Sunday, 27 July 2014

ነጭ ማር ለአገርህ

 
 



በተለሳለሰው በአውሮፓ ጎዳና
የልጅ ፍቅርን መጦ
ወግ ትዳርን መልኩን ሳያጣጥም ገና
የስቃይ ድምፅ ጠርቶ አላስተኛም ብሎት
ለነፃነት ፍትህ ዋጋን ሰጥቶ ሰርፆት
መኖር እየቻለ ግድ የለኝም ብሎ
በዱር ቤቴ አላማ ድጉን ተጠቅልሎ
በረሀን ንዳድን ወዳጆቸ ብሎ
እየቀለጠ እሱ ለእኛ ላብራ ብሎ
የረጋውን ጎበዝ እናት የወለደች
ደረቱን ለአረር ለፍትህ ያረገች
ጅንጉርጉሩን ፍጡር አንድ ላድርግ ባለ
አገር አንድ ትሁን ዘረኝነት መድሎ ይረገጡ ባለ
ፍትህ ይንገስልን ይደላደል ባለ
ጥንተ ታሪካችን አይደምሰስ ባለ
ድምፃችን ይሰማ የጅምላ ርሸና ይቅር ይብቃ ባለ
ወገን በወገኑ ቃታን አይሳብ ባለ
ይነበብ የፃፍነው ክብር ለህዝብ ባለ
አልሰማ አይል ጆሮ
አንድአርጋቸው ፅጌ ዘብጥያ ተጣለ?
ታሪክ ይዘክረው በወርቅ ቀለሙ
ውሻ የማይልሰው የነፃነት መብራት ክብር ይሁን ደሙ
ነጭ ላብህ ይውለድ ነጭ ማር ለአገርህ
ሁለተኛው ጴጥሮስ አንዳርጋቸው ፅጌ እኛም አለንልህ
ክንድህ ረጅም ነው አንተ የኔ ጀግና
በፍቅር የወለድከው ደጀንህ አለና
ጀግናው የፅጌ ልጅ አንዳርጋቸው ደማ
ለአንተ አለም ቢጠብህ
ቀን ቢጨልምብህ
አናጎነበሰም የተከልከው አርማ
 
ከዳዊት አበበ
 
 










 




 







No comments:

Post a Comment