Tuesday, 27 January 2015

ኢትዮጵያ የማን ነች?


“ኢትዮጵያ የማን አገር ነች” የሚል ጥያቄ ከዚህም ከዚያም እየተሰማ ነው። ህወሃቶች ከፈጠሯቸው ቀውሶች መካከል አንዱ ይሄው ነው። ዜጎች የአገር አልባነት ስሜት ውስጥ ገብተው የገዛ አገራቸውን “የማን ነች” ብለው እንዲጠይቁ መገደዳቸው።
ለኢትዮጵያዊያኑ ኢትዮጵያ አገራቸው እየሆነችላቸው አይደለም። ኢትዮጵያዊ መሆን ወንጀል እስኪመስል ድረስ በዜጎች ላይ ግፍ እየተፈፀመ ነው። የሚፈፀመው የግፍ ዓይነት ወሰን የለውም። ግማሹ በጠራራ ፀሃይ ደሙ እንዲፈስ ይደረጋል። ሌላው ለቁም ስቃይ ወደ ወይኒ ይጋዛል። ቀሪውም እትብቱ የተቀበረበትን አገር ትቶ ለመሰደድ ይገደዳል። በአገሪቷ ውስጥ የሚፈፀመውን ወሰን አልባ በደል የተመለከቱ ኢትዮጵያን ከውዳቂ መንግስታት ተራ መድበዋታል። በኢትዮጵያችን የዜጎችን መብት አስከብሮ ለመምራት ብቃት ያለው መንግስት ባለመኖሩ እጣ ፈንታችን እንዲህ ከውዳቂ አገራት ተርታ መግባት ሁኗል።
ኢትዮጵያን ለመምራት ብቃት ያለው መንግስት ቢኖር ኑሮ ለረዥም ዘመን በሰላም ተጎራብተው ይኖሩ በነበሩ ህዝቦች መካከል ግጭት ተፈጠረ መባልን ባልሰማን ነበር።ህወሃት አገሪቷን ከተቆጣጠረ ዘመን ጀምሮ ሆን ተብሎ በሚፈጠር ግጭት ብዙ ደም ፈሷል። አማራው ከኦሮሞው፤ ትግሬው ከአማራው እና ከአፋሩ፤ ሶማሌው ከኦሮሞ፤ኦሮሞው ከጉጂው፤ ኑዌር ከአኙዋክ፤ ዲዚ ከሱርማ፤ ሌሎችም ብዙ ግጭቶች በየቀየው ተፈጥረው አይተናል። የብዙ ዜጎችም ህይወት ተቀጥፏል። ይሄ ሁሉ ደም መፋሰስ የሚከሰተው ህወሃት ከህዝብ ፈቃድ ያልሆነ እና ከህዝቡ የተለየ በመሆኑ ነው።
ህወሃቶች ከህዝብ የተለዩ ብቻ ሳይሆኑ የህዝብ ጠላት መሆንን የመረጡ ብድኖች ስለመሆናቸው ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። ህወሃቶች “አማራና ተፈጥሮ” የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ናቸው ብለው መፃፋቸው እና ማስተማራቸው የህዝብ ጠላት መሆንን ስለመምረጣቸው ቋሚ ምስክር ነው። ህወሃቶች በስልጣን የሚያቆየን በህዝቦች መካከል የሚፈጠረው አለመተማመንና የጠላትነት ስሜት ብቻ ነው ብለው ከልባቸው ያምናሉ። በህዝቦች መካከል የሚፈጠረው አብሮነት፤ አብሮነቱን ለማዘመን የሚረዳ መተማመን፤ ይሄም የሚወልደው አንድነትና ህብረት በህወሃት ዘንድ የሚወደድ ነገር አይደለም። በህወሃት ዘንድ የሚወደደው በህዝብ መካከል የሚፈጠረው የአለመተማመን ስሜት ይህም አለመተማመን የሚወልደው ግጭት ነው። ግጭት ተፈጥሮ የንፁህ ደም ሲፈስ በህወሃቶች መንደር ደስታ ይሆናል።በዜጎቹ ግጭት እና ደም መፋሰስ ተደስቶ የሚኖር ቡድን እንደ ህወሃት ዓይነት በየትም አገር ታይቶ አይታወቅም።
ከሰሞኑ በአማራ ክልል ነዋሪዎችና በትግራይ ክልል ነዋሪዎች መካከል ግጭት ተከሰተ መባልን ሰምተናል። ይሄ በጣም አሳፋሪና አሳዛኝ ነገር ነው። ህወሃት ከመፈጠሩ በፊት በሠላም ተጎራብቶ የሚኖር ህዝብ ዛሬ ደም መፋሰስ ደረጃ ወደ ሚያደርሰው ግጭት ተሻግሮ መስማታችን አሳፋሪ ነው። ህወሃቶች ከመቸውም ግዜ በላይ የኢትዮጵያ አንድነት ተጠናክሯል እያሉ ሳይታክቱ በሚያወሩበት በዚህ ግዜ አብሮ ለብዙ ዘመን የኖር ህዝብ ወደ ግጭት የመግባቱ ነገር የህወሃቶች ትሩፋት ሁኖ እናገኘዋለን። ህወሃቶች በዘመናቸው ካተረፉልን ቀውሶች መካከል ሳይጠቀስ የማይታለፈው በህዝቦች መካከል የሚፈጥሩት ግጭት ነው። በህዝቦች መካከል በሚፈጠረው ግጭት ብቻ እድሜያችን ይረዝማል ብለው ማመናቸው ህወሃቶች የገበቡት የክፋት አዘቀት ምን ያክል ጥልቅ እንደሆነ ያሰየናል።
ጥላቻ ለህወሃቶች የመኖሪያቸው ድንኳን ሁኖ አቆይቷቸዋል። ከእነርሱ ያልሆኑት በሙሉ ከጠላትነት በታች ስፍራ የላቸውም። ሁሉንም ጠላት አድርጎ ማየት ደግሞ ከፍርሃት እና በራስ ላይ ዕምነት ከማጣት የሚመነጭ መሆኑ ይታወቃል። አሁን አሁን እነዚህ ቡድኖች ፍራቻቸው ፈሩን ለቆ የራሳቸውን ጥላ የመፍራት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። የራሱን ጥላ መፍራት የጀመረ ቡድን ራዕይ ኖሮት በሰከነ መንፈስ አገርን የመሰለ ትልቅ ነገር ለመምራት ብቃት አይኖረውም። ህወሃቶች አስቀድሞ በነበርው የአቅም ማነስ ተግዳሮታቸው ላይ ፍርሃት ታክሎበት አገሪቷን ወደ ከፋ ሁኔታ ሊወስዷት እየሞከሩ ነው።
ለህወሃቶች አገር ማጥፋት ጀግንነት ሁኖ እንደሚቆጠር ድርሳናቶቻቸው ይመሰክራሉ። ለምስሌ “እኛ ከሌለን አገሪቷን እንበትናታለን” የሚለው ሟርት በእያንዳንዱ የጥፋት ቡድኑ አባል ልብ ውስጥ የተፃፈ ሃሳብ ነው። ከዚህ በላይ አገር የሚያጠፋ ሃሳብ የለም።” እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” የሚሉ ቡድኖች በአገሪቷ ጫንቃ ላይ ተቀምጠው ስለ ሰላምና እድገት ማውራት ፈፅሞ አይቻልም። ሠላም ማለት የጦርነት አለመኖር ማለት አይደለም፤ ልማትም ሰማይ ጠቀስ ፎቆችን ማቆም ማለት አይደለም። ሠላምም ሆነ ልማት ህወሃቶች ከሚያወሩት የተለየ የአስተሳሰብ ደርዝ ያለው ትልቅ ፅንሰ ሃሳብ ነው። ህወሃቶች ይህን ትልቅ ትርጉም ያለውን ቁም ነገር ለመረዳት አዕምሮአቸው የተከፈተ አይደለም። በክፉ አስተሳሰባቸው ተተብትበተው፤ ከቂምና በቀል ራሳቸውን መለየት አቅቷቸው ራሳቸው ለራሳቸው የገነቧቸውን ህንፃዎች እየቆጠሩ ኢትዮጵያ በልማት እየገሰገሰች ነች ይሉናል። ዕለት ዕለት የንፁህ ሰው ደም እያፈሰሱ ከመቸውም ግዜ በላይ ሠላማችን ተጠብቋል ሲሉም ፈፅሞ አያፍሩም። ይህን ወሬያቸውን እውነት ነው ብለን እንድንቀበል የሚያደርገን አንዳችም እውነት የለም። ህወሃቶች የሃሰት ልጆች በመሆናቸው መዋሸት በእነርሱ ዘንድ የፖለቲካ ጥበብ ነውና በትልቁም በትንሹም ይዋሻሉ።
ለእነዚህ የጥፋት ቡድኖች የልማትንና የሠላምን ምንነት ለማስተማር መሞከር በጭንጫ መሬት ላይ መልካም ዘርን እንደመዝራት ይሆንብናል።የህወሃቶች አዕምሮ በጎ ነገር የማይዘልቅበት ፍፁም ጭንጫ ሁኗል። እነዚህ ቡድኖች ከህዝቡ ሁሉ በላይ ጠቢብ የሆኑ ይመስላቸዋል። እንደ ፈጣሪ ቃል እነርሱ ያሉት ካልሆነ ህዝቡ ሁሉ ቢጠፋ ግድ እስከማይኖራቸው ድረስ በትዕቢት ታውረዋል። ትዕቢተኛ ቡድን አገርንና ህዝብን ያጠፋል እንጂ አያለማም። ደም መፋሰስን ያበዛል እንጂ ሠላምን አያመጣም።የህወሃቶች የስንፍናቸው ብዛት የወለደው ግጭት አብሮ በኖረው ወደፊትም አብሮ መኖር በሚችለው ህዝብ መካከል ደም እያፋሰሰ ነው።በቅርቡ በአማራ እና በትግራይ ክልል ድንበር አካባቢ ተነስቶ የሰው ህይወት ያለፈበትን ግጭት ምሳሌ አድርጎ ማቅረብ ይቻላል።
በአጠቃላይ ህወሃቶች በአገሪቷ ጫንቃ ላይ እስካሉ ድረስ ሠላምም ሆነ ልማት ተብሎ ሊጠራ የሚችል ነገር በኢትዮጵያችን አይኖርም። እነዚህን የጥፋት ልጆች ከቅዥታቸው ነቅተው ከሰው መሃል ሁነው እንደ ሰው ልጅ ያስባሉ ብሎ መጠበቅም ከንቱ ምኞት ነው። ለብዙ ዘመን ከዛሬ ነገ ከቅዥታቸው ነቅተው ሰው ይሆናሉ ብለን ስንመኝ ነበር። የቻሉትን ያክል ዘርፈው በቃኝ ይሉ ይሆናል የሚልም ተስፋ ነበረ። ምኞታችንና ተስፋችን ግን እንዲሁ በከንቱ ውሃ በልቶት ቀርቷል። በጎ ምኞታችንን የሚገዳደሩን ኃይሎች በወንበሩ ተቀምጠው ፈራጅ ሆነው ሳለ፤ ተስፋችንን በሚያመክኑ ቡድኖች እግር ተወርች ታስረን እያየን ዝም ብለን እንኖር ዘንድ ሰው መሆናችን ሊከለክለን ይገባል።አዎን ሰው መሆናችን ብቻ ህወሃቶች የሚፈፅሙትን እኩይ ተግባር ለማስቆም እንድንነሳ ያደርገናልና ሁላችንም አብረን ተነስተን በፍርድ ወንበር የተቀመጡ ክፉዎችን አደብ እናስገዛለን።
ህወሃቶች አገር አጥፊ ኃይሎች እንደሆኑ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሚስማማበት እውነት ሁኗል። ከዚህ እውነት ለጥቆ የሚያሳስበን ብርቱ ነገር በዚያች አገር እጅግ በጣም ብዙ አደር ባዮች የመፈጠራቸው ነገር ነው።”እኛ ምን እናድርግ ታዘን ነው እንዲህና እንዲያ የምናደርገው “የሚሉ የሂሊና ሙግት የሌለባቸው ዜጎች በዚያች አገር የመብዛታቸው ነገር አሳሳቢ ነው። ሰው ለቁሳቁስ፤ ለሚበላና ለሚጠጣ ኃላፊ ነገር ብሎ የወንድሙን ደም ማፍሰስ ሲጀምር ያን ግዜ አገር መፍረስ ትጀምራለች። በተለይም እንዲህ ዓይነቱ ነውር ድርጊት በህግ አስከባሪው አካል መፈፀም ሲጀምር አንድ አገር እንደ አገር የመቀጠሏ ሁኔታ አደጋ ላይ ይወድቃል። ዛሬ በኢትዮያችን የፍርድ ቤት ወንበሮች በምናምንቴዎች ተይዘዋል፤ የፍትህ መዶሻዎችም በጨካኞችና በሃሰተኛ ልጆች እጅ ወድቀዋል። አገርንና ህዝብን ለመጠበቅ የተሰለፉ ኃይሎች የህዝባቸውን ደም በከንቱ የሚያፈሱ ሁነዋል። የፖሊስ ኃይሉም የዘራፊዎችንና የነፍሰ ገዳዩን ቡድን የሚጠብቅ እንጂ የዜጎችን ሠላም የሚጠብቅ ሊሆን አልቻለም። እነዚህ ኃይሎች ከሂሊናቸው በላይ ለሥጋቸው እንዲገዙ የሚያደርጋቸው ምን እንደሆነ ባናውቅም አደር ባይነታቸው አገርንና ህዝብን በብርቱ እየጎዳ እንደሆነ መካድ አይቻልም።
ታዝዤ የገዛ ወገኔን ገደልኩ የሚል የመከላከያ ኃይል አባል፤ ታዝዤ በሃሰት ማስረጃ ክስ መሰረትኩ የሚል ፖሊስ እና አቃቤ ህግ ፤ታዝዤ በሃሰት ማስረጃ ፈረድኩ የሚል ዳኛ ነገ የሚያስጠይቅ ዘመን ሲመጣ ማምለጫ ምክንያት እንደማይኖረው ሊገነዘበው ይገባል። ታዞ ወንጀል መፈፀም ከወንጀሉ ነፃ አያደርግም። በተለይም በህግ አስከባሪውና አስፈፃሚው አካል ይህን መሰሉ ነውር ሲፈፀም ማየት ለኢትዮጵያችን ትልቅ ውድቀት መሆኑን እነዚሁ አካላት እንዲያውቁት ያስፈልጋል።ታዞ ደግሞ ደጋግሞ ወንጀል መፈፀም ከአደር ባይነት በላይ የሆነ ራሱን የቻለ ወንጀል ነው። በንፁሃን ላይ ወንጀል ሲፈፀም አይቶ እንዳላዩ መሆን፤ ሰምቶም እንዳልሰሙ መምሰል አደር ባይነት ሊባል ይችላል ታዞ የገዛ ወገንን መግደል ግን ወንጀል መሆኑን ማወቅ ይገባል። ኢትዮጵያችን ከገጠሟት ቀውሶች መካከል አንዱ ነፍሰ ገዳዮችን እያዩ ዝም የሚሉ አደር ባዮች የመበራከት ነገር ነው። ከትላልቅ የኃይማኖት መሪዎች አንስቶ እስከ ተራው ምዕመን ድረስ ያለው ኃይል በዚህ እርግማን የተያዘ እስኪመስል ድረስ በዝምታ ተውጧል።ይህ ዝምታ የሚሰበርበት ግዜ እሩቅ አለመሆኑን ስንናገር በህወሃቶች ዘንድ ድንጋጤ እንደሚሆን እናውቃለን። እናም ዝምታው ይሰበራል።ዜጎችም ለፍትህ፤ለእኩልነት እና ለነፃነት የሚያደርጉትን ትግል አፋፍመው ይቀጥላሉ። እስከ ህይወት መስዋዕትነት ድረስ ለመክፈል የተዘጋጁ ወጣቶች ሰይፋቸውን ከሰገባው መዘዋል።
ግንቦት ሰባት ንቅናቄም የጥፋት ኃይል መሆንን ምርጫቸው ያደረጉ ህወሃቶች የገነቡትን የጥፋት መረብ እንበጣጥሰዋለን። በወገኖች መካከል የሚፈጠረው ግጭት የመኖሪያቸው ድንኳን የሆናቸው የጥፋት ኃይሎችን አደብ ለማስገዛት የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል እየሰራን ነው። ህወሃቶች ሆይ በዜጎች ደም እየቀለዳችሁ አትቀጥሉም። በተገኘው አጋጣሚ በተገኛችሁበት አምባ ሁሉ እንታገላችኋለን። በሚገባችሁ ቋንቋም እናናግራችኋለን። ደግሞም እውነት ከእኛ ዘንድ ስላለ አለ ምንም ጥርጥር እናሸንፋችኋለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

United Nations Review Should Condemn Crackdown –Human Rights Watch


(Geneva) – United Nations member countries should call on Ethiopia to stop targeting activists and the media under draconian laws. The UN Human Rights Council will review Ethiopia’s human rights record under the Universal Periodic Review (UPR) procedure on May 6, 2014.
A Human Rights Watch submission to the UN on Ethiopia highlights its ongoing suppression of the media and nongovernmental organizations, and the lack of accountability for torture and other serious abuses by its security forces. The arbitrary arrest of nine bloggers and journalists on April 25 and 26, just 10 days before the review, reflects Ethiopia’s blatant disregard for fundamental rights and should be strongly condemned by UN members.
“The UN review is taking place just as Ethiopia is renewing its crackdown on free speech,” said Leslie Lefkow, deputy Africa director. “To make this review meaningful, UN member countries should forcefully tell Ethiopia that its attacks on the media and activist groups are a blight on its human rights record.”
Since Ethiopia’s first UPR review in 2009, the human rights situation has deteriorated substantially. The authorities have shown harsh intolerance of any criticism of government actions and have sharply restricted the rights to free expression and association.
Despite Ethiopia’s commitment during the 2009 review to take “measures to provide for free and independent media,” Ethiopia now has one of the most repressive media environments in the world. Numerous journalists languish in prison, independent media outlets have been closed down, and many journalists have fled the country.
Critics of government policy – including journalists, rights activists, and opposition party supporters – risk harassment, arbitrary detention, and politically motivated prosecutions. Many prosecutions are carried out under repressive laws that have dramatically curtailed the ability of independent Ethiopian and international organizations to investigate and report on human rights violations and other concerns.
Critics are also subject to illegal surveillance of telephone communications, and the contents of these communications are sometimes used during unlawful interrogations. Government censors routinely block websites of opposition parties, independent media sites, blogs, and several international media outlets.
During the 2009 review Ethiopia rejected recommendations to amend two draconian laws – the Charities and Societies Proclamation (CSO law) and the Anti-Terrorism Proclamation – to comply with international human rights standards.
“Ethiopia’s membership in the Human Rights Council should make it a leader in respecting rights, not repressing them,” Lefkow said. “UN members should press Ethiopia to amend the laws it uses to decimate independent media and civil society.”
The Ethiopian government has failed to conduct credible investigations or prosecutions of members of the security forces implicated in torture and other rights violations, war crimes, and crimes against humanity. This includes security force abuses in Gambella, the Somali regionOromia, and inSomalia.
In an October 2013 report, Human Rights Watch documented the use of torture by police and investigators against detainees in Maekelawi, the main investigation center in Addis Ababa, the capital.
At the Human Rights Council, countries should stress the need for Ethiopia to address torture and other serious crimes by security forces, and to investigate and prosecute security personnel responsible for serious crimes.
“Ethiopia’s refusal to address serious crimes by security forces is a major obstacle to human rights progress and deeply distressing for the families of the victims,” Lefkow said. “UN members need to push Ethiopia to meaningfully investigate grave violations and to hold those responsible to account.”

Monday, 19 January 2015

በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የግንቦት 7፣ ለፍትህ፣ ዴሞክራሲና የነጻነት፣ ንቅናቄ ፣መሀል የተደረገውን ውህደት በተመለከተ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፣



pg7-header.gif

ጥር 2 2007 ዓ.ም

በዛሬው ዕለት፣ ጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የግንቦት 7፣ ለፍትህ ለዴሞክራሲና የነጻነት፣ ንቅናቄ፣ ድርጅቶች፣ ተዋህደን “አርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ለዴሞክራሲ፣ ንቅናቄ” በሚባል ሥም መጠራት መጀመራችንን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስናበስር፣ እጅግ ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ባለፉት በርካታ አስርተ አመታት፣ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለነጻነት፣ መብትና አንድነት፣ ከፍተኛ ትግል ሲያካሂድ ቆይቷል። በአደረገውም ትግል እጅግ ከፍተኛ መስዕዋትነት ከፍሏል። ለከፈለው ከፍተኛ ዋጋ የሚመጥን ግን ምንም ዓይነት ውጤት አላገኘም። እንዲያውም ከጊዜ ወደ ጊዜ የመብት ረገጣው፣ አድሎው፣ ማስፈራራቱና ማዋከቡ ተጠናክረው መቀጠል ብቻ ሳይሆን፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ልትቀጥል የማያስችል ከፍተኛ የመበታተን አደጋ አንጃቦባት ትገኛለች ።
በሀገራችን ላይ ላንጃበበው ከፍተኛ የመበታተን አደጋ ምክንያት የሆነው በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ የአምባገነን ቡድን ነው። ይህ ዘረኛ አምባገነን ቡድን በሀገራችን ታሪክ በሥልጣን ላይ ከመጡ የገዥ ሃይሎች ጋር ሲወዳደር ሀገርን ለከፍተኛ አደጋ በማጋለጥ፣ ሕዝቧን በማወረድ፣ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ዕኩይ ሃይል መሆኑን በበርካታ ተግባራቶቹ ያለ ምንም ጥርጣሬ አረጋግጧል።
በሌላ በኩል ለቀድሞቹም ሆነ ለዛሬው ዘረኛው የወያኔ አምባገነን ገዥ በሕዝብና በሀገር ላይ በደል እየፈጸመ በሥልጣን መቆየት የቻለበት ምክንያት፣ በተቃዋሚነት የሕዝቡን ትግል ለመምራት የተንቀሳቀስን ድርጅቶች፣ የተቋቋምንበት ዓላማ መለያዬት ብቻ ሳይሆን፣ አንድ ዓይነት ዓላማ ያለንም ብንሆን፣ ከድርጅቶቻችን ጠባብ ፍላጎቶችና ስሜቶች ባለፈ፣ የሀገርና የሕዝብን ጉዳይ በማስቀደም በጋራ መሰባሰብና መታገል ስላቃተን ነው። በዚህም ድርጊታችን የራሳችንን ብቻ ሳይሆን የወገናችንንም የመከራ ዘመን እያራዘምን እንገኛለን ።
ይህ ሁኔታ በተለያዩ ተቃዋሚ ድርጅቶች መሀል ከፍተኛ ጥርጣሬና ፍርሀት ከመፍጠሩ የተነሳ በምንም ዓይነት ሁኔታ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶች በጋራ በሀገርና በሕዝብ ደረጃ ትርጉም ያለው ስራ መስራት አይችሉም፣ የሚለው አመለካከት የበላይነት እንዲያገኝ አድርጎታል።
በዛሬው ጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም ወደ ውህደት የመጣነው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የግንቦት 7፣ ለፍትህ፣፡ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ መዋሃድ መወሰናችንን፣ ስንገልጽ በተናጠል ከሚደረጉ በጋራ የሚደረጉ የትግል ጥረቶች ውጤታማ ይሆናሉ በሚል ብቻ ሳይሆን፣ የተቃዋሚ ድርጅቶች፣ በምንም ዓይነት ሁኔታ በሀገርና በሕዝብ ደረጃ ትርጉም ያለው ሥራ በጋራ መስራት አይቻሉም የሚለውን፣ አስከፊ ተመክሮና አመለካካት ለመስበርም ነው።
በእኛ እምነት ከትናናሽ ድርጅቶች ዙሪያ ከሚሽከረከሩ ሀሳቦችና ስሜቶች ለመውጣትና ሀገራዊና ሕዝባዊ የሆነው ጉዳይ ለማስቀደም የወሰነ ማንኛውም ድርጅት፣ አርበኞችና ግንቦት7፣ የደረሱበት የውህደት ውሳኔ ወይም በሌሎች በጋራ ሊያሰሩ በሚችሉ ስምምነቶች አብሮ ለመስራት መወሰን የማይችልበት ምንም ምክንያት አይታየንም። በወያኔ አድሎ ስርዓት የተንገፈገፈና ትግሉን ለመቀላቀል የቆረጠ ማንኛውም ዜጋ፣ የተገኘውን አጋጣሚ በመጠቀም ትግሉን መቀላቀል ይችላል፣ የኢትዮያ ሕዝብ በአንድነት የተነሳ ቀን ደግሞ፣ የወያኔ ግብዓተ መሬት ይፈጸማል፣ ብለን ከልብ እናምናለን።
ይህም በመሆኑ፣
ለተቃዋሚ ድርጅቶች፣
ዛሬ በአርበኞችና በግንቦት 7፣ የተጀመረው ጉዞ ውጤታማ በመሆን ሀገራዊና ታሪካዊ ትርጉም እንዲኖረው፣ ሌሎችም በተግባር የምትንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ድርጅቶች፣ ወያኔን የማስወገድንና ብሎም ሀገር የማረጋጋቱን ሀላፊነት በጋራ እንድንወጣ የሚያስችል መቀራረብ እንድናደርግ፣ በውህደት በመሰረትነው፣ በአርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ዴሞክራሲ፣ ንቅናቄ፣ ሥም፣ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
1ለወታደራዊና የፖሊስ ሠራዊት አባላት፣
የወያኔ ዘረኛና አምባገነን ቡድን ዕድሜን ለማሳጠርና ሁላችንንም በእኩልነት የምታስተናግድ ሀገር እንድትኖር ፣ በየቦታው የሚደረገውን ትግል፣ የሰሞኑን ቆራጥ የዓየር ሃይል መኮንንኖች ያሳዩትን ዓርያነት በመከተልና በተገኘው አጋጣሚና ሁኔታ በመጠቀም፣ እንድትቀላቀሉ በውህደቱ ድርጅት፣ በአርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ዴሞክራሲ፣ ንቅናቄ፣ ሥም፣ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የተከበርከው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ፣
በረጅም ታሪክህ አይተሄው ለማታውቀው፣ ውርደት፣ ክፋት፣ የመከፋፈልና የመጋጨት አደጋ፣ የመብት እረገጣና አፈና፣ ሀገርና ሕዝብን የማራከስና የመሸጥ፣ ዕኩይ ተግባር፣ የተጠናወተው ወያኔ እና የግብር አበሮቹን፣ ጠራርጎ ለማስወገድ በተጀመረው የጋራ ትግል ውስጥ በቀጥታ እንድትሳተፍም ሆነ በምትችለው ሁሉ እርዳታ እንድታደርግ፣ በዛሬው ጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም የአርበኞችና የግንቦት 7 ውህደት በወለደው፣ በአርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ዴሞክራሲ፣ ንቅናቄ ሥም፣ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
አንድነት ሃይል ነው!!! ድል ለኢዮጵያ ሕዝብ!!!
አርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ለዴሞክራሲ፣ ንቅናቄ ጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም

Monday, 12 January 2015

ትናንት ከዉጭ ወራሪዎች የታደገን መከላከያ ሠራዊታችን ዛሬም ከአገር ዉስጥ ወራሪዎች ይታደገናል


አስተዋዩ የኢትዮጵያ ህዝብ እድገቱን ለሚመኙ አስተዋይ መሪዎች እለታደለምና ደሃ ነዉ፤ ረሀብተኛ ነዉ አልተማረም ወይም ኋላ ቀር ህዝብ ነዉ ማለት ይቻል ይሆናል፤ ሆኖም የኢትዮጵያ ህዝብ ያሰኘዉን ያክል ቢደኸይ ወይም ኋላ ቀር ቢሆን ለነፃነቱ፤ ለአንድነቱና ለግዛት አንድነቱ መከበር ያለስስት ደሙን የሚያፈስ ጀግና ህዝብ ነዉ። ይህ ጀግንነት ደግሞ አንደተረት በአፍ ተነግሮ የሚያበቃ ሳይሆን በመተማ፤ በአድዋ፤ በማይጮዉ፤ በወልወል፤ በፊልቱና በጎዴ የጦር ሜዳዎች ሊወጉትና ሊወሩት የመጡ ጠላቶቹ ጭምር የመሰክሩለት የታሪክ ሐቅ ነዉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ከጀግንነቱ ጋር አርቆ አስተዋይና ታጋሽ ህዝብ ነዉ፤ ሆኖም ይህንን ህዝብ የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ በተከታታይ የገዙት የገዢ መደቦች ጀግንነቱን ለራሳቸዉ ክብርና ዝና ታጋሽነቱን ደግሞ ለስልጣን ዘመናቸዉ ማራዘሚያ አድርገዉ የመከራ ዘመን እያስቆጠሩ ኖረዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ታጋሽ ህዝብ ቢሆንም እርግጫዉና ጭቆናዉ በበዛበት ቁጥር አምርሮ የሚነሳ ለገዢ መደቦች የማይመች ቁጡና እልህኸኛ ህዝብ መሆኑንም በተከታታይ አሳይቷል። ይህንን ደግሞ በ1966 ዓም ከዳር ዳር ባቀጣጠለዉ ህዝባዊ አብዮት በ1983 ዓም ደግሞ በአራቱም ማዕዘናት ባካሄደዉ ህዝባዊ አመጽ አሳይቷል። ሆኖም አብዮቱንና ህዝባዊ አመጹን ከትግል ሜዳ እስከ ፖለቲካ ስልጣን አደባባዮች ድረስ አቀነባብሮ የሚመራ የተደራጀ ህዝባዊ ኃይል ባለመኖሩ የኢትዮጵያ ህዝብ የታገለላቸዉ የትግል ዉጤቶች ሁሉ የአምባገነኖች መጠቀሚያ ሆነዉ ቀርተዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ጀግና ነዉ፤ ተጋሽ ነዉ፤ ወይም አርቆ አስተዋይ ነዉ ሲባል እንዚህ እሴቶች ወንዱን፤ ሴቱን፤ ምሁሩን፤ ገበሬዉን፤ ሰራተኛዉንና መለዮ ለባሹን ሁሉ የሚያጠቃልሉ ህዝባዊ እሴቶች ናቸዉ እንጂ የአንድ ህብረተሰብ ክፍል ልዩ ንብረቶች አይደሉም። በእርግጥም አብዛኛዉ የታሪካችን ክፍል በአገር አንድነት ግንባታና ይህንኑ አንድነት ከዉጭ ወራሪዎች በመከላከል ጦርነት ላይ ያተኮረ በመሆኑ ጀግንነትን በቀጥታ የምናያይዘዉ ከዚሁ አገርንና የአገር አንድነትን ከማስከበር ስራ ጋር ነዉ። በእርግጥ አገርን ከጠላት መከላከል ጀግንነት ነዉ፤ ሆኖም መሳሪያ ተሸክሞ አገሩን ከጠላት የሚከላከል ሠራዊት ምን እለብሳለሁ፤ ምን እበላለሁ፤ በምንስ እዋጋለሁ ከሚለዉ ስጋት ተላቅቆ በሙሉ ኃይሉና አዕምሮዉ መዋጋት የሚችለዉ እንደነሱ ጀግና የሆነና በደጀንነት የተሰለፈ ህዝብ ሲኖር ብቻ ነዉ።
እስከ አድዋ ጦርነት ድረስ አገራችን ኢትዮጵያ የመሪዉን የክተት አዋጅ ጥሪ እየሰማ የሚዘምት ህዝብ እንጂ ቋሚ የመከላከያ ሠራዊት አልነበራትም። ባለፉት 60 አመታት ግን ኢትዮጵያ የምድር ጦር፤ አየር ኃይል፤ ብሔራዊ ጦርና እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ ደግሞ የባሕር ኃይልን ጭምር ያካተተ ዘመናዊ የመከላከያ ሠራዊት ነበራት። ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የአገራችንን በትረ ስልጣን እስከጨበጠበት እስከ 1983 ዓም ድረስ የነበረዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከሞላ ጎደል በመስኩ ልምድ፤ ችሎታና እዉቀት ባካበቱ ባለሙያዎች የተሞላና የአገረን ዳር ድንበር ከመጠበቅ ባሻገር ለወገናቸዉ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ ደህንነት ቀና አመለካከት ባላቸዉ አገር ወዳዶች የተገነባ ሠራዊት ነበር። ወያኔ በ1983 ዓም አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ይህንን አገር ወዳድ የሆነ ፕሮፌሺናል ሠራዊት በትኖ ነዉ ለአንድ ድርጅት ጥቅምና ዝና በቆሙ፤ ፊደል ባልቆጠሩና ሙያዊ ብቃት በሌላቸዉ መሀይሞች የተሞላ መከላከያ ሠራዊት የተካዉ። እንደዚህ ስንል ግን ወያኔ በገነባዉ የአገር መከላከያ ሠራዊት ዉስጥ አገራቸዉ ኢትዮጵያን ከራሳቸዉ በላይ የሚወዱና ለአገራቸዉና ለወገናቸዉ ክብርና ጥቅም መስዋዕት ለመሆን የቆረጡ ሰዎች የሉም ማለት አይደለም፤ እንዲያዉም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሚመራዉና የግዳጅ ትዕዛዝ የሚወስደዉ አገራቸዉን በሚጠሉ ዘረኞች መሆኑ ነዉ እንጂ ዛሬም ቢሆን አብዛኛዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባል የእናት አገሩ ዳር ድንበር መደፈርና የወገኖቹ መረገጥ የሚያንገበግበዉ አገር ወዳድ ሠራዊት ነዉ።
የ1966ቱ ህዝባዊ አብዮት ሲፈነዳ የነበረዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የፊዉዳሉ መንግስት የደሞዝ ጭማሪ አድርጎለት ከህዝባዊ ኃላፊነቱ ሊያዘናጋዉ ሲሞክር – “ሎሚ ተራ ተራ፤ “ሎሚ ተራ ተራ እኛስ አግኝተናል ሲቪሉን አደራ” ብሎ የህዝብ ወዳጅነቱን ያረጋገጠ አገር ወዳድ ሠራዊት ነበር። አመጸኛዉ ደርግ ይህንን ሠራዊት ተጠቅሞ ነዉ የቀዳማዊ ኃ/ሥላሤን ስርዐት ያስወገደዉና የመሬት አዋጅን የመሳሰሉ ስር ነቀል አርምጃዊዎች መዉሰድ የጀመረዉ። አምባገነኑ ደርግ ቁልፍ በሆኑ የመከላከያ ሠራዊት ተቋሞች ዉስጥ ታማኝ የሆኑ የራሱን ሰዎች አስቀምጦ ለ17 አመታት የኢትዮጵያን ህዝብ ቢረግጥም ጄኔራል ተፈሪ በንቲን፤ ኮሎኔል አጥናፉ አባተን፤ ተስፋዬ ትርፌን፤ ጄኔራል መርዕድ ንጉሴን፤ ቁምላቸዉ ደጄኔን፤ አምሀ ደስታንና ፋንታ በላይን የመሳሰሉ እስከመጨረሻዉ ትንፋሻቸዉ ድረስ ህዝባዊ አደራቸዉን የጠበቁ ታማኝ የህዝብ አገልጋዮች በመከላከያ ሰራዊቱ ዉስጥ ነበሩ። በንጉሰ ነገስቱም ዘመን ቢሆን ገና ከጥዋቱ ከዝናና ጥቅም ይልቅ የአገራቸዉን ጥቅም ያሰቀደሙ እንደ ጀኔራል መንግስቱ ነዋይ አይነት የለዉጥ አርበኞች ነበሩ።
ወላድ በድባብ ትሂድ – ዛሬም ቢሆን እጅግ በጣም ጨለማ በሆነዉ ጨካኝና ዘረኛ ስርዐት ዉስጥ ጨለማዉን እየገለጡ በድፍረት የአገራቸዉን ህዝብ ጩኸትና ሰቀቃ አዳምጠዉ ዘረኝነት በቃ ያሉ ጀግኖች በመከላከያ ሠራዊቱ ዉስጥ አሉ። በአንድ ቋንቋና በዘር ሰንሰለት ተሳስረዉ የሚሰሩ የወያኔ ደህንነቶች መግቢያዉንና መዉጪያዉን ቆልፈዉ ለጌቶቻቸዉ ዘብ ቢቆሙም ጀግናና ጭስ መዉጪያ አያጣምና ከፍተኛ ልምድና ችሎታ ያላቸዉ የወያኔ መከላከያ ሠራዊት አባላት ከወያኔ ጎራ እየወጡ የህዝባዊ አመጹን ጎራ እየተቀላቀሉ ነዉ። ሁላችንም በየቀኑ በግልጽ እንደምናዉ ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ ሁለት አይነት ዜግነት ፈጥረዋል። አንደኛዉ ዜግነት ወያኔና አገራቸዉን ከድተዉ የወያኔ ተላላኪ በሆኑ እንደነ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ፤ አዲሱ ለገሰና ሬድዋን ሁሴንን በመሳሰሉ ሆድ አደሮች የተሞላ ሲሆን፤ ሁለተኛዉ ዜግነት ደግሞ አገር ወዳዶችና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ያሉበት ነዉ። ከእንደዚህ አይነቱ በዘር ከተከፋፈለና እያንዳንዷ ኮሽ ያለች ነገር በወያኔ ደህንነት ሰራተኞች ተመዝግባ በምትመረመርበት አገር ዉስጥ ለህዝባዊ አላማ ጸንቶ መቆምና ስርዐቱን አልፈልግም ብሎ የነፃነት ኃይሎችን መቀላቀል ከፍተኛ ጀግንነትንና ቆራትነትን ይጠይቃል። ቆየት ባለዉ ግዜ እነ መቶ አለቃ ተሾመ ተንኮሉና ጄኔራል ከማል ገልቹ፤ አሁን በቅርቡ ደግሞ ሦስቱ የተዋጊ ሂሊኮፕተር አብራሪዎችና አራቱ ባለከፍተኛ ማዕረግ የአየር ኃይል ተዋጊ ጄት አብራሪዎች የወሰዱት ህዝባዊ እርምጃ ከሆነ በኋላ በሰበር ዜና ስንሰማዉ ቀላል ይመስላል እንጂ እርምጃዉ ጀግንነትን፤ ቆራጥነትንና በህይወት መወራረድን ይጠይቃል። እነዚህ ለፍትህ፤ ለነጻነትና ለእኩልነት የቆሙ ቆራጥ ዜጎች በወሰዱት እርምጃ አገር ዉስጥና ከአገሩ ዉጭ የሚኖረዉን ኢትዮጵያዊ እጅግ በጣም ደስ አሰኝቷል። በእርግጥም እነዚህ ጀግኖች የወሰዱት እርምጃ ህዝባዊ ትግሉን የሚያነቃቃና የሚያጠናክር ነዉና በልጆቻችን እርምጃ ልንኮራና ደስ ሊለን ይገባል። ሆኖም ይህ ቆራጥ እርምጃ የትግል ጥሪም ነዉና ሁላችንም ጥሪዉን አዳምጠን ዛሬ ነገ ሳንል አሁኑኑ አቤት ማለት አለብን።
ዛሬ ለአመታት በላይ ሲታመስና ሲብሰለሰል የቆየዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ብሶት ገንፍሎ ወጥቶ ወደ ለየለት ህዝባዊ አመጽነት እየተቀየረ ነዉ። ይህንን ህዝባዊ አመጽ በትክክል መርቶ ከግቡ ለማድረስና ከዚህ በፊት በተከታታይ የተፈጠሩትን የስልጣን ከፍተቶችና ስህተቶች አርሞ ትግሉን በእስማማኝ መሰረት ላይ ለማቆም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ታሪካዊና አገራዊ ሃላፊነት አለበት። በቅርቡ ተዋጊ የጦር ሂሊከፕተራቸዉን እንደያዙ የወያኔ ስርዐት በቃን ብለዉ የነጻነት ሀይሎችን የተቀላቀሉት ጀግኖች ዜና ሲሰማ ወያኔ ከፍሎ ያሰማራቸዉ ተናካሽ ዉሾቹ ያንን የለመዱትንና የተካኑበትን እንቆርጣችኋለን እንፈልጣችኋለን የሚል ተራ ዛቻቸዉን አሰምተዉናል። ከዚህ አልፈዉም ወያኔ የታጠቀዉን መሳሪያ ዘመናዊነትና ያደራጀዉን ሠራዊት ብዛት ደጋግመዉ በመጥቀስ እነሱን መንካት ከእሳት ጋር መጫወት እንደሆነ ሊነግሩን ሞክረዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ በወቅቱ ስሙን እንኳን አጣርቶ የማይጠራዉ ህወሓት ከሰሃራ በታች ተወዳዳሪ የለዉም የተባለዉ ሠራዊት የገነባ ኃይል ለምን አንደሚዋጋ እንኳን በማያዉቅ ጀሌ ጦር ማሸነፍ ከቻለ ዛሬማ ፍጹም የሆነ ህዝባዊ መሠረት ያላቸዉና ለምንና ለማን እንደሚዋጉ ጠንቅቀዉ የሚያዉቁ የነጻነት ኃይሎች ካሰቡበት ለመድረስ የሚያግዳቸዉ ምንም ምድራዊ ኃይል እንደሌለ ወያኔና ሆድ አደር ደጋፊዎቹ ተንቅቀዉ ሊያዉቁ ይገባል። ወያኔ ልቡ ስላበጠ የተለቀ ይምሰለዉ እንጁ የትልቅነቱ መገለጫ አድርጎ የሚተማመንበት የመከላከያ ሠራዊት ያቺ የፍጥጫ ቀን ስትመጣ ወያኔን ለመደምሰስ ወገኖቹን የሚቀላቀል ሠራዊት ነዉ። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ጀግኖቹ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት የወሰዱት ህዝባዊ እርምጃም በአየር ኃይሉ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን ቀን፤ ግዜና ሁኔታ እየመረጠ እግረኛ ሠራዊቱም የሚወስደዉ እርምጃ እንደሆነ ያለ ጥርጥር እናምናለን።
ዉድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሆይ – አንተንና ወገኖችህን በዘር ከፋፍሎ እየገዛ አገርህን የሚያፈርሰዉ ወያኔ ለዚህ እኩይ ስራዉ የሚጠቀመዉ አንተኑ ከህዝብ አብራክ የወጣኸዉን የህዝብ ልጅ ነዉ። በቅርቡ ባህር ዳር ዉስጥ የቅዱስ ታቦት ማደሪያ የሆነዉን ቦታ ከቤ/ ክርሲቲያን ቀምቶ የሸቀጥ መሸጫ ለማድረግ ያደረገዉን ሙከራ የተቃወሙ ኢትዮጵያዉያን ወንድሞችህና ወንድሞችህ እንዲሁም አለም በቃኝ ያሉ መነኩሴ ጭምር በጥይት ጨፍጭፏል። በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ወልቃይት ጠገዴን ከጎንደር ቆርጦ ትግራይ ላይ የቀጠለዉ ወያኔ ይህ ፀረ ህዝብና ፀረ አገር ወንጀል አልበቃ ብሎት ለዘመናት አብሮ የኖረዉን የትግራይንና የጎንደርን ህዝብ ለማባላት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ነዉ። በታህሳስ ወር አጋማሽ ጎንደር ዉስጥ የትግራይና ክልልና የጎንደር ሚሊሺያዎች የተኩስ ልዉዉጥ ካደረጉ በኋላ ወያኔ አገርን ለመዉረር በሚመጣ ጠላት ላይ እንጂ በራሱ ወገን ላይ መዝመት የሌለባቸዉን ከ30 በላይ ታንኮችና ከባድ መሳሪያ የታጠቁ ወታደሮች ወደ ጎንደር በማሰማራት አገሩንና ወገኑን መጠበቅ ያለበትን ሠራዊት ከገዛ ወገኖቹ ጋር እንዲፋጠጥ አድርገዋል።
በዚህ ፈታኝና እጅግ በጣም አስቸጋሪ ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሂድና ግድል በተባለ ቁጥር መጠበቅና መንከባከብ የሚገባዉን የገዛ ወገኖቹን የማይገድል አስተዋይና ወገንተኛ ሠራዊት መሆኑን በተግባር ማሳየት አለበት። አዎ! የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ምንግዜም ቢሆን በአገሩ ጠላቶችና ወራሪዎች ላይ ብቻ እንጂ እያበለና እያጠጣ ባሳደገዉና እኔንና አገሬን ጠብቅ ብሎ ባስታጠቀዉ ህዝብ ላይ በምንም አይነት አፈሙዙን አያዞርም። ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔ በላይ ጠላት የላቸዉም። ህዝብና አገር እስከ ምድር ፍጻሜ ድረስ አብረዉ የሚዘልቁ ተከታታይ ክስተቶች ናቸዉ፤ ወያኔ ግን ትናንት በጠመንጃ ሀይል መጥቶብን እኛንና አገራችንን ለማጥፋት የሚታገል የለየለት ጠላት ነዉ። ከዛሬ ጀምሮ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ባገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ ወያኔን ከዉስጥ ሆኖ መቦርቦር አለበት፡ ይህንን ማድርግ ካልቻለ ደግሞ ወያኔ ከወገኖቹ ጋር እንዲዋጋ ሲያሰማራዉ ወያኔን እየከዳ ከነጻነት ኃይሎች ጋር ተቀላቅሎ ወያኔን ለመደምሰስ በሚደረገዉ ትግል ዉስጥ ወሳኙን ሚና መጫወት ይኖርበታል። ግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከዚህ ቀደም እንዳደረገዉ ሁሉ አሁንም እንደገና ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት . . . ና ተቀላቀለንና አንድ ላይ ሆነን ወያኔንና ወያኔ የገነባዉን ዘረኛ ስርዐት ቀብረን የኢትዮጵያን ህዝብ ከዉርደት፤ ከእስር፤ ከድብደባ ከግድያና ከስደት እናድን የሚል አገራዊ ጥሪዉን ከአደራ ጋር ያስተላልፋል።

ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌን እንሁን!!!


በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የፌደራል ፓሊስ በእሁድ ታህሣሥ 28 ቀን 2007 ዓ.ም. የቴሌቪዥን ፕሮግራሙ በግፍ እስር ላይ የሚገኘውን የግንቦት 7 ዋና ፀሐፊን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አቅርቦት ነበር። ይህ የ10 ደቂቃዎች ምስል ለቁጥር በሚያታክት ብዛት ተቆራርጦ የተቀጣጠለ በመሆኑ አቶ አንዳርጋቸው ምን ተጠይቆ ምን እንደመለሰ ማወቅ አይቻልም። ስለሆነም በንግግሩ ይዘት ላይ አስተያየት መስጠት ይናገረው አይናገረው በአልታወቀ ጉዳይ ማብራሪያ መስጠት ይሆናል።  ስለዚህም፣ በንግግሩ ይዘት ላይ ጊዜ ከማጥፋት ህወሓት አንዳርጋቸው ጽጌን አሁን ማቅረብ ለምን እንደፈለገ መተንተን ይበልጥ ጠቀሜታ  አለው ብሎ ግንቦት 7 ያምናል።
አሁን ህወሓት በውስጥም በውጭም ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የገባበት ጊዜ ነው፤ በራሱ በድርጅቱ ውስጥም ሰላም የለም። ህወሓት የትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ስር እንደሆነ አድርጎ በመቁጠር መላዋን ኢትዮጵያን ለመዝረፍና ለማጥቃት እንደ መንደርደሪያ፤ በሌላኛው የኢትዮጵያ ክፍል ተቃውሞ ሲበዛበት ደግሞ እንደ መደበቂያ ዋሻ ሲጠቀምበት የነበረው ጊዜ አብቅቶ የትግራይ ሕዝብ በህወሓት ላይ ማመጹ በግልጽ በተግባር እየታየ ነው። በርካታ የትግራይ ልጆች በህወሓት ላይ ነፍጥ አንስተዋል፤ ከፊሎቹ ደግሞ በሰላማዊ ትግል ህወሓትን ማስወገድ ይቻላል ብለው በክልላቸውም ከክልላቸውም ውጭ ከህወሓት ጋር ፍልሚያ ገጥመዋል። ህወሓት መሠረቴ ነው ከሚለው የትግራይ ክልል ፈጽሞ ሊነቀል የሚችል መሆኑ ግልጽ ምልክቶች እየታዩ ነው። የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ከትግራይና ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያገናኘው የአማርኛና የትግርኛ የቴሌቪዥን ፕሮግራም መጀመሩ የህወሓት ሹማምንትን ናላ ያዞረ እርምጃ ሆኗል።
የህወሓት ሌላው መተማመኛው የጦር ሠራዊቱ ነበር። ህወሓት፣ የኢትዮጵያን መከላከያ ጦር ሠራዊት ዘረኛ በሆነ መንገድ አደራጅቶ፤ ከፍተኛ አመራሩን በታማኝ አባላቱ ሞልቶ ተደላድሎ  የተቀመጠ መስሎ  ታይቶ ነበር። አሁን ግን ይህም ምስል አሳሳች እንደሆነ ግልጽ እየሆነ መጥቷል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን ህወሓትን የማገልገል ፍላጎት የሌላቸው መሆኑን፤ እንዲያውም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን በመቆም የህወሓትን ውድቀት ለማፋጠን ያላቸውን ጉጉት በግልጽ እያሳዩ ነው። አየር ኃይል ውስጥ ያለው ተቃውሞ ገሀድ የወጣ  ዜና ሆኗል። እንደ አየር ኃይል ገሀድ የወጣ ዜና አይሁን እንጂ በሌሎችም የሠራዊቱ ክንፎች ያለው አመጽ ተመሳሳይ የጡዘት ደረጃ ላይ ደርሷል።
ብአዴን እና ኦህዴድ ውስጥ ለአገራቸው ለኢትዮጵያ፣ እንወክለዋለን ለሚሉት ሕዝብ እና ለራሳቸው ክብር ያላቸው አባላት ብቅ ብቅ እያሉ ነው። ብአዴንንና ኦህዴድ እንደ ድሮ ፍጽም ታማኝ አገልጋዮች የመሆናቸው ጊዜ እያበቃ ነው። ደኢህዴንም ቢሆን ሙሉ በሙሉ የሚታመን አይደለም። ጊዜው ለህወሓት እጅግ የመክፋቱ ምልክት ደግሞ እራሱ ህወሓት ውስጥም ስምምነት የሌለ መሆኑ ነው። ህወሓት ይይዘው ይጨብጠው ጠፍቶታል።
ለዓመታት የዘለቀው የሙስሊም ወገኖቻችን ተቃውሞ እረፍት ነስቶት እያለ በባህርዳር የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ተቃውሞ ተጨመረበት። የአምቦውን ተቃውሞ አዳፈንኩ ሲል የጎንደር ተቀሰቀሰበት። ለጉራና ለሀብት ዘረፋ ሲል ያስጀመረው  የአባይ ግድብ፣ ጥበቃው ብቻ እንኳን ፋታ የሚነሳ ሥራ ሆነበት። ጋምቤላ፣ አፋርና፣ ሶማሊ የግጭት ቀጠናዎች ከሆኑ ዓመታት አስቆጠሩ።
ከላይ የተዘረዘሩት ጉምጉምታዎች፣ ተቃውሞዎችና አመጾች ተቀናጅተው የመጡ ዕለት መድረሻ እንደሚያጣ የተገነዘበው ህወሓት ትኩረት ማስቀየሻ መፈለጉ ግድ ነበር። በግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እምነት በአሁኑ ሰዓት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ወደ ሚዲያ መቅረብ ምክንያቱ ይህ ነው። አንዳርጋቸውን ወደሚዲያ በማቅረብ ትኩረትን የማስቀየስ ስትራቴጂ!
የፊልሙ ማጀቢያዎች የነበሩት የሂውማን ራይትስ ዎች ሪፓርት፣ ስለእንግሊዝ ጋዜጣ የተነገረው፣ አሜሪካ ስለምትፈጽመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተዘከረው፣ ወዘተ … ወዘተ የሚያመላክቱት አንድ አቢይ ሀቅ አለ። ይህም ኢትዮጵያዊያን ፀሐይና ብርድ ሳይበግራቸው “እኔ አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ” እያሉ በእንግሊዝ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ በእንግሊዝ ኤምባሲዎች እና በአውሮፓ ኅብረት ሲያደርጓቸው የቆዩ ተቃውሞዎች ውጤታማ መሆናቸው ነው። በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የፈጠሩት ጫና ወያኔን ወደ ተከላካይነት አውርዶት “እኔ ንፁህ፣ አሜሪካ ርኩስ” እንዲል አድርጎታል።  ወያኔ፣ ስለንፅህና ምስክርነትት ይሰጥልኛል ብሎ ተስፋ ያደረገው ደግሞ ራሱ ነፃነቱን ገፎ እስረኛው ያደረገው ሰው መሆኑ ጥረቱ እንደምን ውል አልባ እንደሆነበት ያሳያል። ንፅህናን ነፃ ባልሆነ ሰው ማስመስከር ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? ይህ ክስተት፣ የኢትዮጵያዊያን ዘርፈ ብዙ ተቃውሞ የወያኔን የመከላከል አቅም ማዳከሙን በግልጽ ያሳያል። ይህ ለኢትዮጵያዊያን ትልቅ ብሥራት ነው።
ከላይ የተዘረዘሩት ምክንያቶች ህወሓት አንዳርጋቸውን ወደሚዲያ ለማቅረብ ምክንያት ይሁኑ እንጂ የአንዳርጋቸው ለሶስተኛ ጊዜ በወያኔ ቴሌቬዥን መታየት በኢትዮጵያዊያን ላይ የፈጠረው ስሜት ህወሓት ከጠበቀው ፈጽሞ የተለየ ነው።
ኢትዮጵያዊያን አንዳርጋቸውን ሲያዩ የሚታያቸው ጽናት፣ አርበኝነትና አልበገር ባይነት ነው። የአንዳርጋቸው ምስል በታየ ቁጥር ኢትዮጵያዊያን ፀጉራቸው ይቆማል፤ ደማቸው ይፈላል። ወያኔዎች አንዳርጋቸውን የፈለጉትን ቢያናግሩት ችግር የለም። ለጊዜው በእጃቸው ውስጥ ስለሆነ ያላለውን ያለ ሊያስመስሉ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቃል። ወደፊት ደግሞ ሊናገር ያልፈለገውን ያናግሩት ይሆናል። ይህ ሁሉ የሚያመጣው ለውጥ የለም። አንዳርጋቸው ስለወያኔ ምንነትና ማንነት ማንም ሳያስገድደዉ በነፃነት አገር ዉስጥ በግልጽ ተናግሯል፣ አሁንም ወያኔዎች እራሳቸዉ በሰሩት ፊልም ዉስጥ እነሱ በማይገባቸው መንገድ ለኢትዮጵያን ሕዝብ ተናግሯል። እንኳንስ እነሱ እሱም ራሱ በማይገባው መንገድ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ ገብቷል። አንዳርጋቸውን ስናይ በህወሓት ፋሽስታዊ መዳፍ ውስጥ የወደቁብንን ጀግኖቻችንን ሁሉ ያስታውሰናል። በአስር ሺዎች ይቆጠራሉ። የአንዳርጋቸው ምስል ለግላጋ ወጣቶች፣ በሳል አዛውንት፣ ምርጥ ወንድሞችና እህቶች በወያኔ እስር ቤቶች ፍዳቸውን እያዩ መሆኑን ያስታውሰናል። ምስሉ ብቻውን ያናግረናል፣ ያነቃናል፣ ያነሳሳናል!!!
ግንቦት 7:  የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አንዳርጋቸው ጽጌን፣ በርካታ ጀግኖቻችንን፣እራሳችንንና አገራችንን ከወያኔ እስር ነፃ ለማውጣት ክንዳችንን እናበርታ፤ ሁላችንም “እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነን” እንበል፤ ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌን እንሁን ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

ሕወሃት በመንግስት ስልጣን ባለቤትነትና በወንበዴነት መሐል ያለው ልዩነት ተምታቶበታል


ኢትዮጵያን በግፍና በዝርፊያ የሚገዛው የህወሀት ጉጅሌ በመንግስትነትና በወንበዴነት መሀል ያለውን ልዩነት ከ፪፫ ዓመት ስልጣን ዘመን ብኋላ እንኳን ሊገለጥለት አልቻለም። ወይም እንዳመችነቱ ሁለቱን እያምታታ መቀጠሉን እንደብልህነት ቆጥሮታል። መንግስት መሆንንና ባለህገመንግስት መባልን ከመቆነጃጃ ኩልነት ባልተናነሰ በለጋሾቻቸው ባዕዳን ፊት ይጠቀሙበታል እንጂ ለኛ ለዜጎቹማ ወንበዴነታቸውን ሊደብቁን እንኳን አይጨነቁም።
በቅርቡ ህወሀት የትግራይ ሪፐብሊክ ለማቋቋም የክህደት ተግባሩን የጀመረበትን ፵ኛ ዓመት በዓሉን ትግራይ ውስጥ በማክበር ላይ ሳለ የቀድሞው የህወሀት ታጋይ ያሁኑ የሀገሪቱ ጦር ሎች ኤታማዦር ሹም ተብዬው ሳሞራ የኑስ የህወሀት መንግስት ያገራችን ገበሬ ወፎችን ከማሽላው ለመከላከል እንደሚጠቀምበት መስፈራሪቾ የሚጠቀምበት ሕገ መንግስት ላይ የተጠቀሰውን የሀገሪቱን ሰራዊት የፖለቲካ ገለልተኝነት ድንጋጌና ሰራዊቱ “ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ ይሆናል” የሚለውን የይስሙላ ህግ ባደባባይ አውልቆ ጥሎ ተቃዋሚዎችን የሚወነጅል ሰፊ ንግግር ሲያደርግ ተደምጧል። ሳሞራ ይህን ንግግር በሚደረግበት ቦታ አፋቸውን ከፍተው ከሚያደምጡት ውስጥ የሀገሪቱን መንግስት እንዳሻቸው የሚዘውሩት የወያኔ ሹማምንት ነበሩ። በዚህ ንግግር ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የባዕዳን መሳሪያ ሆነው የሀገሪቱን ሉዓላዊነት እንደሚፈታተኑ ሀይሎች በመቁጠር ፍጹም ሀሰትና ጅምላ ፍረጃ ሲያደርግ “እረ ይህ ነገር በመደበኛ ስራህ የስራ ዝርዝር ውስጥ አለመኖር ብቻ ሳይሆን የተከለከለ ነው” ያለው አልነበረም። ይህን መርዝ ከተናገረና ተቃዋሚዎችም ላይ ዛቻውን ካሰማና ከወነጀለ በኋላ የህወሀት ልዩ አገልጋይነቱንም ካረጋገጠ በኋላ “ለማንኛውም እኔ ወታደር ስለሆንኩ አይመለከተኝም” ይምትል የፌዝ የግርጌ ማስታወሻ ብጤ በመናገር ህወሀት እያምታታ የሚጠቀምበትን ውንብድናና መንግስትነት አደባልቆ የሚያደርገውን ጉዞ ካላንዳች ሀፍረት አመልክቶናል። መሰረታዊ መንግስታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ባለባቸው ሀገሮች የዚህ ዓይነት እነጋገር ባደባባይ አሰምቶ ለቀናት በያዙት ስልጣን ላይ መቀመጥ አይቻልም። ውንብድናና መንግስትነት ድንበር ባጣባት ኢትዮጵያ ይህ ህግ መተላለፍ ሳይሆን በገሀድ የምንኖረው የውርደት ህይወት ከሆነ አመታት ተቆጠሩ።
ግንቦት ሰባት የፍትሕ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ሀገሪቱን በቅንነት ለማገልገል ሰራዊቱን የተቀላቀለው ተራው ወታደርና የበታች ሹማምንት ይህንን መልዕክት በቅጡ ሊያደምጡት ይገባል ብሎ ያምናል። በየትኛውም ዘርፍ ያለው ሰራዊት አለቆቹ የህወሀት ስንቅ ተሸካሚዎች እንጂ የውዲቱ ሀገራችን ዘበኞችና ሉዓላዊነት አስከባሪዎች አለመሆናቸውን ጠንቅቆ ማወቅ አለበት። ሰራዊቱን እያዘጋጁት ያሉትም በደል የበዛበት የገዛ ወገኑ መብቱን በሚጠይቅበትና ለመብቱ በሚታገልበት ስዓት አፈሙዝ ወገኑ ላይ እንዲያዞር እንጂ የሀገርና የህዝብ ከለላ እንዲሆን አይደለም። ለነዚህ የወያኔ የጦር አለቆች መታዘዝ ለሀገሪቱ ዘብ መቆም ሳይሆን የህወሀት ሎሌነት መሆኑንም በቅጡ መገንዘብ ያሻል። ብዙዎች የሰራዊቱ አባላት ከዚህ ቀደም እንዳደረጉትና ዛሬም እያደረጉ እንዳሉት በተገኘው አማራጭ ሁሉ ሰራዊቱ ይህዝቡን ወገኖች እንዲቀላቀል ጥሪያችንን እናቀርባለን። በየከተሞቹ በራሳቸው በቁባቶቻቸውና በዘመዶቻቸው ስም የጦፈ ንግድ ፣ ፎቅ ግንባታና ፈንጠዝያ ላይ ያሉት የወያኔ የጦር አለቆች የቆሙት የራሳቸውን የዝርፊያ ስርዓት አደረሳቸው ድረስ ለማቆየት እንጂ ለሀገር ዘብነት አይደለም።
ሀገራችን የዜጎቿ ሁሉ መብት ተጠብቆ ስልጣኑ በህገመንግስት ተገድቦ የሚሰራ መንግስት ያስፈልጋታል ይገባታልም። በህግ አምላክ ተባብለው ህግ አክብረው መኖር ባህላቸው ላደረጉ ህዝቦች ህግና ውንብድናን አደባልቆ የሚገዛ መንግስት አይገባንም። ሰራዊቱም ለሀገር አገልግሎቱ የሚገባውን ክብር የሚያገኝበት ስርዓት እንጂ ነጋ ጠባ በወያኔ ግምገማ ከሚሸማቀቅበት በወገኖቹ ላይ እንደባዕድ እንዲተኩስ ከመታዘዝ የሚላቀቅበት ስርዓት ይገባዋል።
ከሳሞራ የእብሪትና ማናለብኝነት ንግግር የምንማረው የህወሀት የጦር አዛዦች የሀገሪቱ ወታደሮች ሳይሆኑ ህዝብ የናቁ ጭፍን ራስ ወዳድ፣ ዘረኛና ሀገር ዘራፊ ማፊያዎች መሆናቸውን ብቻ ነው። ይህን ሀቅ በተለይ በቅርብ ሆናችሁ የምትታዘቡ በተራ ውትድርናና የበታች መኮንኖች ሆናችሁ ሀገሪቱን ለማገልገል የገባችሁ የሰራዊቱ አባላት የህዝብና የሀገር ወገንተኝነታች ሁን ማረጋገጫ ጊዜው ነገ ሳይሆን ዘሬ መሆኑን ላፍታም ልትዘነጉ አይገባም።

ቀኑ ሲቃረብ መውጫው ይጠባል!



ኢትዮጵያ ሀገራችን በታሪኳ ከአስከፊ የፈተና አረንቋ ውስጥ ተገፍታ የገባችበት ዘመን ቢኖር ይህ የምንገኝበት ዘመነ ወያኔ ብቻ ነው፡፡ ዜጎቿ ከፋሽስት ኢጣልያ በከፋ ሁኔታ ይህ ቀረሽ የማይባል የመከራ መአት የወረደባቸውና እየወረደባቸው የሚገኝበት ዘመን ቢኖር ይህ የምንገኝበት ዘመን ወያኔ ብቻ ነው፡፡ እስር ቤቶች ሞልተው ተጨማሪ እስር ቤቶች መገንባት ከልማት ተቆጥሮ የሚፎከርበት ዘመን ቢኖር ይኸው ዘመነ ወያኔ ብቻ ነው፡፡ የሀገሪቱ ብሄራዊ ባንክ ንብረት የሆ ነው ወርቅ በባሌስትራ ለውጦ እስከ መዝረፍ የደረሰ በጠራራ ፀሀይ የህ ዝብና የሀገር ሀብት ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ በጥቂቶች የሚዘረፍበት ዘመን ቢኖር የምንገኝበት ዘመነ ወያኔ ብቻ ነው፡፡ የጅምላ እስር፤ የጅምላ ግድያ፤ የጅምላ ስደትና መፈናቀል፤ ይበልጡንም በታሪካችን ታይቶ በማያውቅ መልኩ ለሞት፤ ለእስር፤ ለመፈናቀልና ለስደ ት ምክንያቱ የተገኘንበት ዘውግ የሆነበት ዘረኛ ዘመን ቢኖር ይኸው ዘመነ ወያኔ ብቻ ነው፡፡
ባጠቃላይ ላለፉት 23 አመታት ወያኔ ማድረግ የሚችለውን አስከፊ ነገር ሁሉ በሀገርና በህዝብ ላይ ሲፈፅም ቆይቷል፡፡ ዛሬ ከ23 አመ ታት በኋላ ሀገራችንና ህዝባችን ያልተዘፈቁበት የችግር ማጥ፤ ያልደረሰ የሀብትና የሰብአዊ ውድመት፤ ያልተፈፀመ የግፍና የሰቆቃ አይነት የለም፡፡ ወያኔ ይህን ሁሉ ሲፈፅም መሳሪያ አድርጎ ከተጠቀመባቸው ተቋማት ውስጥ ዋነኛዎቹ የመከላከያ፤ ፍርድ ቤትና የፖሊስና የደህንነት መሆናቸው ጥያቄ የለውም፡፡ የእነዚህ ተቋማት አባላት ከወያኔ ጥቃት ሰለባ ከመሆን ባይተርፉም የዚህን ወንጀለኛና ዘረኛ ቡድን እድሜ በአንድ ቀን በመጨመሩ ስራ ላይ ከፍተኛውን ድርሻ እንደያዙ ዛሬም መገኘታቸው አሌ የማይባል እውነት ነው፡፡ይህ ሲባል ግን በሀገርና በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ክህደት፤ ግፍና ሰቆቃ የሚያማቸው፤ መከራው መረራቸው፤ ብሶቱ ብሶታቸው የሆኑ አባላት የሉም ማለት እንዳልሆነ፤ ይልቁንም አብዛኛዎቹ የዚህ ስሌት ተካፋይ ስለመሆናቸው የሚጠራጠር የለም፡፡
ነገር ግን ከህዝብ አብራክ በወጡና ልጆቹን ሳይመግብ በከፈለው ታክስ በተደራጀ የመከላከያ፤ የፖሊስና የደህንነት ተቋማት ውስጥ የምትገኙ አብዛኛውና የግፉ ቀማሽ የሆናችሁ አባላት ዛሬ የምትገኙበት ሁኔታ እንደ አለፉት 23 አመታት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ፤ ከዛሬ ነገ የተሻለን ነገር ተስፋ በማድረግ፤ በግርግሩ ፍርፋሪ ሊወድቅልኝ ይችላል ከሚል ራስ ወዳድነት…… ወዘተ በመሳሰሉ በርካታ ምክንያቶች ለፍትህ፤ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ብሎም ለኢትዮጵያችን ቀጣይ ህልውና በሚደረጉ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በመቆም ብሎም የጥቂት ዘረ ኛች ስልጣንና ምቾት እድሜ ለማራዘም የተጓዛችሁበት መንገድ ብዙም ማስኬድ ከማያስችልበት፤ ይልቁንም ዛሬ ከሁለት መንታ መንገድ የ ደረሳችሁበትና ቆም ብሎም ማየትና ማገናዘብን ከሚጠይቅ ወቅት ላይ ትገኛላችሁ፡፡ አንዱ በዘረኝነት በትር እየተወቀጡ የወያኔ ሎሌ ሆኖ መቀጠል፤ ሌላው ከህዝብ አብራክ የተገኛችሁ ናችሁና ከህዝብ ወገን ተቀላቅሎ ሀገርን፤ ወገንንና ራስን ነፃ ለማውጣት መነሳት..
ለመከላከያ ሰራዊት፦ ላለፉት 23 አመታት ከጠመንጃ ተሸካሚነት ላለፈ ለማይፈልጉህ፤ ለአንተነትህ መለኪያው እውቀትህ፤ ችሎታ ህና አገልግሎትህ ሳይሆን የተገኘህበት ዘውግ መስፈሪያህ ለሆነበት ዘረኛ ስርአት፤ መቀየሪያ መለያ ልብስ ተነፍጎህ ቀዳዳ እየጣፍክ የልጆችህን የረሀብ ልቅሶ እያዳመጥክ በአንተ ትከሻ በዘረፉት ሀብት የገነቧቸውን ህንፃዎች ጠባቂ ላደረጉህ፤ ፍትህ ነፃነት ሲል በተራበ አንጀታቸውና በደ ከመ ድምፃቸው በጠየቁ ወገኖችህ ላይ ይህ ቀረ የማይባል ግፍ ሲያ ስፈፅምህ ለቆየው የወያኔ ዘረኛ ቡድን ዛሬም ተገቢውን ምላሽ የመስጠት እድሉ አለህ፡፡አልረፈደምና ተጠቀምበት!!!
የፖሊስ ሰራዊት አባላት፦ ፍትህ ላሉ ጥይትን፤ ነፃነት ላሉ የጭካኔ በትርን፤ ሀገሬን ላሉ ከጨለማ ዘብጥያ መወርወርን.. ዋነኛ ተግባርህ በሆነበት በዚህ ዘረኛና በወንጀል የተጨማለቀ ስርአት ውስጥ የቆየህበት ያለፉት 23 አመታት ለአንተም፤ ለቤተሰብህም፤ ለተገኘህበት ህብረ ተሰብ ሆነ ለሀገርህ የፈየደው አንዳች ነገር ያለመኖሩን ይበልጡኑ ከእሳት ወደ እረመጥ ከሆነው የወያኔ ጉዞ ራስህን አውጥተህ ከህዝባዊው ወገን የምትቀላቀልበት የመጨረሻው ሰአት መሆኑን ተገንዝበህ ምርጫህን ከወገንህ አድርግ፡፡ ለአንተም አልረፈደም!!
የደህንነት አባላት፦ ለሀገር ደህንነት ለህዝብ ሰላም ሲባል በህዝብ ሀብት በተደራጀ ተቋም ተጠቅመህ በሀገርህ ላይ ክህደትን፤ በወገ ንህ ላይ ግፍና ሰቆቃን ስትፈፅም መቆየትህ ከወንጀሎች ሁሉ የከፋ ወንጀል መሆኑን ተገንዝበህ ለፍትህ ለነ ፃነትና ለዲሞክራሲ ሲሉ በተነሱ ወገኖችህ ላይ ስትሰነዝር የቆየኸውን በትር በፍትህ በነፃነትና በዲሞክራሲ ላይ በቆሙት ዘ ረኛ አዛዦችህ ላይ የማሻው ጊዜ አሁን ነው፡፡ ስለ ዚህም ከህዝባዊው ወገን ተቀላቅለህ ህዝባዊ ወገንተኝነትህን የምታሳይበት ብሎም የበደልከውን የምትክስበት ጊዜውም እድሉ አለህና ተጠ ቀምበት፡፡ ላንተም አልረፈደም!!
በመጨረሻም ልጇን የምትጠላ እናት፤ ወገኑን የሚገፋ ህዝብ፤ ዜጎቹን የማይቀበል ሀገር የለምና ይህን በአስከፊነቱ ወደር የማይገኝለት የወያኔ ዘረኛ ስርአት ደግፎ ማቆየት ከማይቻልበት ይበልጡንም እንደ ትሪፖሊና ኢያሪኮ የግፈኞች ግንብ በህዝባዊ ሀይል ከሚገረሰስበት ከ መጨረሻዋ ደቂቃ ከመደረሱ በፊት ከእናታችሁ እቅፍ ከወገናችሁ መሀል ግቡ!! ተቀላቀሉ!! ቀኑ ሲቃረብ መውጫው ይጠባልና ጊዜ ሳታጠ ፉ ፈር ቀዳጅ ወንድሞቻችሁን መከተል ብልህነት ነው እንላለን!!!
የኢያሪኮም የጋዳፊም ግንብ ተንዷል፤ የወያኔም ይናዳል!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!