Tuesday, 14 February 2017

የህወሓት ተላላኪ ሆኖ በርካታ በደሎችን በህዝብ ላይ ሲፈፅም የነበረው ደረጄ መከታው የተባለው ግለሰብ በአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች እርምጃ የተወሰደበት መሆኑ ታወቀ፡



January 12, 2017
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
የህወሓት ተላላኪ ሆኖ በርካታ በደሎችን በህዝብ ላይ ሲፈፅም የነበረው ደረጄ መከታው የተባለው ግለሰብ በአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች እርምጃ የተወሰደበት መሆኑ ታወቀ፡፡
ሰሞኑን በአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች የተገደለው ደረጄ መከታው የተባለው ግለሰብ ከዚህ በፊት የቀድሞው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አባል የነበረና በድርጅቱም ግዳጅ በመላክ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄድ አብሮት ሲሄድ የነበረውን የትግል ጓዱንና ድርጅቱን በመካድ የጠላት ተባባሪ በመሆን በታጠቀው የድርጅቱ መሳሪያ ጓዱን በመግደል ለወያኔ ስርዓት እጁን በመስጠት ተቀላቅሏል፡፡ ከአገዛዙ ተቀላቅሎ በመኖር ላይ እያለም ከአንድ የስርዓቱ አገልጋይ ጓደኛው ጋር በመሆን የትጥቅ ትግሉን ይደግፋሉ እንዲሁም በገዢው ቡድን ላይ ህዝብን ያሳምፃሉ ብለው የሚፈርጇቸውን ሰዎች እንዲሰልሉ በአገዛዙ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበረ ቢሆንም ከእለታ አንድ ቀን ሰው በመግደል ታስረው የቆዩ ሲሆን ባልታወቀ ምክንያትም ብዙም ሳይቆዩ ከእስራት ተፈተዋል፡፡ ይኸው ደረጄ መከታው የተባለው ግለሰብ ከእስራት ከተለቀቀ በኋላም ከወያኔ ደህንነት ጋር በመሆን በአሳቻ ሰዓትና በማታ ንፁሃን ዜጎችን በማደን ሲያሳስርና ሲያስደበድብ በተጨማሪም ሲያስገድል መቆየቱን የአካባቢው ህዝብ የአይን ምስክሮች ናቸው ፡፡
በመሆኑም ይህን የህዝብ ሰቆቃ ሰምቶ መታገስ ህሊናቸው ያልፈቀደላቸው በአርበኞች ግንት 7 ስር በሃገር ቤት የሚንቀሳቀሱ የውስጥ አርበኞች በዚሁ ደረጄ መከታው በተባለው ግለሰብ ህዝብ የሚደርስበትን በደልና ይኸው ግለሰብ ለወያኔ መላላክን ምርጫው ያደረገ በንፁሃን ዜጋ ሞት የሚደሰት መሆኑን በመመልከታቸው የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች ተከታትለው ሊገድሉት ችለዋል ፡፡
አሁንም በዚህ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ከህዝብ ጎን መቆም ሲገባቸው ለጥቅም ያደሩ ግለሰቦች መለስ ብለው መሳሳታቸውን አምነው ከህዝብ ጎን ካልተሰለፉና የህዝቡን ትግል ካልደገፉ ወይም ከቀደመው እኩይ ተግባራቸው ተቆጥበው ማሳሰራቸውንና ማስደብደባቸውን እስካላቆሙ ድረስ በሰላም መኖር እንደማይችሉና የእነርሱም እጣ ፈንታ እንደ ደረጄ መከታው እንደሚሆን የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች ከሃገር ቤት ባደረሱን መረጃ አስታውቀዋል ፡፡

No comments:

Post a Comment