Sunday, 27 July 2014

ነጭ ማር ለአገርህ

 
 



በተለሳለሰው በአውሮፓ ጎዳና
የልጅ ፍቅርን መጦ
ወግ ትዳርን መልኩን ሳያጣጥም ገና።
የስቃይ ድምፅ ጠርቶ አላስተኛም ብሎት
ለነፃነት ፍትህ ዋጋን ሰጥቶ ሰርፆት።
መኖር እየቻለ ግድ የለኝም ብሎ
በዱር ቤቴ አላማ ድጉን ተጠቅልሎ
በረሀን ንዳድን ወዳጆቸ ብሎ
እየቀለጠ እሱ ለእኛ ላብራ ብሎ።
የረጋውን ጎበዝ እናት የወለደች
ደረቱን ለአረር ለፍትህ ያረገች።
ጅንጉርጉሩን ፍጡር አንድ ላድርግ ባለ
አገር አንድ ትሁን ዘረኝነት መድሎ ይረገጡ ባለ
ፍትህ ይንገስልን ይደላደል ባለ
ጥንተ ታሪካችን አይደምሰስ ባለ
ድምፃችን ይሰማ የጅምላ ርሸና ይቅር ይብቃ ባለ
ወገን በወገኑ ቃታን አይሳብ ባለ
ይነበብ የፃፍነው ክብር ለህዝብ ባለ
አልሰማ አይል ጆሮ
አንድአርጋቸው ፅጌ ዘብጥያ ተጣለ?
ታሪክ ይዘክረው በወርቅ ቀለሙ
ውሻ የማይልሰው የነፃነት መብራት ክብር ይሁን ደሙ።
ነጭ ላብህ ይውለድ ነጭ ማር ለአገርህ
ሁለተኛው ጴጥሮስ አንዳርጋቸው ፅጌ እኛም አለንልህ።
ክንድህ ረጅም ነው አንተ የኔ ጀግና
በፍቅር የወለድከው ደጀንህ አለና።
ጀግናው የፅጌ ልጅ አንዳርጋቸው ደማ
ለአንተ አለም ቢጠብህ
ቀን ቢጨልምብህ
አናጎነበሰም የተከልከው አርማ።
 
ከዳዊት አበበ
 
 










 




 







Thursday, 24 July 2014

Ye chelema guzo



የአለማችን ሀያል አሜሪካ በአገራችን በኢትዮዽያ በአንድ ወገን በኩል አየሮቿ በረራ እንዳያደርጉ አጥብቃ ከለከለች ተባለ

ወዳጅ ሲያረጅ!

ምን ሸተታት ይሆን?


አሸባሪው የወያኔ መንግስት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የወያኔ ሰራዊትና ከባድ መሳሪያ በደረቀ ለሊት ወደ ሰሜኑ አገራችን ክፍል እያጓዘ ነው
ኧረ ጎበዝ ከጨለማ ጉዞ ያውጣን በሉ!

በአስረአንድ ሰአት ወደ ጨለማ? ኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪ