Sunday, 25 October 2015

Britain Stands “Shoulder To Shoulder” With Ethiopia Despite British Man On Death Row


October 24, 2015
Alan White, BuzzFeed News Reporter, UK
Andy-Tsege-2
This is 59-year-old Briton Andargachew Tsege with his family
Last June, he was snatched by Ethiopian security forces at an airport in Yemen while he was waiting for a flight to Eritrea, and taken to Ethiopia having been sentenced to death in his absence for allegedly plotting a coup and planning to kill Ethiopian officials. He denies the claims.
Tsege has lived in the UK since 1979. The Mail on Sunday reported that his problems began because he “fell out with his university friend ex-Prime Minister Meles Zenawi, after he exposed government corruption and helped establish a pro-democracy party.”
The campaign group Reprieve claims that he has appeared on Ethiopian TV “looking ill and gaunt” and is worried that Tsege could be executed “at any time.” It also claims that he was illegally rendered, and was “sentenced to death during a mass trial in violation of basic fair trial standards”.
BuzzFeed News has obtained documents that explain how Britain is showing a publicly united front with Ethiopia while lobbying behind the scenes to secure justice for Tsege.
In September, Foreign Office minister Grant Shapps sent a letter to campaigners in which he wrote that the British government took Tsege’s detention and welfare “very seriously”.

He added: “We are deeply concerned that Mr Tsege has been held in Ethiopia for the past year without a legal process to challenge his detention, and we consistently raise these concerns with the Ethiopian authorities. We are disappointed that, despite repeated requests at the highest levels, we have only been allowed four consular visits during the past year.”
Shapps went on to describe a number of occasions when the British government had lobbied the Ethiopian government over Tsege’s case:
“The Foreign Secretary subsequently spoke to the Ethiopian Foreign Minister on 30 June, and informed him that the lack of progress risked undermining the UK’s valued bilateral relationship with Ethiopia. The Secretary of State for International Development raised our concerns with the Ethiopian authorities on 16 July, during her visit to Ethiopia.”
He lists further occasions, including an approach by David Cameron, before concluding:
“As a result of our ongoing lobbying, Mr Tsege has been transferred to a federal prison. While we welcome this news, the British Government will continue to press and urge the Ethiopian authorities for regularised consular access, assurances that he receives appropriate medical treatment and a legal process by which he can challenge his detention.”
Yesterday, Ethiopian foreign minister Tedros Adanhom was in London for the UK Ethiopia Trade Investment Forum, an event supported by the Foreign Office and the Department for Business, Innovation, and Skills.
Shapps delivered the keynote address at the forum. He is understood to have said that “the UK stands shoulder to shoulder with Ethiopia in transformational change”.
However, behind the scenes, his department continued to lobby for Tsege’s release.
In response to a request from BuzzFeed News, foreign secretary Philip Hammond released a statement:
“I have again raised the case of Andargachew Tsege and made it clear that the way he has been treated is unacceptable. I welcome the improvement in access to him, following the British Government’s intervention, but it must be more regular and it must include access to a lawyer.
“I am still not satisfied that Mr Tsege has been given an ability to challenge his detention through a legal process, something we are now pursuing further. The Foreign Office will continue to provide consular support to Mr Tsege and his family.”
The latest ministerial action may be due to pressure from diplomats. In February the Mail on Sunday obtained documents that highlighted diplomats’ frustration at political inaction over the abduction, which they felt was illegal.
The Mail reported:
Foreign Secretary Philip Hammond’s office said he could not ‘find time’ for a phone call to raise the issue and did not want to send a ‘negative’ letter.
In one email, an exasperated official asks: ‘Don’t we need to do more than give them a stern talking to?’
Regarding Tsege’s extradition, one Foreign Office official wrote: “It feels a bit like I’m throwing the kitchen sink at the Yemenis but I want them to think twice before they do this again.”
The same official noted a prominent Ethiopian minister had given assurances over Tsege’s treatment – but added: “I wouldn’t take them with complete confidence.”
The officials also called into question the evidence that had led to Tsege being branded a terrorist: “All we have seen are a few pictures of him standing in an Eritrean village – hardly proof that he was engaged in terrorist training.”
Maya Foa, head of the death penalty team at legal charity Reprieve, said: “Grant Shapps’ promise to stand ‘shoulder to shoulder’ with Ethiopia will be cold comfort to Andy Tsege’s desperate family in London. Even the UK’s limited requests for proper consular access have been flatly ignored by our allies in Ethiopia.
“Andy is a British father who is the victim of a series of terrible abuses by the Ethiopian government – from kidnap to torture to an in-absentia death sentence. The UN itself has demanded Andy’s return to the UK, as have thousands of members of the British public.
“The government must do the same, and call for Andy’s immediate release – today seems to have been a missed opportunity to do so.”
Alan White is a reporter for BuzzFeed News and is based in London.
Contact Alan White at alan.white@buzzfeed.com.

ሶማሊያ የሚገኙ የጦር ሠራዊት አባላት ሲበደሉ ያመናል !

def-thumbየተባበሩት መንግሥታት ማኅበር የሚሰጠው ገንዘብ ህሊናቸውን በሰወራቸው፤ የህወሓት አባላት በሆኑ ጄኔራሎች አዝማችነት ሶማሊያ የገባው ኢትዮጵያዊ ድሃ ወታደር እጣ ፈንታ በጣም አሳዛኝ ደረጃ ላይ ደርሷል። በየእለቱ ኢትዮጵያዊያንወታደሮች እየተገደሉ፤ አስከሬናቸው በጎዳናዎች እየተጎተተና እየተቃጠለ ነው። ሶማሊያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ወገኖቻችን ናቸውና በእነርሱ ላይ የሚደርሰው ስቃይ ይሰማናል፤ ሲበደሉ ያመናል፤ ጭንቀታቸው ይጨንቀናል። ወገኖቻችን ናቸውና የደህንነታቸው ጉዳይ ያገባናል።
የህወሓት ጄኔራሎች ሙሉ ትኩረታቸው ያለው በእያንዳንዱ ወታደር ስም ከተባበሩት መንግሥታት በሚያገኙት ገንዘብ መጠን ላይ ነው። ለሶስት ሣምንታት ብለው የገቡበት ጦርነት እነሆ አስር ዓመታት አስቆጥሯል። አንዱ የገቢያቸው ምንጭ ነውና ጦርነቱ ለሌላ አስር ዓመታት ቢራዘም ለእነሱ ደስታቸው ነው። ኢትዮጵያዊው ምስኪን ወታደር ግን አዛዦቹ እንዲያልቅ በማይፈልጉት ጦርነት ውስጥ ገብቶ መስዋዕትነት ይከፍላል፤ ሲወድቅ የሚያነሳው የለም፤ መስዋዕት ሲሆን የክብር አሸናኘት የለውም፤ ቤተሰቦቹም ይኑር ይሙት አያውቁም። ይህ ሁላችንንም ሊያስቆጣ የሚገባ ግፍ ነው።
ኢትዮጵያን ለመታደግ ብሎ የዘመተን ወታደር ስለኢትዮጵያ ግድ በማይሰጣቸው፤ ጥቅማቸውን ብቻ በማሳደድ ላይ ያሉ አዛዦች ቸልተኝነት ምክንያት ለስቃይ፣ ሰቆቃና ውርደት መዳረግ የለበትም። በሶማሊያ በሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ የሚደርሰው በደል በሁላችም ላይ የደረሰ በደል ነው፤ በእነርሱ ስብዕና ላይ እየደረሰ ያለው ውርደት በአገራችን ላይ የደረሰ ውርደት ነው።
የጦሩ አዛዦቹ በወታደሩ ስቃይና ሞት ከብረው የከተማ ድሆችን እያፈናቀሉ ሕንፃዎችን እየገነቡ፤ የባንኩን፣ የኢንሹራንሱን፣ የገቢና ወጪ ንግዱን እያጧጧፉ ነው። የወታደር ልብስ ቢለብሱም፤ “ጄኔራል እከሌ” ተብለው ቢጠሩም በተግባር መጥፎ ነጋዴዎች እንጂ ወታደሮች አይደሉም። እነዚህ የስም ጄኔራሎች በጦርነት ውስጥም የሚታያቸው ንግድና ገበያ ነው። በእንደነዚህ ዓይነቶች አዛዦች ተመርቶ ጦርነትን ማሸነፍ አይቻልም።
አርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ በህወሓት የጦር አዛዦች ብቃት ማነስ፣ ስግብግብነትና ቸልተኝነት ሳቢያ በሶማሊያ እየሞቱ፣ እየቆሰሉ፣ አስከሬናቸው እየተዋረደ ስላለው ኢትዮጵታዊያን የሚሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል።
ከሶማሊያ ውጭም የኢትዮጵያ ወታደር የሚገኝበት ሁኔታ እጅግ አሳዛኝ ነው። በተለይም በሀገር ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደር እንደ ስሙ “የአገር መከላከያ ሠራዊት” በመሆን ፋንታ ወገንን ማጥቂያ ሠራዊት እየሆነ ነው፤ አገርን በመከላከል ፋንታ ወገንን ማጥቃት የሠራዊቱ የዕለት ተዕለት ተግባር ሆኗል። ለዚህ አሳፋሪ ተግባር ሠራዊቱ ራሱ መላ ሊፈልግለት ይገባል።
አርበኞች ግንቦት 7 እየታገለ ያለው ሠራዊቱን ከሚገኝበት ከዚህ አሳፋሪ ሁኔታ ለማውጣትም ጭምር ነው። ሠራዊቱ የአዛዦቹ መገልገያ መሣሪያ መሆኑ ማብቃት አለበት። ሠራዊቱ ወገንን ማጥቂያ መሆኑ ማክተም አለበት። ሠራዊቱ ወደ ውጭ አገራት ለግዳጅ ሲላክ ተገቢውን ክብር ሊሰጠው፤ ጥቅማ ጥቅሞቹም ሳይሸራረፉ ሊያገኝ ይገባል። የሠራዊቱ አባላት እየደኸዩ፣ ቤተሰቦቻቸው እየተራቡና እየታረዙ አዛዦቹ በሀብት ላይ ሀብት የሚያጋብሱበት ሁኔታ ማብቃት አለበት። ይህ አዋራጅ የሠራዊት አያያዝ መቀየር አለበት፤ መቀየር ደግሞ ይቻላል።
እያንዳንዱ የሠራዊት አባል በግል የጠራ ፀረ-ህወሓት አገዛዝ አቋም ይያዝ፤ ከሚመስሉት ወዳጆቹ ጋር ውስጥ ውስጡን ይምከር፤ አርበኞች ግንቦት 7 ጋር የምስጢር ግኑኝነት ለመመስረት ይጣር፤ ጦሩ ውስጥ እያለ ሥርዓቱን የሚዳክሙ ተግባራትን ይፈጽም። ህወሓትን ለማዳከም የሚደረግ ጥረት ትንሹም ትልቅ ዋጋ አለው። ሠራዊቱ የህወሓት መገልገያ አለመሆኑ ማስመስከሪያ ወቅት አሁን ነው። የህወሓት አምባገነን አገዛዝን ከውስጥም ከውጭም ሆነን እንፋለመዋለን፤ እንደምናሸንፍ ጥርጥር የለውም።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Monday, 19 October 2015

ውሸት ውሎ አድሮ መጋለጡ አይቀርም!!!


  • October 16, 2015
def-thumbሥልጣንን በጠመንጃ አፈሙዝ ተቆጣጥሮ ያለው የወያኔ አገዛዝ ካለመታከት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ተአምር ሊመስል በሚችል  መንገድ እያሳደኩ ነው እያለ ሲዋሽ አመታት ተቆጥረዋል። በተለይ ምዕራባዊያንን ሲያታልልበት የነበረው የዲሞክራሲ ጭንብል በምርጫ 97 ከተገፈፈበት ወዲህ ላለፉት አስር አመታት ባለ ሁለት አሃዝ እድገት አስመዝግቤያለሁ እያለ እጅ  እጅ እስኪለን ድረስ በባዶ ሜዳ ስለ ልማትና የዕድገት ሲነግረን ሰነበቷል።
ወያኔ በጉልበት በሚያስተዳድራት ኢትዮጵያ የልማትና የእድገት ፕሮፓጋንዳ ስለ ሰበአዊ መብትና ስለዲሞክራሲ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለማፈኛና አፍ ለማዘጊያነት በማገልገል ላይ ይገኛል ። አለማቀፍ የሰባአዊ መብት ተቋማት ስለሰበአዊ መብት ጥሰት ለሚያቀርቡት አቤቱታ ሁሉ የሚሰጠው መልስ “ኢኮኖሚውን እያሳደግን ነው” የሚል ነው። ኢኮኖሚ ማደግ አለማደጉን ትርጉም የሚኖረው ከህዝብ የእለተ ተእለት ኑሮ ጋር ሲያያዝ መሆኑ ሁሉ  ትርጉም አጥቷል። ራበኝ የሚለው ሰው ሁሉ ጠገብኩ ማለቱ ነው ተብሎም ይተረጎማል።
የውሸት ነገር ውሎ አድሮም ቢሆን መጋለጡ አይቀርምና ይኼው በቅርቡ የተከሰተው ድርቅ የወያኔን የውሸት ፕሮፓጋንዳ ክንብንብ ገፎታል። አለም በሙሉ አስር አመት ሙሉ በሁለት አሃዝ ሲያድግ የነበረ ኢኮኖሚ ባለበት ሃገር ውስጥ አንዲት የድርቅ አመት ካለርሃብና ልመና እንዴት መሻገር አቃተው የሚል ጥያቄ በሰፊው በማንሳት ላይ ነው። ወያኔ ለዚህ ጥያቄ መልስ የለውም።  በአለም ዙሪያ ያለው ተመክሮ ሁሉ የሚያሳየው ወያኔ አድጌበታለሁ ብሎ ሲለፍፍ ከኖረው አሃዝ በታች በግማሽ ያደጉ ሃገሮች እንኳ አንድም ጊዜ አንድ የድርቅ ዘመን መሻገር አቅቶአቸው  ሲንገዳገዱና መንግሥታቸው ለልመና ሲሄድ አለመታየቱን ነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔ የሚያወራውን ያህል ያልሆነ ቢሆንም በአንዳንድ ከተሞች አካባቢ የሚታየው እድገት የተገኘው ከውጭ መንግስታት የገንዘብ ብድር፣ በአለም አቀፍ ተቋማት እርዳታ፣ ስደተኛው ኢትዮጵያዊ በገፍ በሚልከው ገንዘብና ወያኔ ከድሃውና ከነጋዴው ከዝርፊያ ባላነሰ ሁኔታ በሚሰበሰበው ግብርና መዋጮ የተገኘ እንጂ ወያኔ ባስፋፋው ኢንዱስትሪና ልማት እንዲሁም ሀገር ውስጥ በፈጠረው ሀብት አለመሆኑ የሚታወቅ ነው።
የወያኔ ሹማምንትና አገልጋዮች ሀብት በሀብት መሆናቸውን እንደ እድገት ካልቆጠርን በስተቀር  ህዝባችን ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮውን እንኳን መደጎም አልቻለም ።በዝርፊያ ገንዘብ ሹማምንቱና የወያኔ ባለምዋሎች የገነቡትን ፎቅ የሀገር ልማት ነው ካላልን በስተቀር እውነተኛና የህዝብ ህይወት ከመሰረቱ የሚቀይር ልማት አገር ውስጥ አለመካሄዱ ትንሽ ገለጥ ሲያደርጉት የሚታይ ሃቅ ነው። አንድ የድርቅ ወቅት መሻገር አቅቶት ብዙ ሚሊዮኖችን ከረሃብና እልቂት መታደግ ያልቻለ ኢኮኖሚ አስር አመት ሙሉ በሁለት አሃዝ አድጓል ብሎ የሚያምን ሰው ሊኖር አይችልም።
የወያኔ የኢኮኖሚ አሃዝ “መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ” ከሚለው የሀገራችን ግፈኛ አባባል  ብዙም አይለይም። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለህዝብ በሚጠቅም መንገድ የማደጉ ጉዳይ በመጀመሪያ ፍትሐዊ ኢኮኖሚያዊ ሥርአት መገንባትንና ዴሞክራሲ ማስፈንን ይጠይቃል።
በመሆኑም የዛሬው የወያኔ ኢኮኖሚ የዝርፊያ ኢኮኖሚ እንጂ ህዝባዊ ሽታ የለውም። የኢትዮጵያን ህዝብ እዚህና እዚያ በሚብለጨለጩ ያውም በአብዛኛው በብድርና እርዳታ በተገኙ ልማት ተብዬ ነገሮች ለረዥም ጊዜ ማታለል አይቻልም።
ወያኔ በሚሰጠው አሃዝ የሚያድግ ማንኛውም ሀገር የውጭ ስደተኞችን ያስተናግድ እንደሆን እንጂ ወጣቶች ሞትና ህይወትን አማራጭ አድርገው አይሰደዱበትም። ባለ ሁለት አሃዝ አዳጊ ኢኮኖሚ በየትም ሀገር የስደተኞች ምንጭ ሆኖ ታይቶ አይታወቅም በዘረኛው ወያኔ ተገዢዋ ኢትዮጵያ ካልሆነ በስተቀር።
አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ትንሳኤ ከዘራፊው የወያኔ ሥርዐት መወገድ ጋር በጥብቅ የተሳሰረ መሆኑን ያምናል!  ስለዚህም ህዝባችን ወያኔን ለማስወገድ የተጀመረውን ትግል በነቂስ ለመቀላቀል ዛሬውኑ እንዲነሳና ከጎናችን እንዲሰለፍ የማያቋርጥ ጥሪውን ደግሞ ደጋግሞ ያስተላልፋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Tuesday, 13 October 2015

ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጀርባ – አርበኞች ግንቦት 7



October 10, 2015
def-thumbከሁለት አመት በፊት በቂ ህዝባዊ ምክርና ውይይት ያልተካሄደበት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተግባር ላይ ለማዋል የተደረገው ሙከራ በበርካታ የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ እንደገጠመውና በየኮሌጁ በተነሱ ተቃውሞዎች ሳቢያ በርካታ ወጣቶች በወያኔ እንደተገደሉ ብዙዎች በእስር እየማቀቁ እንዳሉ ይታወቃል። ግጭቱ የፈጠረው ቀስል ገና ባላገመ ማግስት በአሁኑ ወቅት የህወሃቱ አባይ ጻሀይ በውድም በግድም ፕላኑ “ይተገበራል” ብሎ በዛተው መሰረት ተግባር ላይ ለማዋል ሰሞኑን ሽር ጉድ ተይዟል።
ከዚህ ማስተር ፕላን በስተጀርባ የተደበቀው የህወሃትና ጀሌዎቹ አላማ በአግባቡ አለመተንተኑ የፕላኑ ተቃዋሚዎች ኦሮሞዎች ብቻ በመሆናቸው ጥያቄው የግዛት ስፋትና ጥበት ወይም ባለቤትነት ጉዳይ መስሎ ይታይ እንጂ ነገሩ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚያስቆጪና ተቃውሞ ሊያስነሳ የሚገባው ደባ ነው። ከህወሃት/ ወያኔ ማስተር ፕላኑ ጀርባ የመሬት ዝርፊያ እቅድ እንዳለው አርበኞች ግንቦት 7 ከእስከ አሁኑ ተመክሮና ባህሪያቸው በግልጽ ማየት ይቻላል ብሎ ያምናል።
እስከዛሬ ባለን ተመክሮ ከተማውን በማስፋፋት ስምና መሬት የመንግስት ነው የሚለውን ሰበብ በመጠቀም ድሃ ገበሬዎችን በማፈናቀል የተዘረፈውን መሬት ልብ ማለትና ማስታዎስን ያሻል።
በሀገራችን ቅጽበታዊ ሚሊየነር የሆኑት የወያኔ ሹማምንት፣ ዘመዶቻቸውና ባለሟሎቻቸው ዋናው የሃብታቸው ምንጪ ድሆችን በማፈናቀል በገፍ እየዘረፉ የሸጡትና የተቆራመጡት መሬት ነው። የአዲስ አበባ መሬት የወያኔ የወርቅ ማእድን ጉድጓድ ከሆነ ቆይቶል። በየከተማው ዙሪያ ያሉ ምስኪን ገበሬዎች የረባ ካሳ እንኮን ስላላገኙ ከግብርና ወጥተው ወደኩሊነትና የቀን ሰራተኝነት ተበታትነው ቤታቸው ፈርሶ ይገኛል።
የወያኔ መንግስት ይህን ማስተር ፕላን ስራ ላይ ለማዋል የሚስገበገብበት ዋናው ምክንያት የሀገርና ከተማ ልማት ጉዳይ አይደለም። የከተማው መሬት ተዘርፎ በማለቁ ሌላ በገፍ የሚዘረፍ መሬት ለማመቻችት ብቻ ነው። ችግሩ ለምን ፕላን ኖረ፣ አዲስ አበባ በአግባቡ ማደግና መልማት የለባትም የሚል አይደለም። ቁምነገሩ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በቅጽበት እያፈናቀለና እየደኸዩና ቤተሰብ እየፈረሰ፤ በጥቂት ህገ ወጥ ባለስልጣናት የሚደረገው ሀፍረት የለሽ ዝርፊያ ነው ችግሩ። በመሆኑም ይህን የዝርፊያ ተግባር ብሄረሰብ ሳንለይ ሁላችንም ልንቃወም ይገባል። ይህ ማስተር ፕላን የህግ የበላይነትና ተጠያቂነት በሌለበት ሁኔታ ስራ ላይ በአግባቡ ስራ ላይ መዋል አይችልም። በፕላኑ የተጠቃለለውን ህዝብና አካባቢ ሊጠቅም የማይችል ፕላን ሊሆን የሚችለው የዝርፊያ ፕላን ብቻ ነው።
የወያኔ መንግስት በሰፈራ ሁኔታ ባካሄደው የከተማ ቦታ ዝርፊያ ነው ዛሬ በየመሸታ ቤቱና በየከተማው ዋና ዋና መዝናኛ ቦታዎች ብር እንዳሻቸው የሚነዙ የወያኔ ቱባ ባለሟሎች የተፈጠሩት። ወያኔ ሌላው ቀርቶ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ዘረኝነት በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ እናውቃለን።
መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን በማር የተላወሰ መርዛማ ፕሮጀክት አጥብቆ እንዲታገል አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪውን ያቀርባል።
በሀገራችን ጥቂቶች እያረፉ የሚከብሩበት ድሃ ወገኖቻችን ይበልጥ እየደኸዩ የሚሄዱበት ዘመንና ስርአት አለንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲወገድ ወጣቱ አርበኞች ግንቦት 7ን ባለበት ይቀላቀል። ትግላችን እስከመጨረሻው ድል ይቀጥላል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
አርበኞች ግንቦት 7

Sunday, 4 October 2015

ድርጅታችንን እናጠንክር፤ በጽናት እንታገል!

October 3, 2015
def-thumb“የአርበኞች ግንቦት 7 አባል በመሆኔ እኮራለሁ” እያሉ በአገዛዙ የይስሙላ ችሎት ሳይቀር በድፍረት የሚናገሩ ወጣቶች ተፈጥረዋል። ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነትና ለሀገር አንድነት መስዋዕትነት መክፈል የሚያኮራ ተግባር መሆኑ በተግባር የሚያሳዩ ወጣቶች መጥተዋል፤ አሁን በርካቶችም እየመጡ ነው። ወያኔ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በማኅበረሰባችን ውስጥ የዘራው የፍርሀትና የአድርባይነት ስሜት በራሱ በወያኔ የአገዛዝ ዘመን ተወልደው ባደጉ ወጣቶች እየተናደ፤ በምትኩ ሊጠፋ ተቃርቦ የነበረው የአገር ፍቅርና የአርበኝነት ስሜት እያንሰራራ ነው።
ቅንነት፣ ሀቀኝነት እና ጽናት ከተጣሉበት ጉድጓድ አቧራቸውን አራግፈው እየተነሱ ነው። በማኅበረሰባች ውስጥ ትልቅ የስነልቦና አብዮት እየተካሄደ ነው።
ከስነልቦና ለውጡ ጋርም በተግባር የአገር አድን ሠራዊትን የመቀላቀል ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ነው። ወጣቶች የአገራቸው ባለቤት መሆናቸው ተገንዝበው የፓለቲካ ሥርዓት ለውጥ ለማምጣት በቁርጠኝነት መነሳታቸው ተስፋ ሰጪ ነገር ነው።
አርበኞች ግንቦት 7 በዚህ የለውጥ ወቅት ውስጥ ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አጽንዖት ልንሰጣቸው ስለሚገቡ የድርጅትና የሥነሥርዓት (ዲሲፕሊን) አስፈላጊነት ላይ የጋራ ግንዛቤ መያዝና በተግባርም መተርጎም አስፈላጊ ነው ብሎ ያምናል።
ወጣቶች ትግሉን ለመቀላቀል መሻታቸው መልካም ነገር ነው። ሆኖም ግን በድንገት ብድግ ብለው መንገድ ከመጀመር ይልቅ ከሚያምኗቸው ወዳጆቻቸው ጋር የመሠረቱት፤ ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋርም ትስስር የፈጠረ ስብስብ አካል ሆነው መቆየታቸው እጅግ አስፈላጊ ነው።
በአምባገነን ሥርዓት ውስጥ ሆኖ የሚስጢር ድርጅት ማዋቀር አስቸጋሪ መሆኑ የማያጠራጥር ቢሆንም የማይቻል ነገር ግን አይደለም። ወጣቶቻችን በአምባገነን ሥርዓት ውስጥም ሆነው በዲሲፕሊን የታነፀ ድርጅት የመፍጠርን ክህሎት መላበስ ይገባቸዋል። ይህንን ማድረግ ስንችል ነው የህወሓትን ፀረ-አገርና ፀረ-ትውልድ ተግባር ማክሸፍ የምንችለው። ትግሉን በሁሉም የኢትዮጵያ ግዛቶች ማቀጣጠል የምንችለው በየአካባቢው የተደራጀ የለውጥ ኃይል ሲኖረን ነው። ስለሆነም የምስጢር የተደራጀ አካል በየመኖሪያና የሥራ አካባቢዎቻችን ሁሉ እንዲኖር ማድረግ ከአጣዳፊ ሥራዎቻችን አንዱ እናድርገው።
ሁለተኛው ነጥብ ሥነሥርዓትን የሚመለከት ነው። ሥነሥርዓት ከሌለ ድርጅት የለም። የህወሓት አገዛዝ ያሳደረብን ጎጂ የባህል ተጽዕኖ ከባድ በመሆኑ ራሳችንን በሥነሥርዓት ለማነጽ መልፋት ይጠበቅብናል። አገራችንና ራሳችንን ከህወሓት አገዛዝ ነፃ አውጥተን የተሻለ ሥርዓት ማምጣት የምንችለው ራሳችን፣ ድርጅታችን እና ተግባሮቻችን ለሥነሥርዓት ተገዢ ስናደርግ ነው። የነፃነት ታጋዮች ራሳቸውን ለሥነ ሥርዓት ያስገዙ መሆን ይኖርባቸዋል። አስተሳሰባችን ራሱ ሥነ ሥርዓት የያዘ ሊሆን ይገባዋል። እንደዚሁም ሁሉ ተግባሮቻችን በሥነሥርዓት የታነጹ ሊሆኑ ይገባል።
የንቅናቄዓችንን መዋቅር በመላው አገራችን ከዘረጋን፤ ራሳችንን፣ አስተሳሰቦቻችንና ተግባሮቻችን በሥነሥርዓት ከመራን፤ ቅንነት፣ ሀቀኝነትና ጽናት ከተላበስን ድላችን ቅርብ እና አስተማማኝ ነው። ለውጥን የሚናፍቅ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራት ይተግብር።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!