Friday, 1 August 2014

ተጠንቀቅ ቢል ጌትስ!





  ተጠንቀቅ ቢል ጌትስ!
በጎነትህ ጥሩ ለእድገት መነሳትህ
ረሀብ ድንቁርና ችግርን መምታትህ
ብድር ይግባህና እኛን መመልከትህ።
መስመርክን ጠብቀህ ማጣት ልትገፋ
መርፌህ ችግር እንጅ ሌላን ላትሰፋ።
ቢል ጌትስ ተጠንቅቀ!
አትሁን የጥገት ላም ለመዥገር ወያኔ
በንዋይ ደንዝዞ እርምን እየበላ ላጠገበን ጠኔ።
የተካኑበት ነው ጥንብ እንዳየ አሞራ
በአንቱ ሸልመውት ለመጣል ከአቧራ።
በመሀይም መላ አገር እየመሩ
በእሾህ አሜከላ ትውልድን ያጠሩ።
ጠንቀቅ በል ቢል ጌትስ ከአንተ አላውቅምና
ለቸገረው ድረስ ምስጢር እወቅና።
ከመዥገር ወያኔ ፅንሰ ክፉ ስራ
ስርአተ አልበኛ ትፍግፍግ ያልጠራ
ዘር ማጥፋት በጅምላ ወላድን ለአሞራ
ለሀቅ ሸምቀቆ ፍቅርን ለደንቃራ።
ካረገልህ ክብር ካለበሰህ ካባ
ቢል ጌትስ ተጠንቀቅ አለ ብዙ ድብቅ ከሚታየው ጀርባ።
ሲረባረብ ጉንዳን ከተጣለው አጥንት
አየበት ይተባል የቀጣፊ ትምህርት
ካንተ አላውቅምና ተጠንቀቅ ቢል ጌትስ።
የሀቅ ሸምቀቆ ያሰት አባት ናቸው
መዘባረቅ ታሪክ መቶ አመት ድካቸው
የእናት ጡት ነካሾች አስብቶ አራጅ ናቸው
በወገን ደም ዋጋ የጠገቡ ናቸው
ተጠንቀቅ ቢል ጌትስ ቅንቅን ተባይ ናቸው።
 
ከዳዊት አበበ

 


No comments:

Post a Comment