Monday, 31 October 2016

Ethiopia: State of Emergency Risks New Abuses

OCTOBER 31, 2016 12:00AM EDT

Directive Codifies Vague, Overbroad Restrictions

(Nairobi) –An Ethiopian government directive under a state of emergency contains overly broad and vague provisions that risk triggering a human rights crisis, Human Rights Watch said today in a legal analysis. The government should promptly repeal or revise all elements of the directive that are contrary to international law. 

A woman cries as she attends a prayer session at Biftu Bole Lutheran Church during a prayer and candle ceremony for those who died in the town of Bishoftu during Ireecha, the thanksgiving festival for the Oromo people, Addis Ababa, Ethiopia, October 9, 20
A woman cries as she attends a prayer session at Biftu Bole Lutheran Church during a prayer and candle ceremony for those who died in the town of Bishoftu during Ireecha, the thanksgiving festival for the Oromo people, Addis Ababa, Ethiopia, October 9, 2016.

On October 9, 2016, the government announced a six-month state of emergencyfollowing the destruction of some government buildings and private property by demonstrators. Over the past year, security forces have killed hundreds of protesters and detained tens of thousands in two regions where there have been numerous protests over government policies.
“Ethiopia’s state of emergency bans nearly all speech that the government disagrees with anywhere in the country for at least six months,” said Felix Horne, senior Africa researcher at Human Rights Watch. “The state of emergency hands the army new sweeping powers to crack down on demonstrators, further limiting the space for peaceful dissent.”
Under the new state of emergency, the army can be deployed country-wide for at least six months. The implementing directive prescribes draconian restrictions on freedom of expression, association, and assembly that go far beyond what is permissible under international law and signal an increased militarized response to the situation. The directive effectively codifies many of the security forces’ abusive tactics that Human Rights Watch has documented since the protests began.
The directive includes far-reaching restrictions on sharing information on social media, watching diaspora television stations, and closing businesses as a gesture of protest, as well as curtailing opposition parties’ ability to communicate with the media. It specifically bans writing or sharing material via any platform that “could create misunderstanding between people or unrest.” 
It bans all protests without government permission and permits arrest without court order in “a place assigned by the command post until the end of the state of emergency.” It also permits “rehabilitation” – a euphemism for short-term detention often involving physical punishment. Many of these restrictions are country-wide and not limited to the two of Ethiopia’s nine regions where most of the unrest took place.
Under international law, during a state of emergency a government may only suspend certain rights to the extent permitted by the “exigencies of the situation.” Many of the measures, including the restrictions on freedom of expression, assembly, and association go far beyond what is permitted under international law.
The government reports that since the state of emergency began, 1,600 people have been arrested, including about 50 for closing their businesses. Human Rights Watch also has received unconfirmed reports of unlawful killings, mass arrests, and looting of houses and businesses by the security forces. There have been some armed clashes between security forces and unidentified groups. Mobile phone access to the internet has been blocked since October 5. Addis Standard, a monthly English language magazine and one of the few independent publications left in Ethiopia, announced on October 25 that it was halting publication of its print edition due to state-of-emergency restrictions.
Large-scale, and mainly peaceful anti-government protests have been sweeping through Oromia, Ethiopia’s largest region, since November 2015, and the Amhara region since July 2016. Ethiopian security forces have killed more than 500 people during protests over the last year. These protests occurred in a context of the near-total closure of political space.
Protesters have voiced a variety of concerns, including issues related to development, the lack of political space, the brutality of the security forces, and domination of economic and political affairs by people affiliated with the ruling party. The emergency measures send a strong and chilling message that rather than dealing with expressed grievances and ensuring accountability for violence by both government forces and protesters, the government will continue and probably escalate the militarized response.
On October 2, in Bishoftu, a town 40 kilometers southeast of the capital, Addis Ababa,tensions ignited at the annual Irreecha festival – an important Oromo cultural event that draws millions of people each year. Security forces confronted huge crowds with tear gas and fired shots and scores of people then died during a stampede. Since then, alleged demonstrators have damaged a number of government buildings and private businesses perceived to be close to the ruling party, setting some on fire.
The government has in part blamed human rights groups seeking to document violations of international law for the recent unrest. Human Rights Watch has repeatedly called for an independent and credible investigation into the security force response to the protests and to the deaths in Bishoftu.
“Many of the abuses committed by security forces since November 2015 have now been codified under the state of emergency,” Horne said. “Trying to use the legal cover of a state of emergency as a pretext for the widespread suspension of rights not only violates the government’s international legal obligations, but will exacerbate tensions and long-term grievances, and risks plunging Ethiopia into a greater crisis.” 

Human Rights Watch Statement to the European Parliament




Human Rights Situation in Ethiopia: Need for Stronger EU Action October 12, 2016

EUROPEAN PARLIAMENT
Committee on Development Subcommittee on Human Rights Joint Debate
Human Rights Situation in Ethiopia: Need for Stronger EU Action October 12, 2016
Testimony of Felix Horne, Senior Ethiopia/Eritrea Researcher, Human Rights Watch
Thank you for this opportunity to speak to parliament today at a critical time – both for Ethiopians and for the EU’s relationship with Ethiopia.
On October 2, in Bishoftu, Ethiopia, an unknown number of people, possibly hundreds, died during a stampede after security forces used teargas and gunfire to control a tense crowd at the annual Irreecha festival. Irreecha is an important cultural event for the Oromo ethnic group and draws millions of people each year to Bishoftu. The deaths have exacerbated pre-existing anger and frustrations throughout Oromia. Since that terrible day, there have been more anti-government protests and destruction of government buildings and properties. On Sunday, October 9, Ethiopia’s prime minister declared a six-month state of emergency.
The tragic events at Irreecha came after 11 months of anti-government protests in many parts of Oromia. Protesters initially were concerned that a proposed new master plan for the capital, Addis Ababa, would lead to further displacement of Oromo farmers, something that had happened with regularity in previous years. By the time the government announced the cancellation of the master plan in January, protester grievances had expanded to include condemnation of the brutality of the security forces’ response to the largely peaceful protests as well as decades of marginalization and human rights violations of the Oromo people.
In July, large protests also occurred in the Amhara region over complex questions of ethnic identity and the dominance in economic and political affairs of those with ties to the ruling party. The government’s brutality continued. In August in Amhara and Oromia regions, security forces killed over 100 people in one bloody weekend.
As protests have unfolded, Human Rights Watch interviewed several hundred individuals from more than 80 locations across Ethiopia. We were able to document how security forces used excessive and unnecessary lethal force and killed at least 500 protesters, and detained tens of thousands, often without charge. Released detainees told us of widespread mistreatment and torture.
At this point, Ethiopia is in the midst of its worst political and human rights crisis since the government of the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front came to power in 1991. Urgent action is needed before the crisis further deteriorates. While Ethiopian people bravely demand their human rights, concerned intergovernmental bodies and governments should press the Ethiopian government to respect basic rights and hold accountable those who violate them. The EU should be leading the way.
The recent events were a long time in the making. They are the outcome of the government’s systematic and calculated suppression of fundamental rights and freedoms that have closed political space and left few opportunities for the peaceful expression of dissent.


A man at a funeral holds up the portrait of Tesfu Tadese Biru, 32, a construction engineer who died during a stampede after police fired warning shots at an anti-government protest in Bishoftu during Irreecha, the thanksgiving festival of the Oromo people
A man at a funeral holds up the portrait of Tesfu Tadese Biru, 32, a construction engineer who died during a stampede after police fired warning shots at an anti-government protest in Bishoftu during Irreecha, the thanksgiving festival of the Oromo people, in Denkaka Kebele, Ethiopia, October 3, 2016
Ethiopia is among Africa’s leading jailors of journalists, and there is little space for independent journalists to operate. Ethiopian journalists and bloggers must choose between self-censorship, arrest, or living in exile. Websites critical of the government are blocked, radio stations are regularly jammed during sensitive times, and those providing information to journalists are often targeted for arrest. At various times in the last three months, the government has blocked the internet completely in some locations, restricted access to social media, and jammed radio transmissions including German broadcaster Deustche Welle. Bloggers have been arrested, and international journalists continue to report restrictions on access to the country. As we speak, the government is blocking access to the internet in many parts of Oromia.
Independent civil society groups face similar overwhelming obstruction. In 2009 the government passed the Charities and Societies Proclamation, which severely curtails the ability of nongovernmental organizations to work in areas of human rights and good governance. The anti-terrorism law, passed in 2009, has been used to crack down on peaceful expressions of dissent. Many opposition politicians, journalists, and activists have been convicted under that law and sentenced to prison terms. Courts have shown little independence in politically charged trials. There have also been serious restrictions on opposition political parties, which led to the ruling coalition in the May 2015 election to win 100 percent of the seats in the federal and regional parliaments, despite evident anti-government feelings in much of the country, as the protests indicate.
The authorities restrict public protests with routine denial of permits and arrests of real or perceived protest organizers. Fear of opposing the government has historically kept people from protesting, but that fear is rapidly dissipating. For those who do take to the streets, as thousands have done in hundreds of locations over the last year, brutal force from security forces is often the response. What avenues does this leave to express dissent, to question government policies or to voice concern over abusive practices?
The ruling party has dealt swiftly and aggressively with anyone who challenges the government narrative. For example, in March 2015, Pastor Omot Agwa was arrested in Addis Ababa with six other colleagues after trying to attend a food security workshop in Nairobi. Four of them were released, but Pastor Omot and two other colleagues have now been charged with terrorism, accused of belonging to a long inactive armed opposition group. Several months earlier, he had been the translator for the World Bank Inspection Panel complaint into the villagization program in western Ethiopia’s Gambella region. Human Rights Watch and others documented how the villagization program was associated with forced displacement of indigenous people leading to worsening food insecurity and several thousand people fleeing into neighboring countries. The program was funded, albeit indirectly, through the World Bank, the EU, and others. While it’s impossible to say whether the charges against him are linked to his role as translator, his case is typical of those that attempt to question the government’s policies, particularly on sensitive topics like development.
Human Rights Watch has also documented the Ethiopian government’s misuse of development assistance, including some EU funding, by ensuring that only those who are ruling party members or supporters receive the benefits of aid, including access to fertilizers, to seeds, to jobs, and to training opportunities. We first documented this in 2010, and there is little evidence that any action has been taken by the EU to monitor the negative and partisan impact of development assistance to Ethiopia. Concerns over the political capture of aid continue to come up regularly in our research. While EU development assistance makes an invaluable contribution to much-needed poverty reduction efforts in Ethiopia, it also has the unintended side effect of increasing the government’s repressive capacity, by contributing to the reliance that Ethiopians have on the government for their livelihoods and ultimately for their survival.
The EU has employed quiet diplomacy with Ethiopia in response to the dramatic deterioration in the human rights situation that has contributed to the current crisis. Turning a blind eye to the government’s repressive actions is undermining the EU’s priorities in the Horn of Africa and putting partnerships at risk, including in development assistance and migration. While the EU’s approach has been counterproductive in dealing with human rights, there have been some positive steps taken.
In January, this parliament passed the strongest resolution in many years on Ethiopia. Many hoped that this would lead to a shift in policy from the EU, but so far that hasn’t happened.
We therefore call on you today, in close coordination with your national parliament counterparts, to use every opportunity to press the EU and its member states to take strong and urgent action to try to prevent an irreversible and worsening crisis in Ethiopia. In the content of sweeping abuses of free expression, assembly and association, the recently announced state of emergency should prompt urgent questions regarding the government’s plans for implementation. Under international human rights law, governments need to ensure that any measures to restrict freedom of expression and association are “strictly required by the exigencies of the situation” and strictly proportionate to the aim pursued. Importantly, emergency powers must never be applied in a discriminatory manner, nor stigmatize people of a particular ethnicity, religion, or social group.
In the short term there are three critical actions for the EU:
  1. The EU should continue to push for an international investigation into the brutal crackdown in Amhara and Oromia regions since November 2015 and the recent deaths in Irreecha. The EU statement at the UN Human Rights Council session in September was a positive first step in pushing for this. The EU should also be pushing for Ethiopia to invite the UN special rapporteurs and other special procedures, 11 of whom have outstanding requests for access to the country. Ethiopia has not permitted a UN special rapporteur access since 2007, except for the special rapporteur for Eritrea.
  2. The EU should publicly call on Ethiopia to release of all those arbitrarily detained during the protests, including opposition leaders such as Bekele Gerba. Bekele was the deputy chairman for the Oromo Federalist Congress and a staunch advocate for non-violent approaches to address Oromo grievances. He was arrested in December 2015 and charged under the antiterrorism law. Being a peaceful and outspoken critic of the current government should not be defined as terrorism.
  3. The EU should publicly press for the lifting of government restrictions on the right to freedom of information and expression, including on the internet and social media, as well as the jamming of lawful broadcasts. The government should promptly release bloggers and journalists detained for the peaceful exercise of their free expression rights.

Thank you.


Thursday, 27 October 2016

ለኢትዮጵያ የመከላከያና ፓሊስሠራዊት አባላት የተደረገ ጥሪ



October 27, 2016
dr-berhanu-Nega
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር
ጥቅምት 15 2009 ዓ.ም.
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አባላት፤ የፌደራልና የክልል ፓሊስ አባላት፤ የአጋዚ ልዩ ኮማንዶ ጦር አባላትና ሌሎች የሥርዓቱ ታጣቂዎች። አገራችን በለውጥ ሂደት ውስጥ ባለችበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ለእናንተ ቀጥታ መልዕክት ማስተላለፍ የሚገባ ሆኖ ስላገኘሁት ይህንን አጭር መልዕክቴን በጥሞና እንድታዳምጡኝ፤ የሰማችሁ ላልሰሙት እንድታደርሱልኝ እጠይቃለሁ።
የአገር መከላከያ ሠራዊት አባል መሆን ከፍተኛ ክብር ያለው ሙያ እንደነበር የምታውቁት ነው። ለሀገር ዘብ መቆም መልካም ዜጎች ሁሉ የሚመኙት ተግባር ነው። አንድ ሰው ቃለ መሀላ ፈጽሞ የመከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም ከለበሰ በኋላ ተራ ዜጋ አይደለም። አገሪቷ በዜጎቿ ማየት የምትፈልጋቸውን መልካም እሴቶችን ሁሉ በወታደሮቿ ማየት ትሻለች፤ ለሕዝብ ተቆርቋሪነት፣ ሀገር ወዳድነት፣ ፍትሀዊነት፣ ጀግንነት፣ ታማኝነት በወታደሮቿ ማየት ትሻለች። ለዚህም ነው በብዙ አገሮች ውስጥ ያሉ ሕፃናት “ስታድጉ ምን መሆን ትፈልጋላችሁ?” ሲባሉ ከሚሰጧቸው መልሶች ግንባር ቀደሙ “ወታደር” የሚሆነው። በሀገራችንም ዘመናዊ ጦር ከመደራጀቱ በፊት አያት ቅድም አያቶቻችን ራሳቸውን በወታደርነት አሰልጥነው፤ ወራሪ ሲመጣ በየጎበዝ አለቆቻቸው እየተቧደኑ ዘመናዊ ጦሮችን ሳይቀር ተዋግተው በማሸነፍ የአገራችንን ሉዓላዊነት አቆይተውልናል። ዘመናዊ ጦር ከተደራጀ ወዲህም እስከ ህወሓት አገዛዝ የነበሩ አስተዳደሮች ብዙ እንከኖች ቢኖርባቸውም እንኳን የመከላከያ ሠራዊትን የአገር መከላከያ ሠራዊት አድርገውት ቆይተዋል። የሠራዊቱን ክብርና ሞገስ ለመጠበቅም የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል። ይህ ጥረት ግን በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ሙሉ በሙሉ ተቀልብሷል።
የፓሊስ ሠራዊት ሥራ ለሕዝብ የዕለት ተዕለት ኑሮ ዋስትና መስጠት ነው። ዜጎች በሰላም ከቤታቸው ወጥተው በሰላም የመመለሳቸው ዋስትና ከወገናቸው ከፓሊስ ሊያገኙ ይሻሉ። ሕዝባዊ ፓሊስ የወሮበሎች፣ የሌቦችና የማጅራት መቺዎች ጠር፤ የድሆችና ደካሞች አጋር ነው። ሕዝባዊ ፓሊስ የፍትህ ጠበቃ ነው። እንዲህ ዓይነቱን ፓሊስ በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ማየት አልቻልንም።
የህወሓት አገዛዝ የተከበሩትን የውትድርናና የፓሊስ ሙያዎችን አዋርዶ ለሀገርና ሕዝብ ደህንነት ሳይሆን ለአንድ ቡድን ሥልጣን መከበር የቆሙ ኃይሎች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። አሁን ያለው የኢትዮጵያ መከላከያና የፓሊስ ሠራዊትን ስናስብ በአዕምሮዓችን የሚመጡት የሚከተሉት ሀቆች ናቸው።
የጦር ሠራዊቱ፣ ብቃትና ዕውቀት እንዲሁም የሀገር ፍቅር ባላቸው ጄኔራሎችና የጦር መኮንኖች የሚመራ ሳይሆን በተቃራኒው ምንም ዓይነት ወታደራዊ ትምህርት በሌላቸው ከሽምቅ ውጊያ ቡድን አዛዥነት ወደ ዘመናዊና መደበኛ ጦር አዛዥነት በድንገት ያደጉ፤ ራሳቸውን ከዘመናዊ ሠራዊት አደረጃጀትና አመራር ጋር ያላዋሃዱ፤ ከሀገር ጥቅም ይልቅ የራሳቸው የግል ጥቅም የሚበልጥባቸው፤ የማይጠረቁ ስግብግቦች፤ ታማኝነታቸው ለሀገር ሳይሆን አባል ለሆኑባቸው ፓርቲዎች የሆኑ ግለሰቦች ናቸው።
ዛሬ ያለው የኢትዮጵያ ሠራዊት በወያኔየስለላ መረብ ተተብትቦ ወይም በእነርሱ ቋንቋ “ተጠርንፎ” በግድ የተያዘ እንደቁም እስረኛ ሊቆጠር የሚችል በከፍተኛ ምሬትና በደል ውስጥ የሚገኝ ሠራዊት መሆኑን እናውቃለን። የሠራዊቱን ክብር በሚነካ፤ ስብዕናን በሚያዋርዱ ዘለፋዎችና በግምገማናላው እንዲዞር፣ ሞራሉ እንዲላሽቅ የተደረገ ሠራዊት ነው። የህወሓት ጄኔራሎችና ካድሬዎች የሚያወርዱበት ዘለፋና ስድብ የዕለትተዕለት ቀለቡ የሆነ፤ ሞራሉም የላሸቀ ሠራዊት ነው።
አንድ ተራ የህወሓት ካድሬ ወይንም የበታች ሹም የዘረኛው ሥርዓት በሚሰጠው ልዩ ግምትና ስልጣን ከሌሎች ብሔሮችና ብሔረሰቦች የመጡ በማዕረግም በዕውቀትም የበላይ የሆኑንትን ሻለቆችና ኮሎኔሎችን የሚያንጓጥጡበት፣ የሚያዋርዱበትና የሚያሸማቅቁበት፤ አመራሩበወታደራዊእዝና ወታደራዊ ስነምግባር መሠረት የሚመራሳይሆንበብሄር የበላይነት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ዲሲፕሊንና ውህደት የሌለው ሠራዊት ነው። በብሔር የተከፋፈለ በመሆኑ በውስጡ ያለው ጓዳዊ ስሜት በእጅጉ የላላ ሠራዊት ነው።
የፍትህ ጥያቄየሚያነሱ የሠራዊቱ አባላት ለህወሓት ካድሬዎች ስላልጣማቸው ብቻ ያለ ወታደራዊ ህግና አግባብበ አንድ የህወሓት ካድሬ ትዕዛዝ ብቻ ደብዛቸው ሊጠፋ እንደሚችል ስለሚያውቁበከፍተኛ የፍርሃት እና በራሳቸው ላይ እምነት እንዲያጡ የተደረጉ ናቸው።
ይህ ሠራዊት ለወያኔ ጠባብ አጀንዳ በየግንባሩ ዘመቻ እንዲሄድ ሲገደድና ሲማገድ የህወሓት ካድሬዎችና ጄኔራሎች የሕይወትና የደም ግብር እንዳይከፍሉ ከአደጋ እንዲጠበቁ የሚደረግበት ዘዴና ስልት የተቀየሰበት የዘረኝነትና የአድሎ ሥርዓት ውስጥ የተጣደ ሠራዊት ነው።
ሠራዊቱ ሲቆስል፣ ደሙን ሲያፈስ፣ ፈንጂ ሲረግጥ፣ ሕይወቱን ሲገብር የህወሃትቅምጥል ጄኔራሎችና መኮንኖች ቅጥባጣ አስረሽ ምችው በየከተማው እንደሚባልጉ የሚያውቅ ሠራዊት ነው።
ጫማና የደንብ ልብስ ከዚያም አልፎ የሚበላዉን ምግብ ከሚከፈለዉ ትንሽዋ ደሞዙ ላይ እየተቆረጠበት እናት አባቱን ለመጦር እና ልጆችን ለማሳደግፈተና ውስጥ የሚገባ፤ ለበርካታ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የተዳረገ ሠራዊት ሆኖ ሳለ በአንፃሩ የህወሓት ጄኔራሎችና ከፍተኛ መኮንኖች በኮንትሮ ባንድ ንግድና በዘረፋ ሲከብሩ፤ ንግዳቸውን በግላጭ ሲያጧጥፉ፤ ባለብዙ ህንፃዎች ባለቤቶች በመሆን በዘመድ አዝማዶቻቸዉ ስም ጭምርሀብት ሲያካብቱ፤ የህዝቡን መሬት ያላግባብ ሲቀሙና ሲቀራመቱ፤ በሰላም አስከባሪ ኃይል ስም በተባበሩት መንግስታት በየሀገሩ እየተመደቡ በወር እስከ 25,000 የአሜሪካ ዶላር ተከፋይ ሆነው ሲቀማጠሉ በሚገባ እያስተዋለ የሚገኝ ሠራዊት ነው።
በተጨማሪም እንደው ድንገት ለምርጦቹ የሚደርሰው የሰላም ማስከበር ተሳትፎ ግዳጅ ሲሄድ ሊያግኝ ከሚገባው የኪስ ገንዘብ ላይ አብዛኛውን ለራሳቸዉ ጥቅም በማዋል እና ሀገሪቷ ከዚህ ከሰላም ማስከበር ልታገኝ የሚገባትን ጥቅማጥቅም በራሳቸዉ በህዉሃት ጄኔራሎችና አመራሮች የግል ኪስ በማስገባት ራሳቸውንና ዘመድ አዝማዶቻቸዉን እያበለጸጉበት ይገኛሉ።
ሠራዊቱ ከትንሿ ደመወዙ ለመለስፋዉንዴሽን፣ ለአባይግድብግንባታ፣ ለተለያዩ የተሃድሶ መዋጭዎች፣ ለአመት በአል ድግሶች መዋጮ እንዲፈል የሚገደድ ምስኪን ነው። አላዋጣም፤ ገንዘብ የለኝም ብሎ ቢል ጸረ ሰላም ወይንም ሌላ ስም ተሰጥቶት ለተለያዩ አይነት ቅጣቶች ይዳረጋል። ሕገ መንግሥቱ በግልጽ ቢከለክልም እንኳን በሰራዊቱ ውስጥ የድብቅ የሕወሀት አደረጃጀት ፈጥሮ በሰራዊቱ ውስጥ የልጅና የእንጀራ ልጅ ስሜት ፈጥሮ የሚከፋፍል እኩይ ኃይል ነው ይህን ሰራዊት የተቆጣጠረው።
በፌዴራል ፖሊስና በአጋዚ ልዩ ኮማንዶ ውስጥ ነግሶ የሚታየው ሁኔታ ከላይ ከዘረዘርናቸው የተለየ አይደለም። ሠራዊቱ የአዛዦቹ አገልጋይ በመሆን የበይ ተመልካች የሆነበት መዋቅር ነው። ሞት፣ የአካል መጉደልና ድህነት ለሠራዊቱ አባላት፤ በአንፃሩ ምቾችና ድሎት ግን ለአዛዦቹ እንዲሆን ታቅዶ የተደራጀ ሠራዊት ነው።
ኢትዮጵያ በየዘመኑ እያደገና እየዘመነ የመጣ ሞያን፣ ችሎታንና ወታደራዊ ሳይንስን አዳብሎ የታጠቀና ከተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የተዉጣጣ ዘመናዊ የአገር መከላከያ ተቋም የነበራት አገር ነበረች። ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች አዲስ አበባን ሲቆጣጠሩ ይህንን ዘመናዊ የአገርና የወገን መከታ የሆነዉን ሠራዊት አፍርሰዉና ለእናት አገሩ የተዋደቀዉን ሠራዊት ለማኝ አድርገዉት ነዉ በህወሓት የበላይነት የሚመራ አዲስ የመከላከያ ሠራዊት የገነቡት። ይህ ህወሓት የገነባዉ ሠራዊት በአደረጃጀቱም ሆነ በቀን ከቀን ስራዉ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅምና ፍላጎት ጋር በምንም መልኩ የተገናኘ አይደለም። ይህንን መከላከያ ሠራዊት የፈጠረዉ ህወሓት፣ የሚመራዉና የሚቆጣጠረዉ ህወሓት፤ ሠራዊቱ በሚወስዳቸዉ እርምጃዎች ሁሉ ዋነኛዉ ተጠቃሚም የህወሓት/ኢህአዴግ ጥቂትዘራፊ መሪዎች ብቻ ነዉ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሆይ!
ህወሓት/ኢህአዴግ ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቿ የደገሰዉ የጥፋት ተልዕኮ ካልተሳካ አንተን እንደለመደዉ ሜዳ ላይ በትኖና ባንተ ትከሻ ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ የዘረፈዉን የአገር ሀብትና ንብረት ይዞ አገር ለቅቆ እንደሚጠፋ ምንም ጥርጥር የለዉም። ለዚህ የሽሽት ጉዞዉ ደግሞ ለረጂም ግዜ ተዘጋጅቷል። በቢልዮኖ ዶላሮች የሚቆጠር ሀብት በውጭ ሀገሮች አስቀምጧል። በዚህሠራዊት ዉስጥ የአገሩን ዳር ድንበር የጠበቀ እየመሰለዉ የህወሓት መሳሪያ ሆኖ የራሱን ወገኖች ከሚገድለዉ ኢትዮጵያዊ ዉስጥ ከአስር ዘጠኙ የህወሓት/ኢህአዴግን መወገድ የሚናፍቅ ዜጋ ነዉ። ችግሩ ይህ ሠራዊት ልክ እንደ ሲቪል ወግኖቹ በዘርና በቋንቋ ተለያይቶ የተደራጀ በመሆኑ እርስ በርስ ተገናኝቶ መነጋገርና መወያየት አለመቻሉ ነው።
ይህ ሙሉ በሙሉ በህወሓት ቁጥጥር ስር የሚገኘዉ ሠራዊት ባለፉት ሀያ አምስት ዓመታት የወሰዳቸዉን ፀረ ሕዝብና ፀረ አገር እርምጃዎች አንድ በአንድ ስንመለከት ይህ ተቋም በሚወስዳቸዉ እርምጃዎች የሚጎዳዉ የሠራዊቱ ጡንቻ የሚያርፍበትን የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የሠራዊቱ አባላት እራሳቸዉም የራሳቸዉ እርምጃ ሰለባዎች ናቸዉ። ታድያ ለምንድነዉ ይህ ሠራዊት ከ25 አመት በላይ እሱን እራሱን፣ እናቱን፣ አባቱን፣ እህቱንና ወንድሙን የሚጎዳ እርምጃ የሚወስደዉ? የአገርን ዳር ድንበር ከባዕዳን ወራሪዎች ለመከላከል የተደራጀና የታጠቀ መከላከያ ሠራዊት ለአዛዦቹ መታዘዝ እንዳለበት ከማንም የተሰወረ አይደለም። ሆኖም አንድ የአገሬን አንድነትና የወገኖቼን ደህንነት እጠብቃለሁ ብሎ ቃለ መሃላ የፈጸመ የመከላከያ ሠራዊት አባል ደህንነቱን መጠበቅ የሚገባዉን ሕዝብ በነጋና በጠባ ግደል ተብሎ ትዕዛዝ ሲሰጠዉ ትዕዛዙን ከመፈጸሙ በፊት ማንን ነዉ የምገድለዉ ለምንስ ነዉ የምገድለዉ ብሎ እራሱን መጠየቅ አለበት።
ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘመናዊ የባርነት አዋጅ ታዉጆበታል። ህወሓት ይህንን አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ የሚሯሯጠዉ አንተን ከሕዝብ አብራክ የወጣኸዉን የሕዝብ ልጅ በመጠቀም ነዉ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ ሀይል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነትና እኩልነት ይዋጋል እንጂ እሱንና ወገኖቹን የህወሓት ባሪያ የሚያደርግን አዋጅ አያስፈጽምም። ይህ አገርንና ሕዝብን ለመጠበቅ ህገ መንግስታዊ አደራ የተሸከመ ሠራዊት የታጠቀዉን መሳሪያ ማዞር ያለበት በወንድሞቹና በእህቶቹ ላይ ሳይሆን ሠራዊቱንና ኢትዮጵያን በትኖ ለመጥፋት ዝግጅት እያደረገ ባለዉ በጠላቱ በህወሓት ጥቂት ዘራፊ የሲቪልና ወታደራዊ መሪዎችላይ ነዉ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ሆይ!
የኛ ፍላጎት ፍትህ፣ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፉኑባት ኢትዮጵያ እዉን ሆና ማየት ነዉ። እርግጠኞች ነን የእናንተም ፍላጎት ከዚህ የተለየ አይደለም። እነዚህን እኛም አናንተም የምንፈልጋቸዉን እሴቶች ቀምቶን ሁለታችንንም እንደ ባሪያ ረግጦ የሚገዛን ዘረኛዉ የህወሓት/ኢህአዴግሥርዓት ነዉ። እናንተና እኛ ይህንን አንድ ላይ የሚረግጠንን ሥርዓት ጎን ለጎን ቆመን በጋራ መታገል ነዉ ያለብን እንጂ እርስ በርስ መተላለቅ የለብንም። ደግሞም ሁለት ፍትህ፣ ነፃነትና እኩልነት የናፈቃቸዉ ወንድማማቾች ነፃነታቸውን ቀምቶ የሚረግጣቸዉን ኃይል አንድ ላይ ሆነዉ ይፋለሙታል እንጂ እርስ በርስ አይተላለቁም። በዚህ የነጻነት ትግል ላይ የምንሳተፍ ወገኖችህ ወንድሞቻችንን በመግደል አናንተም እኛን ወንድሞቻችሁን በመግደል የሚገኝ ነገር ቢኖር ባርነትና የአገር አንድነት መፍረስ ብቻ ነዉ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አገሩንና ወገኖቹን የሚጠብቅ ኃይል ነዉ እንጂ ጠላቶቹ ግደል የሚል ትዕዛዝ በሰጡት ቁጥር በገዛ ወገኖቹ ላይ የሚተኩስ ኃይል አይደለም።
አንተ የኢትዮጵያ መለዮ ለባሽ ሆይ!
ዛሬ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በኮንሶ፣ በቤኒሻንጉልና ኦጋዴን ዉስጥ እህቶችህ “ወንድም ጋሼ” ድረስልን ብለዉ እየተጣሩ ነዉ፤ ወንድሞችህ “ጋሽዬ” አድነን እያሉህ ነዉ፤ አባትህና እናትህ “ልጄ አንተ እያለህ እንዴት እንዲህ ይደረጋል?” ብለዉ እየጮሁ ነዉ። መቼ ነዉ የምትደርስላቸዉ? መቼ ነዉ ከእስርና ከጥይት የምታድናቸዉ? መቼ ነዉ ተስፋ የምትሆናቸዉ?
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና ፓሊስ አባላት ሆይ!
የህወሓት አገዛዝ ልትጠብቀው ከሚገባህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ደም እያቃባህ ነው፤ የውጭ ወራሪን ሳይሆን ፍትህ የናፈቀውን የገዛ ራስህን ወገን እንድትወጋ እያደረጉህ ነው፤ አገርህ ለጥቂቶች ብቻ የምትታለብ ጥገት ሆና ለማቆየት አንተን በመሣሪያነት እየተጠቀሙብህ ነው። የነፃነት ኃይሎች ትግል የገጠሙት ከህወሓት ዘራፊ ወታደራዊና ሲቪል መሪዎች ጋር እንጂ ከአንተ ጋር አይደለም። እነሱ ሁኔታው አላምር ሲል መሸሻ አዘጋጅተዋል፤ እድሜ ልካቸውን በልተው የማይጨርሱት ሀብት በውጭ አገራት አከማችተዋል። ያ ቀን ከመምጣቱ በፊት ግን አንተ የገዛ ወገንህን ገድለህ እንድትጨርስ፤ አሊያም በገዛ ወገንህ ተገድለህ እንድትጠፋ ይሻሉ። እንደምታውቀው በገባንበት ትግል አንተ ብቻ ተኳሽ፤ አንተ ብቻ ገዳይ አይደለህም። የነፃነት ኃይሎች ሊገላቸው የመጣን ኃይል ከመግደል አይመለሱም። በአሁን ሰዓት እንኳን ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሠራዊቱ አባላት በነፃነት ኃይሎች ተጋድሎ መውደቃቸውን ታውቃለህ። ይህ መሆኑ ያሳዝነናል፤ ልትገድለን ስትመጣ ግን ባዶ እጃችንን አንጠብቅህም። እርስ በርስ የሚያጋድለን የህወሓት አገዛዝ ማብቃት አለበት። አንተ የዚህን እኩይ ስርዓት ትዕዛዝ አልቀበልም፤ ከድንበር መጠበቅ ውጭ የሀገሬን ህዝብ አልገልም ያልክ ቀን፤ ይህ ጦርነት ይቆማል። እንደልባቸው የሚያዙት ጦር እንደሌለ ሲያውቁ የሀገሪቱን የፖለቲካ ችግር በጉልበት ሳይሆን በፖለቲካዊ መንገድ ለመፍታት ይገደዳሉ። ለነጻነትና ለእኩልነት እየተዋደቁ ያሉት ወገኖችህ ልክ እንዳንተ ይህ በአንድ ሀገር ህዝቦች መሀከል የሚደረግ ጦርነት እንዲቆም ይፈልጋሉ። በረሀ የገቡት ገበሬ ዘመዶችህ በሰላም አርሰው ልጆቻቸውን አሳድገው ጥሩ ዜጋ ማድረግ ይፈልጋሉ። መገደል፤ መታሰርና መሰቃየት ሰልችቶት በረሃ የገባው ወጣት ሀገሩ ሰላም ሆና፤ የነጻነት አየር እየተነፈሰ ትምህርቱን በነጻ አዕምሮ ተምሮ ለሀገሩ በጉልበቱና በእውቀቱ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚፈልግ እንጂ የጦርነት አባዜ ኖሮበት አይደለም በረሃ የወረደው። ስለዚህ ይህን ጦርነት ማስቆም የምትችለው አንተ ነህ። ይህን የምታደርገው ደግሞ እንዳንተ ሰላምና ነጻነት የሚፈልገውን ወገንህን በመግደል ሳይሆን አንተንም መላው ህዝቡንም አዋርደው መግዛት የሚፈልጉትን ጥቂት ዘራፊዎች እምቢ ማለት ስትችል ነው።
ከዛሬ ጀምሮ የተገኘውን ሁሉ አጋጣሚ ተጠቅመህ ሥርዓቱን በመክዳት የነፃነት ኃይሎችን ተቀላቀል። የሕዝብ ወገኖችን እንድትወጋ ስትታዘዝ እንድትወጋቸው ከተላክባቸው የነጻነትና የእኩልነት ታጋዮች ጋር ተቀላቀል። በአገኘኅው አጋጣሚ ሁሉ በግልም በቡድን መሣሪያህን ወደጥጋበኛ ህወሓት አዛዦችህ አዙር።
በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ከነፃነት ኃይሎች ጋር የሚቀላቀሉ የሠራዊቱ አባላት የክብር አቀባበል ይደረጋል። ሠራዊቱን የሚቀበሉ የሚያስተናግዱ፣ የሚያቋቁሙ ቡድኖችን በየቦታው አደራጅተናል። ሕዝብ በህወሓት አገዛዝ ላይ እንጂ በአንተ በሠራዊቱ አባል ላይ የያዘው ቂም የለም። እንዲያውም አንተ ራስህ ትግሉን እንድትቀላቀል ይፈልጋል። በሕዝብና በአገር ላይ በደል ሲፈጽም የኖረው የህወሓት አገዛዝ ፍፃሜለማፍጠን በሚደረገው ትግል የአንተ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።
በኢትዮጵያችን ውስጥ እንዲኖር የምንፈልገው ሠራዊት ታማኝነቱ ለፓርቲ ሳይሆን ለሀገር የሆነ፤ ድንበሯን ከጠላት የሚከላከል፤ በሀገር ፍቅር ስሜት የነደደ፤ ሕዝብ የሚወደውና የሚያከብረው ሠራዊት ነው። ይህ ሠራዊት የሚገነባው በአንተው ነው። የህወሓት ወንበዴዎች ከዚህ በፊት እንዳደረጉት ሠራዊቱን የመበተን ዓላማም ሆነ ፍላጎት ያላቸው የነፃነት ኃይሎች የሉም። እነኝህ ብልሹ መሪዎቹ ተወግደውለት መዋቅሩ እንደተጠበቀ፤ ሹመትና የደሞዝ ጭማሪ በችሎታና ባደረገው አስተዋጽኦ ብቻ እንጂ ለአንድ ድርጅት ባለው ድጋፍ ወይም በዘውግ ማንነቱ ያልሆነ፤ ሙያውና ተጋድሎው ሀገሩን ከጠላት መጠበቅና የህዝቡን ደህንነት ማረጋገጥ የሆነ፤ በተልዕኮ ላይ ቢሰዋ ህዝቡ እንደጀግና የሚቀብረው፤ አካለ ስንኩል ቢሆን ህዝቡ በአክብሮት እስከ እድሜ ልኩ የሚጦረው፤ መለዮ ለብሶ በህዝቡ ውስጥ ሲገኝ ወጣቱ እንደሱ ለመሆን የሚመኘው አኩሪ የኢትዮጵያ ሠራዊት ሆኖ እንዲቀጥል ነው ፍላጎታችን። ይህ ምኞት እንዲሳካ ግን ዛሬ የምትፈጽፈው ተግባር ወሳኝ ነው።
ውድ የአገሬ መለዮ ለባሾች፤
ለዴሞክራሲ ሲሉ እየታገሉ በሞቱትና አሁንም በሚታገሉት የሕዝብ ኃይሎች ስም የማቀርብላችሁን ጥሪ አድምጡኝ። ነፃ ሊያወጣችሁ እየታገለ ባለ ሕዝብ ላይ ፈጽሞ አትተኩሱ። ሕዝብ ላይ መተኮስ ማለት፤ የነፃነት ታጋዮች ላይ መተኮስ ማለት፤ በገዛ ራሳችሁ ላይ መተኮስ ማለት እንደሆነ እወቁ። ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው እንዴት በገዛ ራሱ ጭንቅላት ላይ ይተኩሳል? የእስከዛሬው በቅቶን ከእንግዲህ መንገዳችሁን አስተካክሉ። ከቻላችሁ ይህን የባርነት አዋጅ ለማስፈጸም ስንል ከሕዝብ ጋር አንዋጋም ብላችሁ በኅብረት ቆማችሁ ይህንን ጦርነት አስቁማችሁ ሀገሪቱን ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ሽግግር ለመውሰድ ታገሉ። ይህን ካልቻላችሁ የሕዝብን ትግል ተቀላቀሉ። በግልም ይሁን በቡድን መሠሪ የህወሓት ጄኔራሎችና አለቆቻችሁን በማስወገድ የጀግንነት ታሪክ ሥሩ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና ፓሊስ አባላት ሆይ!
የኛ ፍላጎት ፍትህ፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፈነባት ኢትዮጵያ እዉን ሆና ማየት ነዉ። የእናንተም ፍላጎት ከዚህ የተለየ አይደለም። ከሕዝብ ጎን ቁሙ፤ ሕዝብ በጎናችሁ ይቆማል።
ኢትዮጵያ አገራችን በክብር ለዘላለም ትኑር!

Saturday, 22 October 2016

የወያኔ የመጨረሻው እስትንፋስ፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የታወጀ የዘመናዊ ባርነት አዋጅ! – ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተላለፉት መለዕክት



October 22, 2016
dr-berhanu-Negaውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፤
በሀገራችን ኢትዮጵያ የተከሰተው ስር የሰደደ የፖለቲካ ቀውስ በሰለጠነ የውይይትና የድርድር መንገድ እንዲፈታ ለሀገር ደህንነት ከሚያስቡ የአገር ሽማግሌዎችም ሆነ ከተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ወዳጆቹ ጭምር የቀረበለትንና የሚቀርብለትን ጥሪ አሌ ብሎ፤ ይህ እኩይ የጥቂት ሽፍቶች ሥርዓት ለ25 ዓመታት ሲያካሄድ የቆየውን የሕዝብና የሀገር ሀብት ዝርፊያ ከማቆም ይልቅ “ሀገሪቷን መዝረፍ ካልቻልኩ አቃጥያት እጠፋለሁ” ብሎ የመጨረሻው የሆነውን የጥፋት መንገድ ከሰሞኑ “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ” በሚል ስያሜ ባወጀው “የባርነት አዋጅ” ለሁሉም ግልጽ አድርጓል። ይህንን የወያኔ የዘራፊዎች ቡድን ለረጅም ጊዜ በቅርብ ስንከታተልና በተግባርም ስንፈትነው ለቆየነው የነፃነት ኃይሎች ይህ እርምጃው ስንጠብቀውና ስንዘጋጅበት የነበረ ስለሆነ በእውነቱ በፍጹም አልገረመንም። ትንሽም ቢሆን ያስገረመን ይህንን የመጨረሻ ጥይቱን እንደዚህ በቶሎ መጠቀሙ ነው። የመጨረሻ ጥይቱ ነው የምንለው ከዚህ በኋላ ሊጠቀምበት የሚችለው ምንም ሌላ መሳሪያ እንደሌለው ስለምናውቅ ነው።
በእርግጥ በዚህ አዋጅ ውስጥ አገዛዙ ሊወስዳቸው ያሰባቸው እርምጃዎች አብዛኛዎቹ ከዚህ በፊትም እራሳቸው ካወጧቸው ህጎችና ህገመንግስቱም ውጪ ያለምንም ከልካይ ሲተገብሯቸው የነበሩ እርምጃዎች ናቸው። የመንግሥትን ስልጣን ከተቆጣጠሩ ጀምሮ በስልጣናቸው በመጣ ጉዳይ አንድም ጊዜ ሕጋቸውን አክብረው አያውቁም። ያለሕግ ሲያስሩ፤ ያለሕግ ሲገድሉ፤ ያለሕግ የመገናኛ ብዙሀንን ሲዘጉና ሲያፍኑ፤ ከሕግ ውጪ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን ሲያፈርሱና ያላፈረሱትን ደግሞ እራሳቸው የመረጡላቸውን መሪዎች ሲያስቀምጡ ነው እስካሁን የዘለቁት። ከዚህ አንጻር ይህ አዋጅ ቀድሞውንም ኢሕጋዊ የሆነ ስራቸውን ይበልጥ ኢሕጋዊ በሆነና አይን ባወጣ መንገድ፤ ለፈረንጆች ማባበያ ያጠለቁትን የሕጋዊነት ጭምብል አውልቀው እርቃናቸውን ከመታየታቸው ባሻገር ብዙ አዲስ ነገር የለውም። ይህን አዋጅ ከዚህ በፊት ሲያደርጉት ከነበረው በተለየ እንድንመለከተው የሚያደርገን ከአዋጁ እናገኝበታለን ብለው የሚያስቡትና በሕዝባችን ላይ ሊያሳርፉት የፈለጉት፤ ከተሳካላቸው ዘላቂ አንድምታ ያለው የተገዢነት ስነ ልቦና ውስጥ ሕዝቡ እንዲገባ የሚያደርጉት ሙከራ ላይ ነው።
ምንም በማያሻማ መልኩ ይህ አዋጅ ተግባራዊ እየሆነ ባለበት ሁኔታ ምንም አይነት የፖለቲካ መፍትሄ ሊኖርም ሊሞከርም የማይችል እንደሆነ ግልጽ ሆኗል። የህወሓት አገዛዝ ከጉልበት ውጭ ምንም ሌላ መንገድ የማያውቅ አጥፊ ኃይል እንደሆነ ለወዳጅም ለጠላትም ያሳወቀበት አዋጅ ነው። ይህን አዋጅ ሲያውጁ ሰው ሆኖ መኖርን የናፈቀውና ካሁን በኋላ ያለነፃነት በፍጹም አልኖርም ብሎ ፍርሀትን በሚገርም ጀግንነት አሸንፎ ውድ ሕይወቱን እየከፈለና እየታገለ ያለውን፤ ከሞላ ጎደል መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ እንደገና በፍርሀት ቆፈን ውስጥ መልሼ ከትቼ ከቀድሞውም የባሰ ባርነት ውስጥ ዘፍቄ እገዛዋለሁ ብሎ አምኖ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ካሁን በኋላ ባርነትን የሚሸከምበት ምንም ጫንቃ የለውም። በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ሕዝብ በፍጹም በፍጹም ተመልሶ የባርነት ሕይወት ውስጥ ሊኖር አይፈቅድም። ስለዚህ ከዚህ በኋላ የፍትህና የነፃነት ኃይሎች ዋና ተግባር ያላቸውን አቅም ሁሉ አስተባብረውና ነፃነት የራበውንና የጠማውን ሕዝባቸውን ከጎናቸው አሰልፈው፤ ጊዜውና ሁኔታው የሚፈቅደውን ተለዋዋጭና ተለማጭ የትግል ስልት እየተጠቀሙ ይህ አዋጅ በፍጹም ተግባራዊ እንዳይሆንና እንዳይሳካ ማድረግ ነው። ይህን የባርነት አዋጅ ለማስፈጸም በመሪነትና በዋና አስፈጻሚነት የሚንቀሳቀሱት ኃይሎች፤ ይህ የባርነት አዋጅ በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ እንዲተገበርና እንዲሳካ ለማድረግ የሚሞክሩ ወይንም ከዚህ ዘራፊ ሥርዓት ጋር በጥቅም ተሳስረው ከዚህ የባርነት አዋጅ ጋር የሚተባበሩ ማናቸውም ኃይሎች ሁሉ ከአሁን ጀምሮ የሕዝባዊ ትግሉ ቀንደኛ ዒላማዎች መሆናቸውን ግልጽ አድርጎ መንቀሳቀስ ይገባል። በዚህ ሕዝባዊ ትግል ላይ የሚሳተፉ የሕዝብ ወገኖችም ሆነ ይህንን ዘራፊ ሥርዓት የሚያግዙ ኃይሎች በደንብ እንዲረዱት የሚያስፈልገው ይህን አዋጅ አከሸፍነው ማለት የወያኔ ሥርዓት አከተመለት ማለት እንደሆነ ነው። ይህ አዋጅ ተሳካ ማለት ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላልተወሰነ ጊዜ በባርነት መቀመቅ ውስጥ ሊኖር ተፈረደበት ማለት ነው። ለዚህ ነው አሁን የገባንበት ትግል የመጨረሻው የሞት ሽረት ትግል ነው የምንለው።
ለመሆኑ ይህ አዋጅ የሚደነግገው ምንድን ነው? ለምንድን ነው በፍጹም እንዲሳካ የማንፈቅድለት “የዘመናዊ ባርነት አዋጅ” ነው የምንለው?
“ባርነት” የሰውን ልጅ ሰው የሚያደርገውን መሠረታዊ ነጻነቱን ገፍፎ፤ ፈንጋዩ ከሚሰጠው ፈቃድ ውጭ በራሱ ምንም የሚወስነው ነገር እንዳይኖር ከልክሎ፤ ያለውን የጉልበትም ሆነ የማሰብ አቅሙን ሁሉ በባርነት ለሚያሳድረው ባለቤቱ ሀብት መፍጠርና አገልግሎት መስጠት ላይ ብቻ እንዲያውል የሚያደርግ ሥርዓት ነው። ባርያ የኔ የሚለው ንብረት የለውም፤ በገዛ ራሱ ሰውነትና አዕምሮ ላይ ሥልጣን የለውም። የሰው ልጅ እንዲህ ዓይነቱን ማንነቱን የሚነጥቅ በደል እሺ ብሎ በፈቃደኝነት አይቀበልም። ስለዚህ ይህን እንዲቀበል በጉልበት ማስገደድን ይጠይቃል። ይህን ለማድረግ ደግሞ ባርያ ፈንጋዮች የመጀመሪያ ሥራቸው ባርያ የሚያደርጉትን ሰው ከሰውነቱ የሚመነጨውን የነፃነትና ሰው የመሆን ፍላጎት በጉልበትና በሰቆቃ መንጠቅ ነው። አንዴ ይህን የውስጥ ማንነቱን ከነጠቁትና ባርያውን ወደ እንሰሳነት ከቀየሩት በኋላ እንደፈለጉት ለማድረግ በቀጣይነት ጉልበት መጠቀምም አያስፈልጋቸውም። በሕይወት የሚያቆየውን የሚበላውን መጥነው እየሰጡ እስከሚሞት ድረስ ጉልበቱን እየበዘበዙ ለራሳቸው ሀብት ማጋበስ ነው። ይህን በቀጣይነት ለማድረግ ባርያው ለራሱ ጥቅም እንዳያስብ መሆን አለበት። የሚያስበውን የሚነግሩት እነሱ፤ የሚሰማውን ወሬና ከማን ጋር መነጋገር እንዳለበት የሚወስኑለት እነሱ፤ የሚንቀሳቀስበትን ቦታ የሚወስኑለት እነሱ፤ መቼ መተኛትና መነሳት እንዳለበት የሚፈቅዱለት እነሱ፤ ምን ሥራ መሥራት እንዳለበት የሚፈቅዱት እነሱ፤ በሕይወት መኖርና አለመኖሩን የሚፈቅዱለት እነሱ፤ ባጠቃላይ ሕይወቱ በነሱ ፈቃድ ላይ የተመሰረተች እንጂ ከዚያ ውጭ ሕይወት እንደሌለው እንዲቀበል ማድረግ አለባቸው።
ይህን ለማድረግ ከሚጠቀሙት ጉልበት በተጨማሪም ሰውየው ይህ ኑሮው በግድ የተጫነበት ሳይሆን በተፈጥሮ ከፈጣሪው የተለገሰው እጣ ፈንታው እንደሆነ እንዲያምን ይጥራሉ። ይህን የሚያደርጉት ሰዎች በቁጥር ትንሽ ስለሆኑ በባርነት የሚኖሩት ሰዎች ተባብረው ከገቡበት የባርነት ቀንበር ራሳቸውን እንዳያላቅቁ ይህ የማይቻል እንዲሆን በባርያዎቹም መሀከል ልዩነት መፍጠርና አንዱ ባርያ ሌላውን የሚጠብቅበት መንገድ ማመቻቸትም አንዱ የመግዥያ መሣሪያቸው ነው። የተወሰኑትን ጥቂት ባርያዎች በአንጻራዊነት ቀለል ያለ የቤት ውስጥ ሥራ እያሠሩና ከሌሎች ባርያዎች በተለየ ከጌቶቻቸው የተረፈ ፍርፋሪ ምግብ እያበሉ እራሳቸውን እንደባርያ እንዳያዩና ሌላውን የመስክ ሥራ እየሠራ የሚፈጋውን ባርያ እየናቁና እንዳያምጽ የመቆጣጠር ሥራ ያሠሯቸዋል። ለሌላውም ባርያ “የጥሩ ባርያነት” አርአያ አድርገው ያቀርቧቸዋል። የሰው ልጅ እዚያ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ያገራችን ሰዎች አገሩን ላጣ ሰው እንሚተርቱት “ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ” የሆነ እንሰሳ ይሆናል ማለት ነው።
የወያኔ ጥቂት ዘራፊ መሪዎች ይህን አዋጅ ሲያውጁና በተግባር እናሳካዋለን ብለው ሲገምቱ በትግሉ ነጻነቱን እያወጀ ያለውን የኢትዮጵያን ሕዝብ እዚያ ባርነት ደረጃ ላይ እናደርሰዋለን ብለው ገምተው ነው። በዚህ አዋጅ ላይ እነሱ ከፈቀዱለት ሰው ውጭ ያለ ኢትዮጵያዊ ምን መናገር እንደሚችል፤ ምን ማሰብ እንደሚችል፤ ከማን ጋር እንደሚያወራ፤ ምን ዜና እንደሚሰማ፤ ምን ማንበብ እንዳለበት፤ የት የት ቦታ መንቀሳቀስ እንደሚችል፤ ምን ሥራ እንደሚሠራ፤ በስንት ሰዓት ከቤቱ ወጥቶ በስንት ሰዓት እቤቱ መግባት እንደሚችል፤ የራሱን ንብረት እንዴትና መቼ ማንቀሳቀስ እንደሚችልና ይህንን እነሱ ከፈቀዱለት ውጭ በራሱ ፍላጎትና ተነሳሽነት ምንም ዓይነት ነገር ቢያደርግ ሕይወቱን እስከመንጠቅ ድረስ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስዱበት በዚህ የዘመናዊ ባርነት አዋጃቸው አውጀዋል። በቃሊቲ፣ ቂሊንጦ፣ ዝዋይና ቁጥራቸው ተዘርዝሮ በማያልቅ የማጎርያና የማሰቃያ እስር ቤት ያሰሯቸውን ዜጎች ከንጋት 11 ሰዓት እስከ ቀን 11 ሰዓት ድረስ ውጭ ወጥተው ጸሀይ እንዲሞቁና እግራቸውን እንዲያፍታቱ ከመፍቀድ በቀር ቀሪውን ሰዓት በተቆለፈ ቤት ውስጥ እንዲቀመጡ እንደሚያደርጉት ሁሉ በዚህ አዋጅም በሀገሪቱ ድንበር 50 ኪሎ ሜትር ሬድየስ እና ከዋና ዋና መንገዶች በግራና በቀኝ 25 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ሁሉ (ይህ ባገሪቱ ያሉትን ሁሉንም ከተሞችና ትናንሽ መንደሮች ከሞላ ጎደል ያካልላል) ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ እራሱን በገዛ ቤቱ ውስጥ እንዲያስር የወሰነ እጅግ የሚገርምና በዛሬ ዘመን ሊታሰብ የማይችል የጅምላ እስር አዋጅ ነው። ይህ አዋጅ ከተሳካለት ማንም ኢትዮጵያዊ፤ ከነሱና ከቡችሎቻቸው በቀር፤ እራሱን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስፈልገውን ማናቸውንም ዓይነት መሣሪያ እንዳይይዝ የሚከለክልና ያለውንም የሚቀማ ስለዚህም ለዘላለሙ በፍርሀትና በድንጋጤ እንዲኖር፤ በራስ የመተማመን ስሜቱን እንዲሰልብ ያለመ አዋጅ ነው። ይህ አዋጅ ከተሳካ እነሱ የኢትዮጵያውያንን ጉልበት እንደፈለጉ እየመዘበሩ የሚደልቡበት፤ ሌላው ኢትዮጵያዊ በገዛ ሀገሩ የበይ ተመልካች ብቻ ሳይሆን ጉልበቱንና የሀገሩን ሀብት ለነሱ እየገበረ የሚኖርበትን የዘመናዊ ባርነት ሥርዓት እንዲቀበል የሚያደርግ ነው። በዚህ ስድስት ወራት ውስጥ ይህንን ፍላጎታቸውን በኃይል ካሳኩ ከዚያ በኋላ አዋጁን ቢያነሱት እንኳን፤ ማሰሩንና መግደሉን ቢያቆሙት እንኳን፤ ይህ ቅስሙ የተሰበረ ሕዝብ ሰጥ ለጥ ብሎ ይገዛልናል ብለው አምነው የሚወስዱት እርምጃ መሆኑን ላንድ አፍታ እንኳም መዘንጋት የለበትም።
ለመሆኑ እንዲህ አይነት እርምጃ በዛሬው ዓለምና በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ሊሠራ ይችላል ብለው እንዴት ገመቱ?
አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የደረሰበትን የነፃነት ፍላጎት ደረጃና ባጠቃላይ የዓለማችንን ሁኔታ በክፍት ልቦና ለሚመለከት ሰው በሀገራችን ያለውንና እነሱ ራሳቸው የፈጠሩትን የፖለቲካ ቀውስ በዚህ ዓይነት አዋጅ እንፈታዋለን ብለው ማሰባቸው በራሱ በነሱ በሞራ በተሸፈነ ትንሽ ጭንቅላት ውስጥ የሚርመሰመስ የራሳቸው የተለየ የቅዠት ዓለም ውስጥ የሚኖሩ፤ ይህ የቅዠት ዓለማቸው ግን ከእውነተኛው ዓለም እውነታ ጋር ሲጋጭባቸው የሚሠሩትን እስከማያውቁ ድረስ የሚምታታባቸው ግማሽ እብዶች መሆናቸውን ነው የሚገልፀው። በመጀመሪያ፣በዚህ አዋጅ አማካይነት እየታገሉት ያሉት ከማን ጋር እንደሆነ በፍጹም አላወቁም። በነሱ የቅዠት ዓለም፤ ትግላቸው ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሳይሆን እነሱ “ጥቂት” ከሚሏቸው የነሱን “የልማትና የሕዳሴ ጉዞ” ከሚቃወሙ ወይንም ካልተዋጠላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር ነው። ከእነኝህ ጥቂት ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር ለሚደረግ ትግል ግን ለምን በመላው ሕዝብ ላይ ጦርነት ማወጅ እንዳስፈለጋቸው መቼም በትክክል በሚሰራ አዕምሮ ታስቦ የሚደረግ አይደለም። ከመላው ሕዝብ ጋር በሚደረግ ትግል ደግሞ እነኝህን እርምጃዎች በመውሰድ እናሸንፋለን ወይንም ያለሕዝብ ትብብር እነኝህን እርምጃዎች ተግባራዊ እናደርጋለን ብለው እንዴት ሊያምኑ እንደሚችሉ በሙሉ አዕምሮው ለሚያስብ ሰው ለመገመት አስቸጋሪ ነው። ሕዝቡ ቤቱ ውስጥ ያለው ቴሌቪዥን ላይ ምን እንደሚሰማ ለመቆጣጠር ቀደም ብሎ በሕዝቡ ትግል የፈረሰው “የአንድ ለአምስት” ጥርነፋ አሁንም ይሠራል
ስለዚህም ልጅ አባትና እናቱን፤ ወላጆች ደግሞ ልጆቻቸውን ይሰልሉልኛል ብለው በቅዠት ዓለማቸው ካላመኑ በስተቀር ዛሬ እውነታው በምድር ላይ የለም። ለመሆኑ፣ በሀገሩ ውስጥ ያለውን የሳተላይት መቀበያ ሳህን ሁሉ ከየቤቱ ጣርያ ላይ ለማውረድ የሚያስችል የሰው ኃይል አለን ብለው እንዴት ሊያምኑ ቻሉ? በየመንግሥት መሥሪያ ቤት ያለውና በግል ድርጅቶች ውስጥ የሚሠራውን ሠራተኛ ሁሉ “በሥራ መለገም ወንጀል ነው” ብለው ሲደነግጉ ይህንን እንዴት እናስፈጽማለን ብለው ገምተው ነው? ዳሽን ቢራና ፔፕሲ አልጠጣም፤ የህወሓት ንብረት በሆነው ሰላም አውቶብስ አልሄድም፤ ገንዘቤን በህወሓትና እሱን በሚያገለግሉ ባንኮች ውስጥ አላስቀምጥም፤ የመሶቦ ሲሚንቶን አልገዛም ብቻ ሳይሆን በባርነት ታስሬ የምኖርበትን ቤት ከናካቴው አልሰራም ብሎ ያመረረን ሕዝብ እንዴት አድርጎ ነው ፔፕሲንና ዳሽን ቢራን ሊግተው ያሰበው? እንደው እዚህ ግባ የማይባል ደሞዝ ከፍለው መሣሪያ ያስታጠቁት የወታደርና የፖሊስ ኃይል ለዚህች ደሞዙ ብሎ ራሱንና ወገኖቹን ለዘላለማዊ ባርነት ለመዳረግ የሚተጋ ግዑዝ ኃይል ነው ብሎ በዚህ በባዶ ትዕቢት በተወጠረ ንቀታቸው ቢያስቡ እንኳን፤ ይህ ቢበዛ ከ200ና 300ሺ በላይ የማይደርስ ኃይል፤ የሀገሪቱን ድንበር የመጠበቅ ሥራውን ሁሉ ትቶና ከድንበር ላይ ነቅሎ ለዚህ አዋጅ ማስፈጸሚያ ሥራ ቢያውለው እንኳን፤ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የተነሳንና እንዳስፈላጊነቱ በመሣሪያ ኃይል እራሱን ለመከላከል ያደራጀን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብ እንዴት አድርጎ ያሸንፋል ብሎ ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው ሊያምን ይችላል? ከዛሬ በኋላ እንኳንስ ሠራዊቱን በፍላጎት ለመልቀቅ እረፍት እንኳን መውስድ አትችልም ተብሎ በኃይል ተሰንጎ እንዲዋጋ የታወጀበት ሠራዊት ከሕዝቡ ጋር ጦርነት መግጠሙን ሲያውቅ አይደለም ከልቡ ሊዋጋና ሊያሸንፍ ከሕዝቡ ጋር ወግኖ መልሶ አዛዦቹንና ከሕዝብ ጋር የሚያዋጉትን የሀገርና የሕዝብ ጠላቶች ሊወጋ እንደሚዘጋጅ፤ ይህን እንኳን ማድረግ ቢያቅተው ከነመሣሪያው ጠፍቶ ሊሰወር እንደሚችል በትዕቢት የተወጠረና ማሰብ ያቆመ ጭንቅላት ካልሆነ በስተቀር በትክክል ለሚያስብ ሰው እንዴት ይሳነዋል? በመቶ ሺ እስኴር ኪሎ ሜትሮች በሚቆጠር አካባቢ የሚንቀሳቀስን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ስንት ሚሊዮን ተባባሪዎቹን ተማምኖ ነው ሊቆጣጠረው የሚችለው? በሌላ አነጋገር የማሰብ ኃይላቸው ፍጹም ተመናምኖ ያለቀው የአገዛዙ መሪዎች እንኳን ይህንን አዋጅ ያለሕዝብ ትብብር እጃቸው ላይ ባለው ኃይል እናሳካዋለን ብለው ያምናሉ ለማለት በጣም አስቸጋሪ ነው። ሕዝቡ ደግሞ በዛሬ ዘመን በራሱ ላይ ባርነትን ለመጫን ይተባበራል ብሎ መገመት በፍጹም የሚቻል አይደለም።ይልቁንም ወያኔዎች የተማመኑበት የሚመስለው በተለመደ ባዶ ድንፋታቸው ሕዝቡን አስፈራርተው፤ ወይንም የተወሰኑ ሰዎችን ገድለውና አስረው በዚህ እርምጃቸው ሕዝቡ ከተሸማቀቀ በኋላ ለነጻነቱ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ያቆማል ብለው ነው እየቆመሩ ያሉት። የዚህ ክፉ ቁማር ውጤት ግን እነሱ የጠበቁት ሳይሆን እስካሁን ዘርፈው ያካበቱትን ንብረት ሳይበሉ ተሰባብረው የሚወድቁበትን፤ የኢትዮጵያ ሕዝብም በዚህ ዘረኛና ዘራፊ ሥርዓት መቃብር ላይ እውነተኛ ነጻነቱን የሚቀዳጅበት የመጨረሻው ሂደት እንደሚሆን አያጠራጥርም።
ይህ ግን ስለተመኘነው የሚመጣ ሳይሆን በሥራችንና በትግላችን እውን የምናደርገው ድላችን ነው የሚሆነው!
ታዲያ እዚያ የምንናፍቀው ድላችን ላይ ለመድረስ በሕዝባዊ ትግሉ የሚወሰዱ እርምጃዎችና ዋና ዋና ዒላማዎች ምንድን ናቸው?
ቀደም ብዬ እንዳልኩት የወያኔ መሪዎች ይህን በፍጹም ሊሳካ የማይችል እርምጃ መውሰዳቸው ሳይሆን የሚገርመው ይህንን የመጨረሻ የተስፋ መቁረጥ እርምጃቸውን እንዲህ በቶሎ መውሰዳቸው ነው የሚገርመው። እንዲህ ዓይነት ፍጹም ውጤቱን በቅጡ ያላሰቡበት እርምጃ ውስጥ የከተታቸው ደግሞ በዚህ ባጭር ጊዜ ሕዝባዊ ትግሉ የወሰዳቸው እርምጃዎች ከሚጠበቀው በላይና ባልተጠበቀ ፍጥነት ውጤታማ በመሆናቸው ነው። ባንድ በኩል በሀገር ውስጥ የሚደረገው የሕዝባዊ
እምቢተኝነት እንቅስቃሴ ባጭር ጊዜ ትግል የበሰሉ ወጣት አመራሮችን አፍርቶ በየጊዜው የሚቀያየሩና በምድር ላይ የሚፈጠሩ ሁኔታዎችን ከግምት እያስገባ የሚሄድ ተለዋዋጭ የትግል ስልቶችን በመጠቀም ሕዝቡን በሰፊው ያሳተፈ ቀጣይነት ያለው ትግል ማካሄድ በመቻላቸው ነው። ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያለው ትልቁ ነገር ይህ ህዝባዊ እምቢተኛነት እንቅስቃሴ በአንድ የሀገሪቱ ክፍል ብቻ ሳይሆን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል በፍጹም ባልተጠበቀና የወያኔን ዘረኛ መሪዎች ባስደነገጠ መልኩ በደል ባስተሳሰረው የአንድነት መንፈስ መካሄዱ ነው። የወያኔን ዘረኛ መሪዎች ብርክ ያስያዛቸው ጎንደር ላይ የአማራ ሕዝብ ተገልብጦ ወጥቶ ወያኔን ወጊድልኝ ከማለቱ ባሻገር የበቀለ ገርባን ምስል ይዞ “የኦሮሞ ደም ደማችን ነው” የሚል መፈክር እያሰማ መውጣቱና ከኦሮሞ ሕዝብ ትግል ጋር አጋርነቱን ማሳየቱ ነው። በኢሬቻ በዓል ላይ የኦሮሞ ወጣቶች “የአማራ በደል የኛም በደል” ነው ብለው በጎንደርና በጎጃም ለሚደረገው ትግል ወገንተኛነታቸውን ማሳየታቸው ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በሁሉም ክልሎች ሕዝቡ ለሚያደርገው ሰላማዊና የሰለጠነ ትግል የወያኔ መሪዎች መልስ ጥይት መሆኑን በዓይኑ እየተመለከተ ሲሄድና በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የትግል ጓዶቹን እየቀበረ ሲሄድ፤ አረመኔን በሰለጠነ ትግል ብቻ ማስቆም እንደማይችል አውቆ የሕዝባዊ እምቢተኝነት ትግሉን በሕዝባዊ አመጽ ለመደገፍ እየወሰደ ያለው ዝግጅትና መለስተኛ እርምጃዎች ናቸው።
ዛሬ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ለመሞት ብቻ ሳይሆን ለመግደልም የቆረጡ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አርበኞች በረሀ የወጡበት ጊዜ ነው። ዛሬ የአርበኛ ታጋይ አበራ ጎባውን ዓይነት ጀግና ተዋጊዎችና አዋጊዎች ብዙ የአጋዚ ጦር ደምስሰው የሚሰዉ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች ይህን ሥርዓት ከስሩ ለመመንገል የተዘጋጁበት ጊዜ ነው። እንዲህ ዓይነቶች ጀግኖች በኦሮሚያ የተለያዩ ቦታዎች፣ በአርባ ምንጭ፣ በቴፒ፣ በኮንሶ፣በጋምቤላ፣ በአፋር የጀንግንነት ተግባራትን ፈጽመው አሳይተውናል። ዛሬ የህወሓት አገዛዝ የሚመራው ጦር እየከዳ እንዲህ ዓይነት ጀግኖችን የሚቀላቀልበት ወቅት ነው። ዛሬ የብዙ ጊዜ እንቅስቃሴያችን ፍሬውን ለማፍራት የተዘጋጀበት፤ ትግሉን ከዳር ለማድረስ ሁኔታዎች የተመቻቹበት ጊዜ ነው። የወያኔ መሪዎች ይህንን ጠንቅቀው አውቀዋል። ለዚህ ነው ይህንን የመጨረሻ የተስፋ መቁረጥ እርምጃዎችን እየወሰዱ ያሉት።
ይህ በጥሩና በአመርቂ ሁኔታ እየተካሄደ ያለ ትግል ግን እመጨረሻው ምዕራፉ ላይ ሳይደርስ በፍጹም መቆም የለበትም። “የነብርን ጅራት አይይዙም፤ ከያዙም አይለቁ” የሚለው የአበው ብሂል እዚህ ላይ ይሠራል። ሕዝባዊ ትግሉን እዚህ ካደረስነው በኋላ ከዳር ሳናደርሰው መመለስ ከቶ አይቻለንም። ማድረግ ያሉብን ነገሮች ደግሞ ግልጽ ናቸው። አሁን በመላ አገራችን የተቀጣጠለው ሕዝባዊ ትግል እስካሁን ከነበረው በላይ አጠናክሮ መቀጠልና አዲስ ለተፈጠረው ሁኔታ የሚመጥኑ አዳዲስ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባል። የትግል ዒላማዎቻችንን ከዚህ በፊት ከነበሩት በተጨማሪ ይህንን የባርነት አዋጅ ለመተግበር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ላይ ሁሉ ማነጣጠር ይኖርበታል። ከዚህ አንፃር ይህንን የባርነት አዋጅ ለማክሸፍና ትግላችንን ከዳር ለማድረስ የሚከተሉትን ተጨባጭ እርምጃዎች ሕዝባዊ ትግሉ በቀጣይነት ይወስዳል፤
1. ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ነፃነትን የሚሻ ሁሉ ከሚመስለው ጋር ይደራጅ ስንል ቆይተናል፤ አሁን ከመደራጀትም አልፎ ራሱን ለመከላከል ከዚያም አልፎ ለሚደርስበት ጥቃት ተመጣጣኝ ምላሽ ለመስጠት ይዘጋጅ። ባርነትን በጉልበት ሊጭንብን ጦር ሰብቆ የመጣውን እኩይ ኃይል፤ ምርጫችን ሆኖ ሳይሆን በላያችን ላይ የተጫነ ግዴታ ስለሆነ ከእንግዲህ ገድሎ መሞት እንጂ “በሰላምተኝነት” መሞት የለም። ራስንና ሕዝብን ከህወሓት ሽብር ለመከላከል በየቦታው የተደራጁና የታጠቁ ህዝባዊ ቡድኖች አሉ፤ ተጨማሪ ቡድኖችም በከፍተኛ ፍጥነት እየተደራጁ ነው፤ ። ነፃነት የጠማው ኢትዮጵያዊ ሁሉ እነዚህን ቡድኖች ይደግፍ፣ ይቀላቀል።
2. ይህ ትግል የኢትዮጵያውያን ሁሉ ትግል ነው። የተደራጁ ቡድኖች ትግል ብቻ አይደለም። በቡድን ብቻ ሳይሆን በግልም ጭምር ለህወሓት አመፃ የአመፃ ምላሽ ለመስጠት ሁሉም ነጻነት ፈላጊ ኢትዮጵያዊ መዘጋጀት አለበት። የወያኔን ፋሽስታዊ ስርዓት ከበላይ ሆነው የሚዘውሩት ብቻ ሳይሆን በመካከለኛና በስር ሀላፊነት የሚሰሩ የፌደራል ፖሊስ፤ የየከተማው የፖሊስ አባላት፤ ለወያኔ የስለላ ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች፤ የመከላከያ ሹማምንት፤ በተለያዩ ደረጃ ላይ ያሉ የህወሀት/ኢህአዴግ ካድሬዎችን ስም ዝርዝር፤ የስራ ሀላፊነት፤ የመኖሪያና የስራ አድራሻ እንዲሁም ስልክና የኢሜል አድራሻቸውን የያዘ ሙሉ መረጃ አለን። በየቀበሌው የሚሰሩ ትናንሽ የስርዓቱ አገልጋዮችን የያካባቢው ነዋሪዎች ያውቋቸዋል። ይህ የባርነት አዋጅ እስካልተቀለበሰ ድረስ ይህን አዋጅ ለመተግበር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ሁሉ የህዝባዊ ትግሉ የቡድንም ሆነ የግል ኢላማዎች ናቸውና ጊዜው ሲደርስ ይህን መረጃ ለህዝባችን በይፋ የምንገልጽ መሆናችን እንዲታወቅ እንፈልጋለን።
3. ይህ የባርነት አዋጅና የአዋጁ ባለቤት ህወሓት/ኢህአዴግ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ መንገዶች “መሠረተ – ልማቶች” ሳይሆኑ መሠረተ – ጥፋቶች ናቸው፤ አውራ ጎዳናዎች አስጠቂዎቻችን ናቸው። በእነዚህ መንገዶች እየተጓጓዘ ነው የአጋዚ ጦር ወገኖቻችንን እየፈጀ ያለው። ስለሆነም ለትግላችን የሚያስፈልጉ ካልሆኑ በስተቀር መንገዶችን መዝጋት ተቀባይነት ያለው ሥራ ነው፤ ከነፃነታችን የሚበልጥ አንዳች ቁሳዊ ሀብት የለም።
4. የታወቁ የሥርዓቱ ቀንደኛ አራማጆች ብቻ ሳይሆኑ ይህንን የባርነት አዋጅ ለማስፈፀም የሚሯሯጡ ግለሰቦች፣ ቡድኖችና ተቋማት ሁሉ ጠላቶቻችን ናቸው። እነዚህ ሁሉ የትግላችን ዒላማዎች ናቸው። በየሠፈሩ አዋጁን የሚያስፈጽሙ ስማቸው ተለይቶ ይፋ ይደረጋል፤ የነፃነት ኃይሎች በእነዚህ ኃይሎች ላይ በቡድንም በግልም እርምጃ ይወስዳሉ።
5. የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አባላት በተለይም የአጋዚ ጦር አባላት – ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለእናንተ ገደብየለሽ ሥልጣን የሰጠ በመሆኑ የምትጠቀሙ አይምሰላችሁ። እናንተ ዜጎችን በመግደላችሁ፣በማሰራችሁና በማሰቃየታችሁ የሚጠቀሙት አለቆቻችሁ ጄኔራሎች እና የህወሓት/ኢህአዴግ ሹማምንት ናቸው።አዋጁ ከሌላው ሕዝብ ያላነሰ እናንተንም ባርያ የሚያደርግ ነው፤ የዓመት እረፍት እንኳን መውሰድ እንዳትችሉ የተገደባችሁ መሆኑን እወቁ። በአዋጁ ተፈፃሚነት ለእናንተ የሚተርፋችሁ የእድሜ ልክ ፀፀትና ከሕዝብ ጋር የምትገቡበት ቁርሾ ነው።የእናቶችና የሕፃናት ዋይታና ለቅሶ ይሰማችሁ፤ህወሓት/ኢህአዴግ እናንተን ተጠቅሞ የኢትዮጵያን ሕዝብ በባርነት እየገዛ መሆኑ ይታያችሁ።ከኢህአዴድ መወገድ በኋላ የሚመጣው ሥርዓት እናንተን የሚጠቅም እንጂ የሚጎዳ አለመሆኑን አውቃችሁ ከአገዛዙ ጋር ያላችሁን ግኑኝነት በጥሱ።ዛሬውኑ ወስኑ ! በወገኖቻችሁ ላይላለመተኮስ ለራሳችሁ ቃል ግቡ !!! የመሣሪያዎቻችሁን አፈሙዝ በሙስና ወደደለቡት አለቆቻችሁ አዙሩ፤አልያም ሥርዓቱን ከድታችሁ የነፃነትኃይሎችን ተቀላቀሉ። ሥርዓቱን ለሚከዱ የሠራዊቱ አባላት ሕዝባዊ ትግሉ የክብር አቀባበል እንደሚያደርግ ቃል ይገባላችኋል፤ በየቦታውም ይህን የሚያስተባብሩ አካላት ተደራጅተዋል። ይህን ዕድል ከመጠቀም ይልቅ ሥርዓቱን ለማቆየት የወሰናችሁ የሠራዊቱ አባላት የምትዋጉት የጠላት ጦርን ሳይሆን የራሳችሁን ሕዝብ መሆኑን እወቁ። በምንም ዓይነት ሕዝብን ማሸነፍ አትችሉም።
6. የጦርና ፓሊስ ሠራዊት አባላት ቤተሰቦችና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሠራዊቱ ላይ ጫና ያሳድር።ሠራዊቱ ከኢትዮጵያ አብራክ የወጣ ነውና የኢትዮጵያ ሕዝብን ይሰማል።የኢትዮጵያ ሕዝብ ለህወሓት/ኢህአዴግ ሹማምንት ድሎት ሲባል በገዛ ልጆቹ መገደልና መረገጥ የለበትም። ሠራዊቱ የህወሓት/ኢህአዴግ ሠራዊት መሆኑ እንዲያበቃ ሁለገብ ጥረት እናደርጋለን።
7. በአገዛዙ የስለላ መዋቅሮች የምትሠሩ ወገኖቻችን ኃላፊነት አለባችሁ። ማንን እየተከላከላችሁ፤ ማንን እያጠቃችሁ እንደሆነ አስተውሉ። ለራሳችሁ ደህንነት እና ለህሊናችሁ የሚበጃችሁ ከሕዝብ ጎን መቆም ነውና ዛሬውኑ ወስኑ፤ እናንተም ወደ ሕዝብ ትግል ስትመጡ ለመቀበል ዝግጁ ነን፤ ይህን እድል አታስመልጡ። በተመሳሳይም የኢህአዴግ አባላት ጎራችሁን ለዩ። አምርሮ ለዘመተብን ጠላት የመረረ ምላሽ ለመስጠት ተዘጋጅተናል።
8. ህወሓት/ኢህአዴግ ከመነሻው ጀምሮ በአርሶ አደሩ እየነገደ ያለ እኩይ ኃይል ነው። ዛሬ የመንግሥትን ሥልጣን የያዙት ኃይሎች አርሶ አደሩ እየተራበና እየታረዘ ጠግቦ የሚያድር አስመስሎ ለዓለም የሚናገሩ ውሸታሞች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ መሬትን እየቀሙ ለራሳቸውና ለወዳጆቻቸው የሚያድሉ በልተው፣ ገፈው፣በዝብዘው የማይጠረቁ ሆዳሞች ናቸው። ከእንግዲህ የኢትዮጵያ አርሶ አደር በባርነት ለሚገዛው አገዛዝ ግብር፣ መዋጮ፣ የምርጥዘርም ሆነ የማዳበሪያ እዳ አይከፍልም፤ ካድሬዎች በሚጠሩት ስብሰባ አይወጣም፤ ራሱ በመረጣቸው የአገር የቀበሌና የገበሬ ማህበራት አስተዳዳሪዎች እንጂ በሥርዓቱ ካድሬዎች አይተዳደርም፤ ለዳኝነት ወደ አገዛዙ ፍርድ ቤት አይሄድም። በያካባቢው የራሱን ዳኞች ከመሀሉ መርጦ ይዳኛል እንጂ!
9. በማናቸውም የመንግሥት ሥራ ላይ የተሠማራ የመንግሥት ሠራተኛ ሥራውን በአግባቡ ሠራ ማለት ይህንን የባርነት አዋጅ አስፈፃሚ ሆነ ማለት እንደሆነ ይወቅ። እያንዳንዱ ነፃነቱን የሚወድ የመንግሥት ተቀጣሪ የዕለት ተዕለት ሥራውን ሲፈጽም የሥራው ውጤት ህወሓት/ኢህአዴግን የሚያዳክም እንጂ የሚያጠናክር እንዳልሆነ እርግጠኛ ይሁን። ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አሻጥር በሁሉም ቦታዎችና በሁሉም የሥራ ዓይነቶች ተግባራዊ ይሆናሉ። በባርያ ፈንጋይ ላይ አሻጥር መፈፀም በምድር የሚያስመሰግን በሰማይም የሚያፀድቅ ተግባር እንደሆነ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ያውቃል፤ በጣሊያን ፋሽስት የወረራ ዘመን የመንግሥት ሠራተኞች የነበሩ የውስጥ አበርኞች አብነቶቻችን ናቸው። ሕዝባዊ አሻጥር በኢትዮጵያ በህወሓት አገዛዝ ሥር ያለ የመንግሥት ሠራተኛ የሥራ ባህል ይሆናል።
10. ኢትዮጵያውያን በአገራችን በነፃነት መኖር የምንችለው ይህን የባርነት አዋጅ በማክሸፍ የህወሓት/አገዛዝን አስወግደን የሕዝብ ይሁንታ ያለው መንግሥት ስንመሠርት ብቻ እንደሆነ እያንዳንዱ ወጣት ይወቅ። ሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ ሕዝባዊ አመጽና ሕዝባዊ አሻጥር የወጣቱ ትውልድ ባህል ይሆናሉ። ከእንግዲህ የወጣቱ ሙሉ አካላዊና አዕምሮዓዊ ጉልበት ይህንን አዋጅ በማክሸፍ ሥራ ላይ ይውላል። በየቦታውና ጊዜው ተስማሚ የሆነ የትግል ስልት በመቀየስ የዚህን አስከፊ ሥርዓት ፍፃሜ ለማፍጠን የተለያዩ አደረጃጀቾችን በሥራ ላይ አውለናል። ወጣቶች የራሳቸው ፈጠራና አካባቢያዊ ግብዓቶችን በመጠቀም የህወሓት አገዛዝን በኃይል ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት እንደግፋለን፤ እናበረታታለን።
11. በየአካባቢው አካባቢያዊ ጥያቄዎች ሊኖሩን ይችላሉ፤ አካባቢያዊ ጥያቄዎችን ለትግል ማንሳት የሚበረታታ ነው፤ ያም ሆኖ ግን ትግላችን የሚደጋገፍና ወደ ጋራ ድል የሚያመራ እንዲሆን የተቻለንን ሁሉ ጥረት እናደርጋለን። በተለያዩ ማኅበረሰቦችና በተለያዩ እምነት ተከተያዮች መካከል የተፈጠረውን መግባባትና መተጋገዝ ለማዳበር ጠንክረን እንሠራለን። አገራዊ ኅብረት ለመፍጠር ቀንና ሌሊት እንተጋለን።
12. በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንም ሙሉ ጉልበታቸውና ኃይላቸውን የህወሓት አገዛዝን ማዳከም ብቻ ሳይሆን ማጥፋት ላይ እንዲያተኩሩ እንሠራለን። በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የባርነት አዋጅ ታውጆበታልና በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንም ምላሽ የመረረ ይሆናል።
ውድ ወገኖቼ!
በመጨረሻ ማሳሰብ የምሻው አንድ ወሳኝ ነጥብ አለ። ይህ የህወሓት ዘራፊ ቡድን በአንድ በኩልና በዋናነት ይህንን የባርነት አዋጁን በጉልበት ለማስፈጸም ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፤ በሌላ በኩል ደግሞ ሰላም የሚፈልግ ለማስመሰል እሱ ከመረጣቸውና ባፈና መዋቅሩ ውስጥ ከቦ እያስፈራራ ካስቀመጣቸውና በተግባር ሽባ ካደረጋቸው የፖለቲካ ሰዎች ጋር እደራደራለሁ የሚል የተለመደ ማደናገሪያውን ለማስኬድ እየሞከረ እንደሆነ እያየን ነው።ይህ አካሄድ አውቀው ሊታለሉ የሚፈልጉ ፈረንጆችን ያታልልበት እንደሆነ እንጂ በሀገሪቱ ያለውን የፖለቲካ ቀውስ በፍጹም ሊፈታ እንደማይችል የታወቀ ነው። የፖለቲካ ኃይሎች በነፃነት መንቀሳቀስና እንወክለዋለን ከሚሉት ሕዝብ ጋር በነፃነት መምከር ሳይችሉ ትርጉም ያለው ወደ ዘላቂ ሰላም የሚወስድ ድርድር ማድረግ ከቶውኑም አይችሉም። ሽጉጥ በግንባርህ ላይ ደግኖ “ከነብስህ ወይንም ከገንዘብህ” ብሎ ምርጫ ለሚሰጥህ ማጅራት መቺ ሕይወትህን ለማትረፍ “ገንዘቤን ውሰድ” ብትለው በማጅራት መቺውና በሰለባው መካከል “የሰጥቶ መቀበል ድርድር ተደረገ” እንደማይባል ሁሉ በግንባራቸው ላይ ሽጉጥ ደግኖ፤ ወይንም በእስር ቤት ከከተተ በኋላ የሚደረግ ድርድር በምንም አይነት በነፃነትና በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ድርድር ተደርጎ አይወሰድም፤ ተቀባይነትም የለውም። ስለዚህ ይህ አዋጅ በተግባር ላይ እስካለ ድረስ የሀገር ውስጥ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን በማስፈራራት እየሰበሰቡ ወያኔን ብቻ አሸናፊ የሚያደርግ የድርድር ሙከራ ከእስረኞች ጋር የሚደረግ ድርድር ስለሆነ ምንም ተቀባይነት የለውም። የሕዝባዊ ትግሉም በእንዲህ አይነት የማደናገሪያ ሂደት ከጀመረው የነፃነት ትግል ላንዲት ጋት እንኳን እንደማይዘናጋ እንዲታወቅ ያስፈልጋል።
ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ!!!!
በዚህ የመጨረሻ የፍልሚያ ወቅት ጥቂቶቻችን ልናልፍ እንችላለን። ለነፃነታችን ስንል ሕይወታችንን ብንሰጥ ፈጣሪያችን በአምሳሉ ሲፈጥረን የሰጠንን የሰውነት ማንነት እውን ለማድረግ በምናደርገው ትግል ነውና የምናልፈው፤ የፈጣሪያችንን ፈቃድ ለማስፈጸም የገበርነው ሕይወታችን ነውና በደስታ የምንጠጣው ጽዋችን ነው። ይልቅስ ፈጣሪያችን ለምንግዜውም ይቅር የማይለን ከሌላው እንሰሳ ለይቶ የሰጠንን ይህን በነፃነት የታጀበ የሰው ልጅነት፤ እንደ እንሰሳ ለሚበላና ለሚጠጣ ቁሳዊ ጥቅም ሸጠን፤ ሰው መሆንን በእንሰሳዊ የባርነት ሕይወት ቀይረን እኛ ባርነትን ተቀብለን ከራሳችን አልፎ ባርነትን ለልጆቻችን ያስተላለፍን እንደሆነ ነው። የዛሬ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የባርነትን ኑሮ ከኛ እንዳያልፍና ወደ ልጆቻችን እንዳይጋባ ማስቆም ታሪክ የጣለብንና በእርግጠኛነት የምንፈጽመው ተግባራችን እንደሆነ ከቶውንም አልጠራጠርም።
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ
አንድነት ኃይል ነው !!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
ጥቅምት 7 ቀን 2009 ዓ.ም.