱ። ይልቁንስ አፈሙዛችሁን አገራችንን ለውርደት በዳረገውና በሙስና በተጨማለቀው ዘራፊው የህወሓት አገዛዝ ላይ አዙሩት። ታሪካችሁን ከምታበላሹ፤ ታሪክ ሥሩ። ለራሳችሁ፣ ለቤተሰቦቻችሁ፣ ለልጆቻችሁ እና ለሕዝብ የሚጠቅም አገርና መንግሥት እንዲኖረን የእናንተ የግልም ሆነ የጋራ ተነሳሽነት ወሳኝ ነው። ወያኔ ህዝቡን የሚዘርፈው በእናንተ ትከሻ ላይ ቆሞ እንደሆነ ላንዳፍታም አትርሱት:: እንደመላው ህብረተሰብ እናንተም በነጻነትና በኩራት የምትኖሩበት ሀገር እንደምትሹ አልጠራጠርም:: ስለዚህም ይህን የህወሓት የውሸት ምርጫ ተቃወሙ። ዛሬውኑ ነፃነትና ፍትህ ከጠማው ወገናችሁ ጎን ቁሙ።
የኢትዮጵያ ወጣቶች፤ ትግላችን እስከ ነፃነት ድረስ ይቀጥላል። ነፃነታችንን በእርግጠኝነት በትግላችን እንቀዳጃለን። የምትወዷት፣ የምትኮሩባት አገር – ኢትዮጵያ – ትኖረናለች። ለዚህ ግን ዛሬ ተደራጅተን፣ ፀንተን መታገል የሁላችንም ኃላፊነት ነው። ዛሬ ሁላችንም በፍላጎትና በመንፈስ የተገናኘን ነንና ሁሉም በያለበት ትግሉን ያጧጡፍ። ውጤቱ ቀድሞ በታወቀው በዚህ ምርጫ አለመሳተፍ ለትግሉ ያለንን ቁርጠኝነት ማሳያ ነውና ለውሸት ምርጫ ያለን የመረረ ተቃውሞ በምርጫው ባለመሳተፍ እናሳይ።
ነፃ እንወጣለን!
የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነቱ ባለቤት ይሆናል!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
CategoryAmharic

Wednesday, 20 May 2015

ለውጤታማ ድል፤ ተግባራዊ ትብብር!


def-thumbበመርህ ላይ በተመሠረተ ትብብር ወያኔን በጋራ ታግሎ ማሸነፍ እና በየደረጃው የሚገኝ የመንግሥት ስልጣን ነፃ፣ ፍትሀዊና ተዓማኒን በሆነ የሕዝብ ምርጫ ብቻ የሚያዝበት የፓለቲካ ሥርዓት መገንባት የአርበኞች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ተልዕኮ ነው። በዚህም መሠረት አርበኞች ግንቦት 7፣ በተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ከሚገኙት ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ ከጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ፣ ከቤንሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ እና ከአማራ ዴሞክራሲ ኃይል ንቅናቄ ጋር በመርህ ላይ በተመሠረተ ትብብር በጋራ ለመታገል የሚያስችለውን ስምምነት ላይ እየደረሰ ነው።
ይህ የትብብር ጥረት ብዙ ጉዳዮችን ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ የኢትዮጵያን ሕዝብ ጠንካራ ድጋፍ ይሻል።
  1. ህወሓትን ከስልጣን የማባረር ኃላፊነት የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ኃላፊነት ነው። ይህ ትልቅ ኃላፊነት በአንድ ወይም በጥቂት ድርጅቶች ላይ መጣል የለበትም። ይህ ትብብር ይህንን የጋራ ኃላፊነትን በጋራ ለመወጣት የተደረገ በዓይነቱ አዲስ የሆነ ተግባራዊ ትብብር ነው።
  2. ህወሓት በትግራይ ውስጥ መቶ በመቶ ተቀባይነት ያለው አስመስሎ ፕሮፖጋንዳ ሲነዛ ቆይቷል። ህወሓት፣ የትግራይና የአማራ ሕዝብ በጠላትነት እንዲተያዩ፤ የትግራይ ሕዝብ ራሱን ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጥሎ እንዲያይ የረዥም ግዜ እቅድ አውጥቶ ተግባራዊ እያደረገ ነው። ይህን እኩይ ሴራ ማክሸፍ የምንችለው በፀረ-ወያኔ ተግባራዊ ትግል በጋራ ስንቆም ነው። ይህ ትብብር ለአገራችን አንድነትና ዘላቂ ሰላም ወሳኝ የሆነው በፀረ ህወሓት አቋሙ የጠነከረ የትግራይ ሕዝብ እንዲኖር ወሳኝ ሚና ይኖረናል ብለን እናምናለን።
  3. በአሁኑ ሰዓት የህወሓት አገዛዝ የቆመው ዘረኛ በሆነ መንገድ ባደራጀው ጦር፣ በስለላ ድርጅቱ እና ኃያላን መንግሥታት ለጥቅማቸው ሲሉ በሚያደርጉለት ሁለተናዊ ድጋፍ ነው። እነዚህ ህወሓትን ደግፈው የያዙ ኃይሎች ጠባቸው ከመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር መሆኑን በተግባር የምናሳያቸው ተግባርን መሠረት ያደረገ ጠንካራ ኅብረት ፈጥረን ስንገኝ ነው።
  4. ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ነባራዊ ማኅበራዊ ሀቅ ምክንያት ከፓለቲካ አመለካከት ይልቅ በወል ማንነት ላይ የተመሠረቱ ድርጅቶች የሚበዙበት ሆኗል። የኢትዮጵያን ችግር ለመፍታት ሁለቱን አመለካከቶች መሠረት አድርገው በተደራጁ ድርጅቶች መካከል ትብብር መፍጠር ወሳኝ ነው።
አርበኞች ግንቦት 7፣ ከላይ በአጭሩ በተዘረዘሩት ምክንያቶች እየተፈጠረ ያለው ትብብር የኢትዮጵያን የፓለቲካ መልካምድር ወደተሻለ ሁኔታ ለመቀየር የራሱ አስተዋጽዖ ይኖረዋል የሚል እምነት አለው። በዚህም ምክንያት መጠናቀቅ የሚገባቸው ነገሮች ተጠናቀው ትብብሩ በይፋ እንዲመሠረት የበኩሉን ጥረት ያደርጋል።
ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች ሳቢያ የትብብር አድማሳችን ከዚህም መስፋት አለበት ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 ያምናል። ስለሆነም፣ በተለያዩ ምክንያቶች ለጊዜው የትብብር ማዕቀፍ ውስጥ ያልገቡ የፓለቲካ ድርጅቶች ወደ ትብብሩ እንዲመጡ፤ ለሀገራችን እና ለሕዝብ በጋራ መሥራት በምንችላቸው ጉዳዮች ላይ እንድመክር ጥሪውን ያስተላልፋል። በመመካከር ህወሓትን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን ለሁላችን የሚበጅ የተሻለ ሥርዓት በአገራችን ላይ እንዲመሠረት መሠረት መጣል እንችላለን ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 በጽኑ ያምናል። ስለሆነም እንነጋገር፤ ለሁላችን የሚበጀንን መንገድ በጋራ እንፈልግ፤ የህወሓት ፋሽስታዊ አገዛዝን በጋራ እንታገል፤ ከራሷ ጋር የታረቀች አገር ጥንስስ እኛው ውስጥ እንፍጠር ይላል።
ለውጤታማ ትግል እንተባበር!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

CategoryEditorial

Saturday, 16 May 2015

አገራችንና ሕዝባቸን ማዳን ግባችን አድርገን በአንድነት አንሰራለን። የጋራ መግለጫ



May 15, 2015
stamps Joint press release
አገራችንና ሕዝባቸን ማዳን ግባችን አድርገን በአንድነት አንሰራለን።
የአንድነት፣ የመከባበር፣ የመቻቻል እና የነፃነት ምሳሌ የሆነችው አገራችን እኩይ አላማቸውን ለማሳካትና የስልጣን እድሜያቸውን ለማራዘም በሚንከላወሱት የወያኔ ቡደን አገራችንና ሕዝባችን ከምንግዜውም በከፋ ደረጃ ላይ አድርሰዋታል።
ወጣቱ በአገሩ ላይ ተምሮና ሰርቶ የመኖር እድሉ ለወያኔው አገዛዝ ማደር አልያም አገሩን ጥሎ መሰደደ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ አገሩን ጥሎ የሚሰደደው ዜጋ ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ለመሰደድ በሚያደርገው ጉዞ ምን ያህሉ በበርሃ እንደሚቀርና የአሳ እራት እንደሆነ የመገናኛ ብዙሃን በሰፊው ሲዘግቡት ቆይተዋል።
በተለያየ አገር በስደት ከሚፈልጉት አገር የደረሱትና የእለት ጉርሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ ደፋ ቀና በሚሉበት ሂደት ውስጥ በደቡብ አፍሪካ በቁማቸው በአሳት መቃጠል፣ በሊቢያ አይናቸው እያየ መታረድና በጥይት መደብደብ ሆኗል እጣ ፋንታቸው።
እናም አገርና ሕዝብ በእንደዚህ አይነት አስከፊ ሂደት መቀጠል የለበትም የወያኔም የግፍ አገዛዝ ሊበቀው ይገባል በሚል ቀደም ብለን ይህን በታኝ ስርዓት በትጥቅ ትግል እየተፋለምን ያለን ደርጅቶች እኛ አንድ ሆነን ሕዝቡን አንድ በማደረግ አገራቸንና ሕዝባችንን ነፃ ማውጣት የሚገባን ወቅት አሁን ነው በሚል ስርዓቱን ለማስወገድ በሚደረገው የትግል ሂደት በትብብር መስራት አለብን በሚል ውይይት ጀምረናል።
ወደፊት በሚኖረው የትግል ሂደት በትብብር፣ በጥምረት ብሎም በውህደት ለመስራት በውይይት ላይ የምንገኘው ድርጅቶች፡-
1. የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
2. የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ
3. የቤንሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ
4. የአማራ ዴሞክራሲ ሃይል ንቅናቄ
5. አረበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ
ስንሆን ከሁሉም አስቀድመን አገራችንና ሕዝባችን ማዳን ግባችን አድርገን እንስራ በሚል መርህ በማንኛውም መንገድ አብረን መስራት አለብን ወደ ፊት ምንም አይነት ልዩነት ይኖረናል ብለን ባናምንም በሂደት ወደ አንድ የምንመጣበትን ሁኔታ እያመቻቸን አሁን ግን አገርና ሕዝብን የማዳኑን ስራ እንጀምር በሚል ውይይት እያደረግን መሆናችንን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መግለፅ እንወዳለን።
አምባገነኑም የወያኔ ቡድን እንዳለፉት ምርጫዎች ሁሉ በቅርቡ የሚደረገውን የይስሙላ ምርጫ ለማድረግ ደፋ ቀና እያለ ሲሆን በተለያየ አገራት በእናትህ፣ በአባትህ፣ በወንድምህ፣ በእህትህ ላይ ላይ እየደረሰ ላለው ዘግናኝ ግፍ እንኳን ወቅቱን ጠብቆ ተቃውሞውን ያልገለፀ ኢትዮጵያዊ ባህሪ የለሌው እኩይ ሥርዓት በመቃወም ረገድ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገህ ቢሆንም በተደራጀ ሁኔታ እየታገልን ከምንገኘው ተቃዋሚ ድርጅቶች ጎን በመሰለለፍ አስፈላጊውን አስተዋጽዖ እንድታደርግ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
አንድነት ሃይል ነው!!!
30/08/2007 ዓ.ም

CategoryAmharic

Thursday, 14 May 2015

አይሲስን ስንቃወም ህወሓትን አለመርሳት!


  •  
  • May 13, 2015
def-thumbበአይሲስ በግፍ በታረዱብን ወገኖቻችን የተሰማን ሀዘንና ቁጭት ከፍተኛ ቢሆንም እንኳን ከአዕምሮዓችን መውጣት የሌለበት ሀቅ አለ። ይህ ሀቅ “ያስጠቃን፣ ያሳረደን ወያኔ ነው” ከሚለውም ያለፈ ነው። መረሳት የሌለበት ሀቅ፣ ከአይሲስ የከፋ ጨካኝ በአገራችን የመንግሥት ሥልጣን የተቆጣጠረ መሆኑ ነው።
የህወሓት ፋሽስት ጦር በበደኖ፣ በአዋሳ፣ በሀረር፣ በጋምቤላ፣ በጎንደር፣ በኦጋዴን፣ በአዲስ አበባ፣ በሸካና መዠንገር፤ እንዲሁም በሚታወቁም በማይታወቁም የማሰቃያ እስር ቤቶች አይሲስ እየፈፀመ ካለው የባሱ ወንጀሎች በወገኖቻችን ላይ ፈጽሟል፤ አሁንም እየፈፀመ ነው። ባሳለፍነው ሣምንት እንኳን በሁመራ ወገኖቻችን የራሳቸውን መቀበሪያ ጉድጓድ ቆፍረው በጅምላ ተገድለዋል። በአይሲስና በህወሓት መካከል ያለው ልዩነት አይሲስ ነውረኛና አረመኔዓዊ ተግባሩን በቪዲዮ እየቀረፀ ለዓለም ሲበትን ህወሓት ግን እነዚሁኑ ነውረኛና አረመኔዓዊ ተግባሮችን እየፈፀመ መረጃዎች አፍኖ መያዙ ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ግን ህወሓት ሰዎችን ከነሕይወታቸው ጉድጓድ ውስጥ የቀበረ አረመኔ፣ እኩይ ድርጅት ነው።
ስለሆነም ለዓለም ሰላም ስጋት የሆነውን አይሲስን ስንቃወም የራሳችንን አይሲስ – ህወሓትን – አለመርሳት እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ ህወሓት፣ የአይሲስን እኩይ ተግባራት ከኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር እና ከዲሞክራሲያዊያዊ ፓለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ጋር ለማገናኘት እያደረገ ያለው ጥረት ምን ያህል አደገኛ ተግባር እንደሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲረዳው ያስፈልጋል። ዓይን አውጣ ሌባ ንፁሁን ሰው “ሌባ” እንደሚለው ሁሉ የኛው አይሲስ ራሱን ንፁህ አስመስሎ ሌሎችን “አይሲስ” ማለቱ ሊነቃበት ይገባል።
ሌላው ተያያዥ ጉዳይ ደግሞ ስለስደተኝነት የሚሰጠው ገለፃ ነው። ህወሓት ለስደተኝነት ምክንያቱ ደላሎች እንደሆኑ ይናገራል። ይህ የጉዳዩን ግንድ ትቶ ቅርንጫፎች ላይ ማትኮር ነው። ህገወጥ ደላሎች ራሳቸው ሊኖሩ የቻሉት ገንዘብ ከፍለውና የሕይወት ሪስክ ወስደው ለመሰደድ የሚፈልጉ ዜጎች በመኖራቸው ነው። ችግሩን በቅንነት ለመመርመር የሚፈልግ “ይህን ያህል ሰው የሕይወት ሪስክ እየወሰደ ከአገር ለመሰደድ ምን አነሳሳው?” ብሎ መጠየቅ እና ምላሽ ማግኘት ይኖርበታል። በሀገር ውስጥ በነፃነት ተረጋግቶ መኖር፣ ሠርቶ የማደግ ተስፋ ቢኖር ኖሮ ይኸን ያህል ሰው የአደጋውን ከፍተኛነት እያየ ለመሰደድ ይነሳሳ ነበርን? ኢትዮጵያዊው ከስደት ሊያገኝ የሚሻው ምንድነው? እንደ ወያኔ ካድሬዎች ገለፃ ከሆነ ከስደት ሊያገኝ የሚችለው አገሩ ውስጥ እያለለት ነው ኢትዮጵያዊ የሚሰደደው። ይህ ምን ዓይነት አመክኖ ነው? ከዚህ የባሰው ደግሞ ስደትንም የእድገት ውጤት አድርጎ የማቅረብ በሽታ ነው። ይህ እውነት ከሆነ፤ ህወሓት ለኢትዮጵያ አመጣሁላት የሚለው እድገት ውጤት ረሀብ፣ ስደት፣ መርዶ፣ እስር፣ ስቃይ፣ ሞት ከሆነ እንዴት “እድገት” ብለን እንጠራዋለን። ለስደተኝነት መብዛት ህገወጥ ደላሎችን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ፤ “እኔ ከደሙ ንፁህ ነኝ” የማለት ያህል ነው። በህጋዊዎቹም በህገወጦቹም ደላሎች ውስጥ የወያኔ ሰዎች በቀጥታም በተዘዋዋሪም እንዳሉበት መረጃዎች ያመለክታሉ። ገንዘብ ባላበት ሁሉ የወያኔ እጅ መኖሩ ፀሐይ የሞቀው ሀቅ ነው። የሰዎች ዝውውር የህወሓት አንዱ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ መሆኑ የማይታበል፤ በቀላሉ ማረጋገጥ የሚቻል ሀቅ ነው።
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ በዓለም አቀፉ አይሲስ አረመኔያዊ ተግባሮች በደረሰብን የመጠቃት ስሜት ተውጠን የራሳችንን አይሲስ – አረመኔውን ህወሓት – እንዳንረሳ ያሳስባል። መቆሚያው ለማይታየው የዜጎቻችን መሰደድ መንስኤዎች የነፃነት እጦት እና የኑሮ እድሎች መጥበብ መሆናቸው እንዳንዘነጋ ይጠይቃል። ንቅናቂያችን እነዚህ ተያያዥ ችግሮች ሁሉ የሚቃለሉት ህወሓትን አስወግደን በምትኩ ፍትህ፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፈኑባት ኢትዮጵያን ስንመሰረት ብቻ ነው ይላል። ለዚህም ደግሞ ሁላችንም በያለንበት የበኩላችንን ተሳትፎ ማድረግ ይገባናል። ሁለገብ ትግል ማለት፤ እያንዳንዱ ከሚመስለው ጋር እየተደራጀ በያለበት ወያኔ ማስጨነቅ፣ ማዋከብና ማዳከም፤ በመጨረሻም በጋራ ትግል ማስወገድ ማለት እንደሆነ ልብ እንበል። በሁለገብ ትግል ለውጥ የሚመጣው ሁሉም እንደ አቅሙ
በሚያደርገው ተሳትፎ በመሆኑ፣ የሚቻለንን በማድረግ የለውጥ ጠባቂ ሳንሆን፣ የለውጥ አምጭ አካል እንሁን ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
CategoryEditorial

Wednesday, 6 May 2015

የቁልቁለቱን ጉዞ እናስቁም፤ ውርደት ይብቃን!!!


  • May 6, 2015
def-thumbየህወሓት አገዛዝ ፋሽስታዊ ባህርያት እያደር መረን እያጣ፤ ነውረኛ እየሆነ መጥቷል። በአሳለፍነው ሣምንት ብቻ እንኳን አስነዋሪ ይዘት ያላቸው ሁለት ፋሽስታዊ ክስተቶችን አስተውለናል።
አንዱ በምርመራ ስም በታሳሪዎች ላይ የሚደረገው አሳፋሪ ሰቆቃ ነው። በገላቸው በሚያፌዙና በሚሳለቁ ተቃራኒ ፆታ መርማሪዎች ፊት ለሰዓታት ተመርማሪዎች ራቁታቸውን እንዲሆኑ የሚደረግበት እና እየተፌዘባቸው የሚደበደቡበት ሥርዓት መኖሩ የጉዳቱ ሰለባዎች ይፋ ሲያወጡ እፍረቱ ለመርማሪዎቹ ብቻ ሳይሆን ይህንን ጉድ ተሸክመን ለኖርነው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ነው። በተለይም ደግሞ እንዲህ ዓይነት ክብረነክ ሰቆቃ በሴቶች ላይ እየተፈፀመ መሆኑን ስንሰማ አገራዊ ውርደቱ ያሸማቅቀናል። እንዲህ ዓይነቶችን በሰው ስቃይና እፍረት የሚዝናኑ ጉዶችን ተሸክመን የምኖር መሆናችን ሁላችንን ያዋርደናል። ይህንን አስነዋሪ “የምርመራ ዘዴ” ያጋለጡት የዞን 9 ብሎገሮች፣ ጋዜጠኞችና ፓለቲከኞች ክብርና ሞገስ የሚገባቸው ጀግኖች ሲሆኑ የተዋረዱት እነሱ ሳይሆኑ እኛ ኢትዮጵያዊያን መሆናችን ሊሰማንና “ውርደት በቃ” ልንል ይገባናል።
ሁለተኛው አሳፋሪ ድርጊት ደግሞ ወገኖቻችንን በግፍ ባረደው አይሲስ በተሰኘው አሸባሪ ድርጅት ላይ የህወሓት አገዛዝ የተለሳለሰ አቋም ወስዷል ብለው ራሱ ህወሓት በጠራው ሰልፍ ላይ ተቃውሞዓቸውን ባሰሙ ወጣቶች ላይ አገዛዙ የወሰደው የኃይል እርምጃና ከዚያም ወዲህ እየተደረገ ያለው ነገር ነው። አገዛዙ ለፕሮፖጋንዳው ይጠቅመኛል ብሎ በጠራው ሰልፍ ወጥተው ተቃውሞዓቸውን የገለፁ ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድበዋል፤ በጅምላ ወደ እስር ቤቶች ተግዘዋል። የአገዛዙ ካድሬዎች ወገኖቻችንን የፈጀውን አይሲስን በመቃወም ፋንታ የራሱ የህወሓትን ውል አልባ ህግ አክብረው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉትን ሰማያዊ ፓርቲ፣ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን እና አረና ፓርቲን እየወነጀሉ መሆኑ አጅግ አሳፋሪ ነገር ነው። የአይሲስን አረመኔአዊ ድርጊት ከኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር ለማገናኘት በህወሓት የደህንነት ቢሮ አማካይነት እንቅስቃሴ መጀመሩ እየተሰማ ነው። ለወጣቱ በብዛት መሰደድ በምክንያትነት የሚያቀርቡት ደላሎችን መሆኑ አላዋቂነት ሳይሆን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቅራኔው በኢትዮጵያዊያን መካከል እርስ በርስ እንዲሆን ያለመ መሠሪነት ነው። ከዚህም አልፎ የትግራይ ወጣቶችን ነጥሎ በመሰብሰብ “ትምክህተኞች ሊበሉህ ነውና ታጥቀህ ሳይቀድሙህ ቅደም” እያሉ መቀስቀስ በመንግሥት ደረጃ የእርስ በርስ እልቂትን ከማደራጀት ተለይቶ አይታይም። የሥርዓቱ ይሉኝታ ቢስነት የደረሰበት ዝቅጠት ገላጭ ከሆኑ ነገሮች አንዱ “እስከምርጫ መጨረሻ ድረስ ልጆቻችሁን አስረን እናቆይላችሁ” እያሉ ወላጆችን እስከመጠየቅ መድፈራቸው ነው።
ከላይ በአጭሩ የተዘረዘሩት ኩነቶች የሚያረጋግጡት ህወሓት የተማከለ አመራር አጥተው መንገድ የጠፋቸው፤ ሆኖም ግን እጃቸው ውስጥ የገባው ስልጣንና ሀብት ላለማጣት ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱ አውሬዎች ስብስብ መሆኑ ነው። እንዲህ ዓይነቱን የአውሬዎች ስብስብ የሚገዛው የህግም ሆነ የሥነ-ምግባር ገደብ የለም። ህወሓት እስር በርሳችንን አባልቶ አገራችንንና ሕዝቧን ወደ ማንወጣው አዘቅት ከመክተቱ በፊት ራሱ ህወሓትን ማስወገድ እና በምትኩት ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን መገንባት የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው። ይህ ካላደረግን አሁን በወህኒ ቤቶች የሚደረገው ዜጎችን ልብስን አስወልቆ የማዋረድ አስነዋሪ ተግባር ነገ በአደባባዮች የማይደረግ ስለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ የለንም። ይህ ትውልድ ኃላፊነቱ ካልተወጣ ህግን አክብረው ከአገዛዙ የተለየ ሀሳብ እናራምዳለን የሚሉ ወገኖቻችን በሙሉ አደጋ ውስጥ ናቸው። በህወሓት መሠሪ ተግባራት ሳቢያ በክርስትናና እስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን መካከል ያለው መግባባት እንዲሻክር እየተደረገ ነው። ዜጎችን በማዋረድ የሚደሰት አገዛዝና ለመዋረድ የፈቀደ ሕዝብ እስካለ ድረስ የቁልቁለቱ ጉዞ መጨረሻ የለውም። ይህንን ማስቆም ያለብን እኛ ሁላንችንም ነን። በአደባባይ መደራጀት ሲከለከል በምስጢር መደራጀትን መልመድ የኛ ኃላፊነት ነው። የኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ በዓልን ስናከብር ከቀደምቶቻችን ልንወርስ ከሚገቡን እሴቶች አንዱ ለክብራችን ዋጋ መክፈል ያለብን መሆኑን ጭምር ነው። የኢትዮጵያዊያን ክብር በወያኔ ሲዋረድ እያየን ዝምታን ከመረጥን ከዚህም የባሰ እንዲመጣ መፍቀዳችንን እንወቀው።
አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የዜጎችና የአገር ውርደት ይብቃ! በተባበረ ክንድ ህወሓት ይወገድ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመመሥረት መሠረት እንጣል፤ ይህንን ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት በኅብረት እንነሳ ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
CategoryEditorial

Monday, 4 May 2015

State Dept. on Anniversary of Arrest of Ethiopia’s Journalists


April 28, 2015
24 April 2015
U.S. DEPARTMENT OF STATE
Office of the Spokesperson
Washington, D.C.
April 24, 2015
STATEMENT BY MARIE HARF, ACTING SPOKESPERSON
Anniversary of the Arrest of Ethiopia’s Zone 9 Bloggers and Three Journalists
Tomorrow, April 25, marks one year since Ethiopia arrested six Zone 9 bloggers and three other journalists. These nine individuals—Befekadu Hailu, Zelalem Kibret, Atnaf Berhane, Natnael http://ecadforum.com/wp-content/uploads/2015/04/US-on-Ethiopian-bloggers-300x152.jpg?296439Feleke, Mahlet Fantahun, Abel Wabella, Asmamaw Hailegiorgis, Edom Kassaye, and Tesfalem Waldeyes—joined 10 other journalists already imprisoned in Ethiopia, bringing the total number of jailed journalists in Ethiopia to 19, including two Eritrean nationals. This is more than any other country in Africa. In July 2014, Ethiopian authorities charged the six bloggers and three journalists with terrorism under its Anti-Terrorism Proclamation. Their trial is ongoing. Ethiopia also charged one other Zone 9 blogger—Soliyana Shimelis—who was out of the country when her colleagues were arrested, with terrorism, in absentia. Soliyana has been unable to return to Ethiopia and, along with dozens of other Ethiopian journalists, now lives in exile.
Restrictions on press freedoms are inconsistent with the rights outlined in the Ethiopian constitution. Space for media, civil society organizations, and independent voices and views are crucial for democratic progress, development, and economic growth. While we recognize a judicial process is underway, we urge the Ethiopian Government to release journalists and other individuals imprisoned for exercising their right to freedom of expression, particularly those imprisoned who may merit humanitarian release on medical grounds. We urge Ethiopia to refrain from using its Anti-Terrorism Proclamation as a mechanism to curb the free exchange of ideas.
CategoryHuman Rights ...

Sunday, 3 May 2015

The United States’ irresponsible praise of Ethiopia’s regime – The Washington Post


May 1, 2015
Hailemariam Desalegn, Prime Minister of Ethiopia, speaks during the opening ceremony for the groundbreaking of the Ethiopia-China Dong Guan Huajian International Light Industrial Zone outside of Addis Ababa on April 16, 2015. (Zacharias Abubeker/AFP/Getty Images)
 By Editorial Board April 30 2015
ETHIOPIA’S ELECTIONS, scheduled for May 24, are shaping up to be anything but democratic. A country that has often been held up as a poster child for development has been stifling civic freedoms and systematically cracking down on independent journalism for several years.
It was consequently startling to hear the State Department’s undersecretary of state for political affairs, Wendy Sherman, declare during a visit to Addis Ababa on April 16 that “Ethiopia is a democracy that is moving forward in an election that we expect to be free, fair and credible.” The ensuing backlash from Ethiopians and human rights advocates was deserved.
Ms. Sherman’s lavish praise was particularly unjustified given Ethiopia’s record on press freedom: It has imprisoned 19 journalists, more than any other country in Africa. According to a new report by the Committee to Protect Journalists, the country ranks fourth on its list of the top 10 most censored countries in the world. At least 16 journalists have been forced into exile, and a number of independent publications have shut down due to official pressure.
Last weekend marked one year since six bloggers were arrested and jailed without trial. The “Zone 9” bloggers, who used their online platforms to write about human rights and social justice and to agitate for a democracy in Ethi­o­pia, were charged with terrorism under the Anti-Terrorism Proclamation, which has been used to clamp down on numerous journalists critical of the regime. Today, the bloggers remain imprisoned, awaiting what will likely be a trial by farce.
As for the elections, opposition parties say the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front , led by Hailemariam Desalegn, has undermined their efforts to register candidates for the May vote. Since last year, members of opposition parties and their supporters have been arrested and harassed. In March, the sole opposition leader in Parliament said he would not run for reelection due to state interference with his party’s affairs. The EPRDF, which has been in power since 1991, was reported to have won the last elections in 2010 with 99.6 percent of the vote.
The State Department released a statement last week urging Ethiopia to release journalists who have been imprisoned for doing their jobs. But as the considerably more high-profile statement by Ms. Sherman indicated, the Obama administration has been reluctant to criticize what it regards as a key security ally in the Horn of Africa. A State Department spokeswoman confirmed this week that Ms. Sherman’s comments “fully reflect the U.S. government’s positions on these issues.”
With its ancient culture, strategic location and population of 94 million, Ethi­o­pia is indeed key to the future of eastern Africa. But that does not justify make-believe statements or a go-softly approach that is not working. The United States should stop funneling millions of aid dollars to a regime that has continued to choke off the media, hamper the participation of opposition parties and silence its critics. If the election is not judged by independent observers to live up to Ms. Sherman’s billing, the administration should swallow her words — and change its approach.

CategoryHuman Rights ...