አርበኞች ግንቦት 7 የህወሃት አገዛዝ ካልተወገደ በቀር ላለፉት 25 አመታት በአገራችን የሰፈነው ዘረፈ ብዙ ችግሮች አይወገድም ብሎ ከሚያምንባቸው ምክንያቶች አንዱ ቋንቋንና ባህልን መስፈርት ባደረገ አከላለል ተፋቅሮና ተከባብሮ ይኖር የነበረ ህዝብ መካከል የተዘራው የመከፋፈልና የጠላትነት ስሜት ውሎ አድሮ ህዝባችንን ወደ ከፋ የርስ በርስ ጦርነት እንዳይወስዳት ለመከላከልና አገራችንንም ከመበታተን አደጋ ለመታደግ ነው።
ኢትዮጵያን እንደ አንድ አገር ህዝቦቿንም በታሪክና በመልካ ምድር ብቻ ሳይሆን በባህል፤ በቋንቋና በስነልቦና የተቆራኙ መሆናቸውን እውቅና መስጠት ለማይፈልግ ዘረኛው የህወሃት ቡድን ከትግራይ ውጪ ያለው ለምና በተፈጥሮ ሃብት የበለጸጉ ቦታዎች በሙሉ እንደ ባዕድ ሃብት የሚቆጠሩና የጠላት ይዞታዎች ናቸው። በዚህም እምነቱ የተነሳ የመንግሥት ሥልጣን በተቆጣጠረ ማግሥት ከትግራይ ጋር የሚዋሰኑ ለምና ድንግል የሆኑ መሬቶችን በከፍል ወይም በሙሉ ወደ ትግራይ ጠቅልሎአቸዋል። ከወራት በፊት ጎንደር ውስጥ ለተቀሰቀሰውና ወደ ጎጃም ለተዛመተው ህዝባዊ እምቢተኝነት ምክንያት የሆነው የወልቃይት ጠገዴ መሬት ላለፉት 25 አመታት የትግራይ አካል እንዲሆን የተደረገው በዚህ አይነት ያፈጠጠና ያገጠጠ የጠላትነት ስሜት ነው፡፡ ወልቃይት ጠገዴ ጎንደርን ከትግራይ ጋር ብቻ ሳይሆን ከኤርትራና ከሱዳን የሚያዋስን በታሪክ የጎንደር ግዛት አካል መሆኑን በንጉሱ ነገሥቱ ዘመን ትግራይን ለአመታት ያስተዳደሩት ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም በአደባባይ የመሰከሩት እውነታ ነው። ህወሃት አሁን የአማራ ክልል ብሎ ከሚጠራው የትግራይ አዋሳኝ ቦታዎች መሬት የቀማው ከጎንደር ብቻ አይደለም።
በወሎና በአፋር በኩልም እንዲሁ ኮረም፤ ራያ ፤ አበርጌሌ፤ ስሄሎ፤ ጎዶሌ፤ ታላክ፤ ሳውኔ ወይም ጊሊስ የተባሉ ወረዳዎች ተጠቃለው ትግራይ ውስጥ እንዲካለሉ ተደርገዋል። በህወሃት የአገዛዝ ዘመን ወደ ትግራይ እንዲካለሉ የተደረጉ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ቦታዎች በሙሉ በተፈጥሮ ለምነታቸው ወይም የተለያዩ የከበሩ ማዕድናትን በከርሰ ምድራቸው በመያዝ የሚታወቁ ናቸው። እነዚህን ለምና ድንግል ቦታዎች ቀምቶ ለዘመናት የኢትዮጵያ ታሪክ ማዕከል የሆነቺውን ትግራይ በቆዳ ስፋት ለማሳደግ ህወሃት ለምን እንደተጣደፈ ለማወቅ ሰፊና ረዥም ጥናት የሚጠይቅ እንቆቅልሽ የለውም።ኢትዮጵያችንን የመግዛት አቅሙ ከተመናመነና ከሥልጣን ከተባረረ በህገ መንግሥቱ ያሠፈረውን የመገንጠል መብት ተጠቅሞ ገና ከበረሃ የትግል ዘመኑ ጀምሮ በራዕዩ ያስቀመጣትን ታላቋን የትግራይ ሪፑብሊክ መሥርቶ የዘረፈውን ሃብትና ንብረት ለመብላት ዕድል የሚያገኝ ስለሚመስለው ነው። ከትውልድ መንደራቸው ውጪ ያለው ህዝብና አገር ለማይታያቸው ለነ ሳሞራ ይኑስ አይነቶቹ እብሪተኞች የታላቋ ትግራይ ምሥረታ ጉዳይ ህልም ሳይሆን በተፈለገበት ሰዓት መተግበር የሚቻል በእጅ ያለ እውነት ነው።
አርበኞች ግንቦት 7 የህወሃት መሪዎች የፈለጉትን ሁሉ በጉልበት ህዝብ ላይ መጫን የሚችሉ በአገራችን ጉዳይ ብቸኛ አድራጊና ፈጣሪ አድርገው እራሳቸውን እንዲመለከቱ ያስቻላቸው የኛ የህዝቦቿ ትዕግሥትና ዝም ባይነት ነው ብሎ ያምናል። ዛሬ ህዝባዊ እምቢተኝነትን የቀሰቀሰው የወልቃይት ጠገዴ መሬት በጉልበት ተቀምቶ ተወላጆቿ ለአመታት ሲፈናቀሉና በህወሃት ታጋዮችና ታማኝ አገልጋዮች የነዋሪዎች አሠፋፈር ገጽታዋ ሲቀየር ዝም ብለን መመልከታችን ከምን አይነት ችግር ውስጥ እንደከተተን ያልተረዳ የለም። እናም የወልቃይት ህዝብ ያነሳው የማንነት ጥያቄ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲያገኝና ከወሎና ከአፋር ያለውዴታቸው ወደ ትግራይ እንዲካለሉ የተደረጉ ነዋሪዎች ፍላጎት ምን እንደሆነ እንዲታወቅ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ወይም በተለምዶ ስሙ የወያኔ አገዛዝ በአስቸኳይ ማብቃት አለበት።
አርበኞች ግንቦት 7 የወልቃይት ህዝብ እየታገለለት ያለውን ዓላማ ከልብ የሚደግፍ ብቻ ሳይሆን ጥያቄው ምላሽ እንዲያገኝ ባለው አቅሙ ሁሉ ይፋለማል። ንቅናቄያችን በሚያካሂደው ሁለገብ ትግል አገራችን ውስጥ ፍትህ እኩልነትና ነጻነት የሠፈነበት የዲሞክራሲ ሥርዓት ሲገነባ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ህወሃት
አርበኞች ግንቦት 7 የወልቃይት ህዝብ እየታገለለት ያለውን ዓላማ ከልብ የሚደግፍ ብቻ ሳይሆን ጥያቄው ምላሽ እንዲያገኝ ባለው አቅሙ ሁሉ ይፋለማል። ንቅናቄያችን በሚያካሂደው ሁለገብ ትግል አገራችን ውስጥ ፍትህ እኩልነትና ነጻነት የሠፈነበት የዲሞክራሲ ሥርዓት ሲገነባ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ህወሃት
ከዘረጋው የዘር ልዩነቶችና ክፍፍሎች በላይ በዜግነታቸው ገዝፈው የሚታዩበት የበለጸገችና አንደነቷ የተከበረች አገር ባለቤት ይሆናሉ ብሎ ያምናል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !
No comments:
Post a Comment